Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በ850 ሚሊዮን ብር የተገዙ አምስት ዘመናዊ የኬሚካል ርጭትን ጨምሮ ዘርፈ ብዙ አገልግሎት የሚሰጡ ዘመናዊ የርጭት አውሮፕላኖች (ኤር ትራክተርስ)‼️
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
የነቀምቴ ጉዲና ቱምሳ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የበረራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተካሄደ
********************
(ኢ ፕ ድ)

የነቀምቴ ጉዲና ቱምሳ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የበረራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተካሂዷል፡፡

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳሰታወቁት የአውሮፕላን ማረፊያው ተገንብቶ አገልግሎት መጀመር በአካባቢው የሚገኘውን የተፈጥሮ ጸጋ በተሻለ ለማልማት እና የንግድና ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ለማስፋት ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው አስረድተዋል፡፡

አካባቢው ያለውን የቱሪዝም ሀብት ጥቅም ላይ ለማዋል፣ የሕዝቦችን ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ ለማቀላጠፍ ብሎም በአጠቃላይ የሕዝቡን ሕይወት ለመቀየር ጉልህ ሚና አለው ብለዋል፡፡

በበረራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ፣ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው፣ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መሥተዳድር አወሉ አብዲ እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በምሥራቅ ወለጋ ዞን ነቀምቴ ከተማ የተገነባ የሚገኘው የነቀምቴ ጉዲና ቱምሳ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የረጅም ዓመታት ጥያቄያቸውን የመለሰ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች መናገራቸውን ከኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ የማኀበራዊ የትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

ሰኔ 9 ቀን 2016 ዓም
ኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍን ለኃይል አማራጭነት ለመጠቀም እየሠራች ነው
********
(ኢ ፕ ድ)

ኢትዮጵያ በሀገሪቱ የሚገኙ ዋና ዋና ማዕድናትን ለኃይል አማራጭነት በማዋል የካርበን ልቀትን ለመቀነስ እየሰራች ነው ሲል የማዕድን ሚኒስቴር አስታወቀ።

የማዕድን ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሚሊዮን ማትዮስ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍን ለኃይል አማራጭነት በመጠቀም የካርበን ልቀትን ለመቀነስ እየሰራች ትገኛለች።

ኮፐር፣ ኒኬል፣ ኮባልት፣ ሊቲየም እንዲሁም ሌሎች ውድና ለኃይል አማራጭ የሚሆኑ የማዕድን ዓይነቶች በኢትዮጵያ የሚገኙ ስለመሆኑ በተለያዩ መንገዶች መረጋገጡን ያመላከቱት አቶ ሚሊዮን፤ ይህም ሀገሪቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ አሳሳቢ ሁኔታ ላይ የደረሰውን የካርበን ልቀት ለመቀነስ......

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=130092
ስምንት ነጥብ ስድስት ሚሊዮን አርሶ አደሮች ኩታ ገጠም ግብርናን እየተገበሩ ነው
***
(ኢ ፕ ድ)

ስምንት ነጥብ ስድስት ሚሊዮን የሚሆኑ አርሶ አደሮች ማሳቸውን በኩታ ገጠም እያለሙ መሆኑን የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ገለጸ።

የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ማንደፍሮ ንጉሤ (ዶ/ር) ለኢፕድ እንደተናገሩት፤ ኢንስቲትዩቱ ኩታ ገጠም እርሻን ማስፋፋት ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ነው።

በዚህም አርሶ አደሮች በ11 ሰብሎች በኩታ ገጠም እየሠሩ ነው ያሉት ዶክተር ማደፍሮ፤ ከነዚህ ውስጥ ስንዴ፣ በቆሎ፣ ጤፍ፣ ሰሊጥ፣ አኩሪ አተርና የቢራ ገብስ ተጠቃሽ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ከፍራፍሬም አቮካዶ፣ ማንጎ እና ሙዝ እንዲሁም ከአትክልት ቲማቲም እና ሽንኩርት በኩታ ገጠም እየለሙ መሆኑን ተናግረዋል።

የኩታ ገጠም እርሻን የማልማት ሂደት አርሶ አደሮች በተመሳሳይ ጊዜ የማረስ፣ ዘር የመዝራት፣ የግብርና ምርትን የሚያሳድጉ ግብዓቶችን በጋራ የመጠቀም እድል የሚፈጥር......

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=130089
በግንቦት ወር ከቡና የወጪ ንግድ ከ209 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል
*******
(ኢ ፕ ድ)

በግንቦት ወር 43 ሺህ 481 ቶን በላይ ቡና በመላክ 209 ነጥብ 54 ሚሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን የቡናና ሻይ ባለስልጣን ገለጸ።

የቡናና ሻይ ባለስልጣን የሕዝብ ግንኙነትና የኮሚዩኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሳህለማርያም ገብረመድህን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በተያዘው በጀት ዓመት በግንቦት ወር ብቻ 43 ሺህ 481 ቶን ቡና በመላክ 209 ነጥብ 54 ሚሊዮን ዶላር ተገኝቷል።

በበጀት ዓመቱ 11 ወራት ውስጥም በአጠቃላይ 252 ሺህ 466 ነጥብ 98 ቶን የቡና ምርት በመላክ አንድ ቢሊዮን 208 ሚሊዮን 73 ሺህ ዶላር ተገኝቷል።

ይህ ውጤት ካለፉት ሦስት ተከታታይ ዓመታት ተመሳሳይ ወቅት ወደ ውጭ ከተላከው ምርት እጅግ ከፍተኛ ውጤት የታየበት ነውም ብለዋል።ለውጤቱ መገኘት መንግሥት ለዘርፉ የሰጠው ከፍተኛ ትኩረት የጎላ ድርሻ ያለው መሆኑን ጠቅሰው፤ ቡናን ከሚያለማው አርሶ አደር ጀምሮ ቡና አቅራቢና ላኪዎች.......

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=130099
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
"የቦረና ዳልጋ የከብቶች ዝርያ ማሻሻያና ማራቢያ ማዕከል በሙሉ አቅሙ እየሰራ ነው" - የቦረና ዞን ግብርና ጽህፈት ቤት
**
(ኢ ፕ ድ)

በዞኑ ተከስቶ በነበረው ድርቅ  ምክንያት ተጎድቶ የነበረው የቦረና ዳልጋ ከብቶች ዝርያ ማሻሻያና ማራቢያ ማዕከል በሙሉ አቅሙ እየሰራ መሆኑን የቦረና ዞን ግብርና ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

የኦሮሚያ ክልል የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌቱ ገመቹ ጨምሮ ሌሎች የቢሮው ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች  በኦሮሚያ ክልል በቦረና ዞን የሚገኘው የዳልጋ  ከብቶች ዝርያ ማሻሻያና ማራቢያ ማዕከል ጎብኝተዋል።

የግብርና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጃለላ ዱለቻ እንደገለጹት፤ የቦረና ዳልጋ ከብቶች ዝርያ ማሻሻያና ማራቢያ ማዕከል የሚያስፈልገው ግብዓት አሟልቶ በሙሉ አቅሙ እየሰራ ነው።

ማዕከሉ በቀጣይ ዝርያዎቹን ለአርብቶ አደሩ ለማከፋፈል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።

የቦረና ዳልጋ የከብቶች ዝርያ ማሻሻያና ማራቢያ ማዕከል ኃላፊ ተወካይ ዲዳ ኮንሶ በበኩላቸው ድርቁ በተከሰተበት ወቅት 200 የነበረው አሁን ከ450 በላይ ማሳደግ ተችሏል።

በልጅዓለም ፍቅሬ(ቦረና ዞን)

ሰኔ 10 ቀን 2016 ዓም