"የቦረና ዳልጋ የከብቶች ዝርያ ማሻሻያና ማራቢያ ማዕከል በሙሉ አቅሙ እየሰራ ነው" - የቦረና ዞን ግብርና ጽህፈት ቤት
**
(ኢ ፕ ድ)
በዞኑ ተከስቶ በነበረው ድርቅ ምክንያት ተጎድቶ የነበረው የቦረና ዳልጋ ከብቶች ዝርያ ማሻሻያና ማራቢያ ማዕከል በሙሉ አቅሙ እየሰራ መሆኑን የቦረና ዞን ግብርና ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
የኦሮሚያ ክልል የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌቱ ገመቹ ጨምሮ ሌሎች የቢሮው ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በኦሮሚያ ክልል በቦረና ዞን የሚገኘው የዳልጋ ከብቶች ዝርያ ማሻሻያና ማራቢያ ማዕከል ጎብኝተዋል።
የግብርና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጃለላ ዱለቻ እንደገለጹት፤ የቦረና ዳልጋ ከብቶች ዝርያ ማሻሻያና ማራቢያ ማዕከል የሚያስፈልገው ግብዓት አሟልቶ በሙሉ አቅሙ እየሰራ ነው።
ማዕከሉ በቀጣይ ዝርያዎቹን ለአርብቶ አደሩ ለማከፋፈል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።
የቦረና ዳልጋ የከብቶች ዝርያ ማሻሻያና ማራቢያ ማዕከል ኃላፊ ተወካይ ዲዳ ኮንሶ በበኩላቸው ድርቁ በተከሰተበት ወቅት 200 የነበረው አሁን ከ450 በላይ ማሳደግ ተችሏል።
በልጅዓለም ፍቅሬ(ቦረና ዞን)
ሰኔ 10 ቀን 2016 ዓም

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ከኢፕድ ጋር በነበራቸው ቆይታ ካነሷቸው ሀሳቦች‼️
👉 ገና በጥናት ያልተደረሰባቸውን ሳይጨምር፣ ክልላችን ከሁሉም በበለጠ በማዕድን ሀብት የበለፀገ ክልል ነው፣
👉 በ2014 ዓም ሁለት ሺህ 300 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሄራዊ ባንክ ገቢ ተደርጓል፤
👉 ካማሽ ዞን ላይ የድንጋይ ከሰል ማምረት ተጀምሯል፣
👉 ሌላው የማእድን ሀብት እጣን ነው፣ ወጣቶች አንድ ኩንታል እጣን 40 ሺህ ብር በመሸጥና ተጠቃሚ ሆነዋል፣
👉 ከለውጡ በፊት ከ700 ሺህ ሄክታር በላይ አምርቶ አያውቅም ፣ ከለውጡ በኋላ ግን ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሄክታር መሬት በአርሶ አደር ብቻ ለምቷል፣
👉በተለያዩ ዘርፎች ከ900 በላይ ባለሀብቶች ፍቃድ ወስደው ወደ ሥራ በመግባት ላይ ይገኛሉ፤
👉 በተለያዩ ዘርፎች ከ34 ሺህ በላይ የሥራ እድል ተፈጥሮ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፣
👉 11 የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች አሉ፤ ሰባቱ አነስተኛ የመሰኖ ፕሮጀክቶች ናቸው፣
👉 አምስት የመጀመሪያ ደረጃ (ፕራይመሪ) ሆስፒታሎች ተገንብተዋል፣
👉 የሰላም ችግሮቻችንን ሙሉ ለሙሉ ካስወገድን በጥቂት ዓመታት የፈለግነው የብልፅግና ምእራፍ ላይ እንደርሳለን፣
👉 ባለፉት ስድስት ዓመታት ውስጥ በክልላችን የተመዘገበው ትርጉም ያለው ለውጥ ነው፡
👉 ከለውጡ በኋላ ግን ወደ ላይ ተስቦ የተወሰደው መሬትና የመሬት ጉዳይ ወደ ክልሉ እንዲመለስ ተደርጎ ለባለሀብቶች በመሰጠቱ ምክንያት በርካታ ባለሀብቶች ወደ ሥራ ገብተዋል
👉 የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሕዝብ ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል አስተሳሰብና ማንነትን ያዳበረው ገና አሁን ነው፣
👉 እራሱን በራሱ በትክክል ማስተዳደር የጀመረው ከለውጥ በኋላ ነው፣
ዝርዝር መረጃውን ለማግኘት ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=130127

በከተማዋ የሚገኙ 35 ትምህርት ቤቶች ለ2017 የትምህርት ዘመን ምዝገባ እንዳያካሂዱ ዕገዳ ተጣለ
*******
(ኢ ፕ ድ)
በአዲስ አበባ የሚገኙ 35 የቅድመ አንደኛ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለ2017 የትምህርት ዘመን ምዝገባ እንዳያካሂዱ ማገዱን የአዲስ አበባ ትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን አሰታወቀ።
ለ2017 የትምህርት ዘመን የሚቀጥሉና የማይቀጥሉ የትምህርት ተቋማትንም ይፋ አድርጓል።
የአዲስ አበባ ትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ዳኛዉ ገብሩ እንደገለጹት፣ ለ2017 የትምህርት ዘመን ባደረገዉ ቁጥጥር የፖሊሲ ጥሰት የፈጸሙና የትምህርት መመሪያዎችን ያላሟሉ 35 የቅድመ አንደኛ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የግል ይዞታ ያላቸዉ ትምህርት ቤቶች ላይ እገዳ ጥሏል።
ከእነዚህ ትምህርት ቤቶች መካከልም የካ፣ ልደታ ጉለሌና ንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ የሚገኙ የጊብሰን ትምህርት ቤቶች፣የቅዱስ ሚካኤል አምስት ትምህርት ቤቶች፣ የካ አፖሎ ትምህርት ቤት ይገኙበታል።
የቅዱስ ሚካኤል ትምህርት ቤቶች የስያሜ ለዉጥ በማድረግ ለመቀጠል በመጠየቁም ጉዳዩ እየታየ መሆኑ ተገልጿል።
ዕገዳ በተጣለባቸዉ ትምህር ቤቶች ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች በመኖረያ አቅሪያቢያቸዉ በሚገኙ የግልና የመንግስት ትምህርት ቤቶች ያለምንም ተጨማሪ ክፍያ እንዲስተናግዱ ይደረጋል ብለዋል።
በተጨማሪም የተዘጉት ትምህርት ቤቶችም የተሟላ የተማሪዎችን ማስረጃ እንዲሰጡ እንደሚደረግ ገልጸዋል።
መስከረም ሰይፉ

አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከተባበሩት መንግስት ድርጅት ጠቅላይ ጉባኤ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ
****
(ኢ ፕ ድ)
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ የተባበሩት መንግስት ድርጅት ጠቅላይ ጉባኤ ፕሬዚዳንት አምባሳደር ዴኒስ ፍራንሲስን ጋር በአለም አቀፍና በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።
በውይይቱ ወቅት ኢትዮጵያና ተመድ አብረው በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች፣ በአለም አቀፍና በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብዩ ተድላ በሰጡት ማብራሪያ ገልጸዋል።
በአፍሪካ ቀንድ ጉዳይ የሀሳብ ልውውጥ ማድረጋቸውን የገለጹት አምባሳደር ነብዩ፣ ኢትዮጵያ ለቀጣናው መረጋጋት የምታደርገውን ጥረት በተመለከት አድናቆት ችረዋል ብለዋል።
አምባሳደር ዴኒስ ለታዳጊ የሀገራት አጀንዳዎች በተለይ የእዳ ቅነሳና ሽግሽግ፣ የዘላቂ ልማት አፈጻጸም ላይ ለሰጡት ትኩረት አምባሳደር ታዬ ምስጋና ማቅረባቸውን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ለባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ ትኩረት ሰጥታ እንደምትሰራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ ለተባበሩት መንግስት ድርጅት ጠቅላይ ጉባኤ ፕሬዚዳንት ማረጋገጫ መስጠታቸውን ቃል አቀባዩ ጠቅሰዋል።
በውይይቱ ኢትዮጵያ እያከናወነች ያለችውን የፖለቲካና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን በተመለተከተ ገለጻ ተድርጎላቸዋል።
በሞገስ ጸጋዬ

የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት‼️
የታላቁ ህዳሴ ግድብ መገኛ፣ የንጉስ ሼህ ሆጀሌ ሀገር፣ የወርቋ ምድር ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ገብተናል። በቆይታችንም በክልሉ የሚገኙ ልዩ ልዩ የልማት ስራዎችን የምንጎበኝ ይሆናል፡፡ በአሶሳ አውሮፕላን ማረፊያ የሞቀ አቀባበል ላደረጉልን የክልሉ ፕሬዝደንት እና ካቢኒያቸው እንዲሁም የአሶሳ ከተማ ህዝብ ላቅ ያለ ምስጋና አቀርባለሁ።

የአዲስ አበባ ካቢኔ በሦስት ዋና ዋና አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል
****
(ኢ ፕ ድ)
የአዲስ አበባ ካቢኔ 3ኛ አመት 14ኛ መደበኛ ስብሰባ በ3 ዋና ዋና አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል
👉 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ የሚገኙ ዋና ዋና መንገዶች ላይ ባሉ የሴትባክ (setback) ፕላን ትግበራ ከመንገድ ያላቸው ርቀት መጠን በካቢኔ ወስኖ ወደ ትግበራ መግባቱ ይታወሳል።
ከዚህ በፊት የተወሰኑ የሴት ባክ ለማስተግበር፤ ሂደቱን ለማሳለጥና አገልግሎቱን ለማፍጠን የቀረቡ በደንብ የተደገፉ ማብራሪያዎችን በጥልቀት ተወያይቶ በሙሉ ድምጽ አፅድቋል።
👉 የመንገድ ዳር መብራትና መሠረተ ልማቶች ለማስተዳደር የሚችል አስተዳደር ኤጀንሲ ማቋቋሚያ ደንብ መርምሮ አጽድቋል። በዚህም የመንገድ ዳር መብራቶችና መሠረተ ልማቶች ስንታንዳርዶችን ማውጣት፣ መቆጣጠር እንደ አስፈላጊነቱም በሚወጣው መመሪያ መሠረት ተገቢውን የቴክኒክ ድጋፍ የሚያደርግ ይሆናል።
👉 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን አደረጃጀት አሰራር ማሻሻያ ደንብን ካቢኔው መክሮበት አፅድቋል። ከተማዋ ከጊዜው ጋር የሚመጥን የፅዳት አጠባበቅ አጠቃቀምና የቆሻሻ አወጋገድና የተሸከርካሪ የመንገድ አጠቃቀም እንዲሁም የመንገድ ፍሳሽ አወጋገድ ያለአግባብ የመንገድ ላይ የመፀዳዳት ተግባራትን እንዲጠበቁ የሚያደርጉ የህግ ማዕቀፎችና ተጥሰው ሲገኙ ለማስከበር ህገወጥ አሰራሮችን ለመቅጣት የሚያግዙ የህግ ማዕቀፎችን የያዘ ነዉ፡፡