በዘንድሮ የመኸር እርሻ ከ20 ሚሊዮን ሔክታር በላይ መሬት ይታረሳል
*********************
(ኢ ፕ ድ)
በ2016/17 የመኸር ምርት ዘመን ከ20 ሚሊዮን ሔክታር መሬት በላይ መሬት እንደሚታረስ ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
እስከ ሰኔ ወር የመጀመሪያ ሳምንት ድረስ 14 ሚሊዮን ሔክታር መሬት የታረሰ ሲሆን ከ12 ሚሊዮን ሔክታር በላይ መሬት በኩታ ገጠም ለማልማትም እየተሠራ ነው፡፡
በግብርና ሚኒስቴር የሰብል ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ኢሳያስ ለማ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በዘንድሮ የመኸር እርሻ 20 ሚሊዮን 403 ሺህ 245 ሔክታር መሬት የታረሰ ሲሆን እስካሁን ባህላዊና ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም 14 ሚሊዮን ሔክታር ገደማ መሬት ታርሷል።
ከታረሰው መሬት ውስጥ ሶስት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ሔክታር የሚጠጋ መሬት በዘር ተሸፍኗል ያሉት አቶ ኢሳያስ፤ በዘር ከተሸፈነው መሬት ደግሞ ሁለት ሚሊዮን 69 ሺህ 153 ሄክታሩ በኩታ ገጠም
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=130220

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ለዓባይ ግድብ ግንባታ ላበረከተው አስተዋጽኦ እውቅና ተበረከተለት
************************
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ለዓባይ ግድብ ግንባታ ላደረገው አስተዋጽኦ "የላቀ ሙያዊ አስተዋጽኦ" በሚል ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ፅህፈት ቤት እውቅና ተበርክተለት።
የዓባይ ግድብ ግንባታ ቀሪ ሥራዎችን ለማጠናቀቅ መገናኛ ብዙኃን መረጃ የመስጠትና ህብረተሰቡን የማንቃት ሚናቸውን አጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባም የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት ጠይቋል።
በግድቡ የግንባታ ሂደት ተሳትፎ ያደረጉ የመገናኛ ብዙሃን በቀጣይ የግድቡ እንቅስቃሴዎች ተሳትፏቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ የጽህፈት ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አረጋዊ በርሄ አሳስበዋል።
የጽሕፈት ቤቱ የሕዝብ ግንኙትና የሚዲያ ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ኃይሉ አብርሐም፣ የመገናኛ ብዙሃን የግድቡ ግንባታ እስኪጠናቀቅ ከፍተኛ ርብርብ ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል።
የዓባይ ግድብ ከ13 ተርባኖች ውስጥ ሁለቱ ወደስራ መግባታቸውን አስታውሰው በቀጣይ አምስት ተርባይኖችን ወደ ስራ ለማስገባት እየተሰራ መሆኑንም አመላክተዋል።
ለግንባታው ከፍተኛ ሙያዊ አስተዋፅኦ ላበረከቱ መገናኛ ብዙሃን በየደረጃው የምስክር ወረቀት ተበርክቷል።
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=130225

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ያለሥልጣኑ የቅጣት ክፍያ ተመን መመሪያ በማዘጋጀት ገንዘብ ሲሰበስብ መቆየቱ ተገለጸ
በሀገሪቱ የንግድ ሕግ መሠረት ንግድ ፈቃድ ካላወጣ ድርጅት ጋር ሲሠራ መቆየቱም ተጠቅሷል
*********************
(ኢ ፕ ድ)
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ገንዘብ ለመሰብሰብ መመሪያ የማውጣት ሥልጣን ሳይኖረው የፓስፖርት ምዝገባ ቀነ ቀጠሮ ያሳለፉ ግለሰቦችን በቅጣት ለማስተናገድ የቅጣት ክፍያ ተመን መመሪያ አዘጋጅቶ በዋና ዳይሬክተር በማጸደቅ 18 ሚሊዮን ብር ገደማ መሰብሰቡን የፌዴራል ዋና ኦዲተር አጋለጠ፡፡
አገልግሎቱ የፓስፖርት ሥራ ለመሥራት በሀገሪቱ የንግድ ሕግ መሠረት ንግድ ፈቃድ ካላወጣ እና በታክስ ሕጉ መሠረት ግብር ከማይከፍል የግል ድርጅት ጋር ሲሠራ እንደነበርም ተጠቁሟል፡፡
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሶስተኛ ዓመት 32 መደበኛ ስብሰባ የፌዴራል ዋና ኦዲተር የ2015 ዓ.ም የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶች የፋይናንስና ሕጋዊነት ኦዲት እና የክዋኔ ኦዲት ሪፖርት አዳምጧል፡፡
ሪፖርቱን ያቀረቡት ዋና ኦዲተር ወይዘሮ መሠረት ዳምጤ፤ ተቋሙ ገንዘብ ለመሰብሰብ መመሪያ የማውጣት ሥልጣን ሳይኖረው የፓስፖርት ምዝገባ ቀነ ቀጠሮ ያሳለፉ ግለሰቦችን በቅጣት ለማስተናገድ የቅጣት ክፍያ ተመን መመሪያ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=130219