Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
40K photos
303 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ለዓባይ ግድብ ግንባታ ላበረከተው አስተዋጽኦ እውቅና ተበረከተለት
************************
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ለዓባይ ግድብ ግንባታ ላደረገው አስተዋጽኦ "የላቀ ሙያዊ አስተዋጽኦ" በሚል ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ፅህፈት ቤት እውቅና ተበርክተለት።

የዓባይ ግድብ ግንባታ ቀሪ ሥራዎችን ለማጠናቀቅ መገናኛ ብዙኃን መረጃ የመስጠትና ህብረተሰቡን የማንቃት ሚናቸውን አጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባም የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት ጠይቋል።

በግድቡ የግንባታ ሂደት ተሳትፎ ያደረጉ የመገናኛ ብዙሃን በቀጣይ የግድቡ እንቅስቃሴዎች ተሳትፏቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ የጽህፈት ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አረጋዊ በርሄ አሳስበዋል።

የጽሕፈት ቤቱ የሕዝብ ግንኙትና የሚዲያ ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ኃይሉ አብርሐም፣ የመገናኛ ብዙሃን የግድቡ ግንባታ እስኪጠናቀቅ ከፍተኛ ርብርብ ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል።

የዓባይ ግድብ ከ13 ተርባኖች ውስጥ ሁለቱ ወደስራ መግባታቸውን አስታውሰው በቀጣይ አምስት ተርባይኖችን ወደ ስራ ለማስገባት እየተሰራ መሆኑንም አመላክተዋል።

ለግንባታው ከፍተኛ ሙያዊ አስተዋፅኦ ላበረከቱ መገናኛ ብዙሃን በየደረጃው የምስክር ወረቀት ተበርክቷል።

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=130225
የገበታ ለሀገር አካል የሆነዉ #የወንጪ -ደንዲ ኢኮ ቱሪዝም መንደርና ሎጅ ‼️
#ገበታ_ለሀገር
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ያለሥልጣኑ የቅጣት ክፍያ ተመን መመሪያ በማዘጋጀት ገንዘብ ሲሰበስብ መቆየቱ ተገለጸ

በሀገሪቱ የንግድ ሕግ መሠረት ንግድ ፈቃድ ካላወጣ ድርጅት ጋር ሲሠራ መቆየቱም ተጠቅሷል
*********************
(ኢ ፕ ድ)
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ገንዘብ ለመሰብሰብ መመሪያ የማውጣት ሥልጣን ሳይኖረው የፓስፖርት ምዝገባ ቀነ ቀጠሮ ያሳለፉ ግለሰቦችን በቅጣት ለማስተናገድ የቅጣት ክፍያ ተመን መመሪያ አዘጋጅቶ በዋና ዳይሬክተር በማጸደቅ 18 ሚሊዮን ብር ገደማ መሰብሰቡን የፌዴራል ዋና ኦዲተር አጋለጠ፡፡

አገልግሎቱ የፓስፖርት ሥራ ለመሥራት በሀገሪቱ የንግድ ሕግ መሠረት ንግድ ፈቃድ ካላወጣ እና በታክስ ሕጉ መሠረት ግብር ከማይከፍል የግል ድርጅት ጋር ሲሠራ እንደነበርም ተጠቁሟል፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሶስተኛ ዓመት 32 መደበኛ ስብሰባ የፌዴራል ዋና ኦዲተር የ2015 ዓ.ም የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶች የፋይናንስና ሕጋዊነት ኦዲት እና የክዋኔ ኦዲት ሪፖርት አዳምጧል፡፡

ሪፖርቱን ያቀረቡት ዋና ኦዲተር ወይዘሮ መሠረት ዳምጤ፤ ተቋሙ ገንዘብ ለመሰብሰብ መመሪያ የማውጣት ሥልጣን ሳይኖረው የፓስፖርት ምዝገባ ቀነ ቀጠሮ ያሳለፉ ግለሰቦችን በቅጣት ለማስተናገድ የቅጣት ክፍያ ተመን መመሪያ....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=130219
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️