Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የገበታ ለሀገር አካል የሆነዉ #የወንጪ -ደንዲ ኢኮ ቱሪዝም መንደርና ሎጅ ‼️
#ገበታ_ለሀገር
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ያለሥልጣኑ የቅጣት ክፍያ ተመን መመሪያ በማዘጋጀት ገንዘብ ሲሰበስብ መቆየቱ ተገለጸ

በሀገሪቱ የንግድ ሕግ መሠረት ንግድ ፈቃድ ካላወጣ ድርጅት ጋር ሲሠራ መቆየቱም ተጠቅሷል
*********************
(ኢ ፕ ድ)
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ገንዘብ ለመሰብሰብ መመሪያ የማውጣት ሥልጣን ሳይኖረው የፓስፖርት ምዝገባ ቀነ ቀጠሮ ያሳለፉ ግለሰቦችን በቅጣት ለማስተናገድ የቅጣት ክፍያ ተመን መመሪያ አዘጋጅቶ በዋና ዳይሬክተር በማጸደቅ 18 ሚሊዮን ብር ገደማ መሰብሰቡን የፌዴራል ዋና ኦዲተር አጋለጠ፡፡

አገልግሎቱ የፓስፖርት ሥራ ለመሥራት በሀገሪቱ የንግድ ሕግ መሠረት ንግድ ፈቃድ ካላወጣ እና በታክስ ሕጉ መሠረት ግብር ከማይከፍል የግል ድርጅት ጋር ሲሠራ እንደነበርም ተጠቁሟል፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሶስተኛ ዓመት 32 መደበኛ ስብሰባ የፌዴራል ዋና ኦዲተር የ2015 ዓ.ም የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶች የፋይናንስና ሕጋዊነት ኦዲት እና የክዋኔ ኦዲት ሪፖርት አዳምጧል፡፡

ሪፖርቱን ያቀረቡት ዋና ኦዲተር ወይዘሮ መሠረት ዳምጤ፤ ተቋሙ ገንዘብ ለመሰብሰብ መመሪያ የማውጣት ሥልጣን ሳይኖረው የፓስፖርት ምዝገባ ቀነ ቀጠሮ ያሳለፉ ግለሰቦችን በቅጣት ለማስተናገድ የቅጣት ክፍያ ተመን መመሪያ....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=130219
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
በሁመራና አካባቢው የተቋረጠውን ኃይል መልሶ ለማገናኘት የሚያስችል ሥራ ተጀምሯል
*******
(ኢ ፕ ድ)

ከሽሬ- ሁመራ በተዘረጋው ባለ230 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ተሸካሚ የብረት ምሰሶ ላይ በደረሰ ተፈጥሯዊ አደጋ ኃይል መቋረጡን የሰሜን ምዕራብ ሪጅን የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች የኦፕሬሽንና ጥገና መምሪያ አስታወቀ።

የመምሪያው ዳይሬክተር አቶ ውበት አቤ እንዳስታወቁት የኃይል ተሸካሚ ምሰሶው የወደቀው ከሁመራ ከተማ 30 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው እንድሪያስ ቀበሌ ነው።

ሁመራ ከተማን ጨምሮ በዳንሻ፣ ባዕከር፣ አዲረመጥ፣ ሶረቃ፣ ማይካድራ፣ አብደራፊ፣ አብርሃጅራ፣ አዲጎሹ እና አደባይ እንዲሁም በሁሉም የገጠር ቀበሌዎች ከሰኔ 9 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡን ተናግረዋል።

የወደቀውን የኃይል ተሸካሚ ምሰሶ የቴክኒክ ቡድን ጥገና መጀመሩን የገለፁት ዳይሬክተሩ ጥገናውን ለማጠናቀቅ እስከ አስር ቀናት ሊፈጅ እንደሚችልም ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መረጃ ያመለክታል።

ሰኔ 12 ቀን 2016 ዓም
የአፍሪካ ሀገራት ብሔራዊ ቅጽል ስሞቻቸው‼️
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️