የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበለትን የ275 ሚሊዮን ዶላር የብድር ስምምነት አፀደቀ
**********************
(ኢ ፕ ድ)
በኢትዮጵያ እና በዓለም አቀፍ የልማት ማህበር መካከል ለሁለተኛው የከተሞች የመጠጥ ውሃ አቅርቦትና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የሚውል የ275 ሚሊዮን ዶላር የብድር ስምምነት አዋጅን በሙሉ ድምጽ አፅድቋል፡፡
ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው 3ኛ ዓመት 33ኛ መደበኛ ስብሰባው፤ በከተማ ውስጥ በሚገኝ መሬት፤ በመሬት ማሻሻያና በህንጻ ላይ የንብረት ታክስ እንዲሰበሰብ የሚያደርግ የንብረት ታክስ ረቂቅ አዋጅ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ተመራ፡፡
በከተሞች ውስጥ ከሚገኘው ሀብት ውስጥ እያደገ የመጣውን የመንግስት የወጪ ፍላጎት በተወሰነ ደረጃ ለመሸፈን የሚያስችል ሃብት ማሰባሰብ እንዲቻል ዘመናዊ የንብረት ታክስ ስርዓት መዘርጋት አስፈላጊ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
የምክር ቤት አባል አወቀ አምባዬ (ዶ/ር)፣ የጸደቀውን የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥርና አስተዳደር አዋጅን ጨምሮ ሰሞኑን እያጸደቅናቸው የሚገኙ አዋጆች ደሃው ህዝብ ላይ ጫና የሚፈጥሩ ናቸው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ህብረተሰቡ ችግር ውስጥ ባለበት ሁኔታ ተጨማሪ ክፍያ ማስከፈል አግባብነት የለውም ብለዋል፡፡
ጫናው የሚበረታው ደሃው ህብረተሰብ ላይ በመሆኑ ባግባቡ ሊታይ ይገባል ብለዋል፡፡
በረቂቅ አዋጁ ላይ ስጋት አለኝ ያሉት ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ህብረተሰቡ ቤት ለመስራት ከ15 እስከ 20 ዓመታት ከፍሎ ለመጨረስ የሚፈጅ እዳ ገብቶ ነው፡፡
ንብረት ለማፍራት ዕድሜ ልኩን ዕዳ ከሚከፍል ህዝብ ታክስ መሰብሰብ ይከብዳል ሲሉ አዋጁ ባግባቡ እንዲታይ ተጠይቀዋል፡፡
የአዋጁን አጭር መግለጫ ለምክር ቤት አባላት ያቀረቡት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር አቶ ተስፋዬ በልጅጌ፤ በአብዛኞቹ የአለም አገራት በከተማና በገጠር በሚገኝ መሬት ላይ ከጥንት ጊዜ ጀምሮ ‹‹የመሬት ታክስ›› በሚል ስያሜ ሲሰበሰብ መቆየቱን አስታውሰዋል፡፡
በኢትዮጵያም ከ1937 ዓ.ም ጀምሮ ከንብረት ላይ በተለያዩ መጠሪያዎች መጠነኛ ክፍያ በመሰብሰብ ላይ እንደሚገኝም ጠቁመዋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ረቂቅ አዋጅ እና የአካባቢና ማህበራዊ ተጽህኖ ግምገማ ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች መርቷል፡፡
በዘላለም ግዛው
ሰኔ 13 ቀን 2016 ዓም

በ224 ሚሊየን ብር ወጪ የተከናወነው የኤረር የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ሊመረቅ ነው
****
(ኢ ፕ ድ)
በሀረሪ ክልል በ224 ሚሊየን ብር ወጪ የተከናወነው የኤረር የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት በመጪው ቅዳሜ ይመረቃል።
ፕሮጀክቱ በአሁኑ ወቅት ወደ ከተማ ከሚገባው አጠቃላይ የውሃ መጠን በእጥፍ ይበልጣል ተብሏል። የህዝቡን የንፁህ መጠጥ ውሃ ችግርን በማቃለል ረገድ ፋይዳው የላቀ መሆኑ የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን መረጃ ያመለክታል።

ለዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ ሰባት ነጥብ ስድስት ቢሊዮን ችግኞች ተዘጋጅተዋል
**********************
(ኢ ፕ ድ)
ለ2016/17 የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር የአረንጓዴ አሻራ ሰባት ነጥብ ስድስት ቢሊዮን ችግኞች መዘጋጀታቸውን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በአንድ ጀንበር 150 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል ዕቅድ መያዙም ተመላክቷል፡፡
የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ኢያሱ ኤልያስ (ፕ/ር) ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ለ2016/17 የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በሀገር አቀፍ ደረጃ ስድስት ነጥብ አምስት ቢሊዮን ችግኞችን ለማዘጋጀት ታቅዶ ሰባት ነጥብ ስድስት ቢሊዮን ችግኞችን በማዘጋጀት ከእቅድ በላይ ማከናወን ተችሏል፡፡
አጠቃላይ ከተዘጋጁት ሰባት ነጥብ ስድስት ቢሊዮን ችግኞች መካከል 56 በመቶ የሚሆኑት ብዝሀ ጥቅም ያላቸው የፍራፍሬና የማገዶ ችግኞች ሲሆኑ፤ 44 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ የአካባቢ ጥበቃና የደን ሽፋንን የሚጨምሩ ችግኞች መሆናቸውን.......
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=130384

ቴክኒክና ሙያ – የኢኮኖሚ ዕድገት ሞተር
******************
(ኢ ፕ ድ)
ቴክኒክና ሙያ የአዕምሮና እጅ ጥበብ ውጤቶች የሚፈልቁበት ዘርፍ ነው፡፡
ይህን ዘርፍ የሀገርን ኢኮኖሚ በተገቢው ልክ እንዲደግፍ ለማስቻል የተለያዩ ጥረቶች ተደርገዋል፡፡
ዜጎችን በተለያየ መስክ የሙያ ባለቤት እና የፈጠራ ምንጭ ያደረገ የስልጠና ዘርፍ እንደመሆኑ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ የዕድገት ሞተር ለማድረግ የተሠሩ ሥራዎችን መዳሰስ ተገቢ ይሆናል፡፡
የቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር (ዶ/ር) የስልጠና ዘርፉ ለአንድ ሀገር ምጣኔ ሀብታዊ እድገት ወሳኝ ሚና የሚጫወት፤ ለኢንዱስትሪው መስክ ደግሞ ቀኝ እጅ ነው ይላሉ፡፡
ዘርፉ የሚያፈራው የሰው ኃይል ከኢንዱስትሪው ጋር ቀጥታ ግንኙነት እያለው እንኳን ይህን ሚናውን ያገናዘበ ትኩረት ሲሰጠው አልነበረም ባይ ናቸው፡፡
የመንግሥት ትኩረት በተለያዩ ጊዜያት እየተሻሻለ መምጣቱን የሚገልጹት ዳይሬክተሩ፤ በተለይ ከጣሊያን ወረራ ወዲህ ተግባረ ዕድ የቴክኒክ ትምህርት ቤት 1942 ላይ እንዲከፈት መደረጉን ይናገራሉ። ከትምህርት ቤቱ መቋቋም በኋላ ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=130385

❤1
ወደ ውጭ በሚላኩ የግብርና ምርቶች ላይ ዘመናዊ የቁጥጥርና ደህንነት ሥርዓት እየተገነባ ነው
***************
(ኢ ፕ ድ)
ወደ ውጭ በሚላኩ የግብርና ምርቶች ላይ ዘመናዊ የቁጥጥርና ደህንነት ሥርዓት እየተገነባ መሆኑን የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን አስታወቀ፡፡
በኢትዮጵያ ሆርቲካልቸር አምራችና ላኪዎች ማህበር እና በኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የተዘጋጀው የግብርና ውጤቶች ቁጥጥርና ደህንነት ላይ ያተኮረ ጉባኤ ትናንት ተካሂዷል፡፡
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ድሪባ ኩማ በወቅቱ ባደረጉት ንግግር፤ ባለስልጣኑ ወደ ውጪ የሚላኩና ከውጭ ወደ ሀገር ቤት የሚገቡ የግብርና ምርቶችን የደህንነትና ቁጥጥር አገልግሎት እንደሚሰጥ ገልጸዋል፡፡
እስካሁን የነበረው የአገልግሎት አሰጣጥ በአብዛኛው ወረቀት ላይ የተመሰረተ እንደሆነና አሁን ላይ አገልግሎቱን ወደ ዲጂታል ሥርዓት ለመቀየር ከአውሮፓ ኅብረትና ከትሬድ ማርክ አፍሪካ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=130447

የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ሳምንት በነገው ዕለት በኤግዚቢሽን ማዕከል ይከፈታል
*****
(ኢ ፕ ድ)
የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ሳምንት ነገ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል እንደሚከፈት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ አስታወቀ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ የውጤት ተኮር ሥልጠናና የተቋማት ልማት ዘርፍ ሀላፊ ዶክተር አበራ ብሩ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት:- የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ሳምንት የቴክኒክና ሙያ ለዘላቂ ልማት በሚል መሪ ሀሳብ ከሰኔ 15 እስከ 20 ይካሄዳል።
የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ሳምንት በነገው ዕለት በኤግዚቢሽን ማዕከል ይከፈታል ያሉት ዶክተር አበራ በከተማው የሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች;ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች:የሥራ ፈጠራ ባለቤቶች ወጣቶች ምርትና አገር በቀል ሥራዎች ለእይታ ይቀርባሉ ብለዋል።
ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ሳምንቱ ዓላማ በዘርፉ እየተሰሩ ያሉት ተግባራት ለህብረተሰቡ ለማስተዋወቅ የሚያስችል መሆኑን ጠቅሰው በተለይም በማህበረሰቡ ዘንድ በቴክኒክና ሙያ ያለውን ግንዛቤ ከፍ ለማድረግ በየዓመቱ የሚዘጋጅ መርሃግብር መሆኑን ገልጸዋል።
በመርሃግብሩ በርካታ ኮሌጆች ተሳታፊ እንደሚሆኑ በመግለጽ በተለይም ሁሉም የመግስት ኮሌጆች ያመረቷቸውን ምርቶችና ቴክኖሎጂዎች ይዘው የሚቀርቡበት አውደርዕይ መሆኑን ተናግረዋል።
የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ሳምንት ለ14 ጊዜ የሚከበር መሆኑን በመግለጽ በኮሌጆች መካከል የተለያዩ የችግር ፈቺ የቴክኖሎጂ ውድድርና እውቅና እንደሚካሄድ ተናግረዋል።
በተጨማሪም በጋርመንት ሥራዎች ላይ የፋሽን የስፖርት የቴክኖሎጂ ውድድር የተከናወነ መሆኑን ጠቅሰው ዘርፉ ወደ ተሻለ ደረጃ እንዲያድግ ድጋፍ ያደረጉ ተቋማት እውቅና እንደሚሰጥ አስረድተዋል።
ሰኔ 20 የማጠቃለያ መርሃግብር እንደሚካሄድ ገልጸው አውደርዕዩን ከ50 ሺህ በላይ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚጎበኙት ይጠበቃል ብለዋል።
በማርቆስ በላይ
ሰኔ 14 ቀን 2016 ዓም