Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.76K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ሳምንት በነገው ዕለት በኤግዚቢሽን ማዕከል ይከፈታል
*****
(ኢ ፕ ድ)
የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ሳምንት ነገ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል እንደሚከፈት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ አስታወቀ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ የውጤት ተኮር ሥልጠናና የተቋማት ልማት ዘርፍ ሀላፊ ዶክተር አበራ ብሩ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት:- የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ሳምንት የቴክኒክና ሙያ ለዘላቂ ልማት በሚል መሪ ሀሳብ ከሰኔ 15 እስከ 20 ይካሄዳል።

የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ሳምንት በነገው ዕለት በኤግዚቢሽን ማዕከል ይከፈታል ያሉት ዶክተር አበራ በከተማው የሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች;ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች:የሥራ ፈጠራ ባለቤቶች ወጣቶች ምርትና አገር በቀል ሥራዎች ለእይታ ይቀርባሉ ብለዋል።

ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ሳምንቱ ዓላማ በዘርፉ እየተሰሩ ያሉት ተግባራት ለህብረተሰቡ ለማስተዋወቅ የሚያስችል መሆኑን ጠቅሰው በተለይም በማህበረሰቡ ዘንድ በቴክኒክና ሙያ ያለውን ግንዛቤ ከፍ ለማድረግ በየዓመቱ የሚዘጋጅ መርሃግብር መሆኑን ገልጸዋል።

በመርሃግብሩ በርካታ ኮሌጆች ተሳታፊ እንደሚሆኑ በመግለጽ በተለይም ሁሉም የመግስት ኮሌጆች ያመረቷቸውን ምርቶችና ቴክኖሎጂዎች ይዘው የሚቀርቡበት አውደርዕይ መሆኑን ተናግረዋል።

የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ሳምንት ለ14 ጊዜ የሚከበር መሆኑን በመግለጽ በኮሌጆች መካከል የተለያዩ የችግር ፈቺ የቴክኖሎጂ ውድድርና እውቅና እንደሚካሄድ ተናግረዋል።

በተጨማሪም በጋርመንት ሥራዎች ላይ የፋሽን የስፖርት የቴክኖሎጂ ውድድር የተከናወነ መሆኑን ጠቅሰው ዘርፉ ወደ ተሻለ ደረጃ እንዲያድግ ድጋፍ ያደረጉ ተቋማት እውቅና እንደሚሰጥ አስረድተዋል።

ሰኔ 20 የማጠቃለያ መርሃግብር እንደሚካሄድ ገልጸው አውደርዕዩን ከ50 ሺህ በላይ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚጎበኙት ይጠበቃል ብለዋል።

በማርቆስ በላይ
ሰኔ 14 ቀን 2016 ዓም
በ10 ወራት በትምህርት ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶች‼️

👉በተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም 7 ነጥብ 88 ሚሊዮን ተማሪዎችን ተደራሽ ማድረግ ተችሏል፣

👉22 ነጥብ 7 ሚሊዮን የሁለተኛ ደረጃ መጽሐፍት ታትመዋል፣

👉ትምህርት ለትውልድ መርሐግብር 5 ሺህ 873 አዲስ ትምህርት ቤቶች ግንባታና 14 ሺህ 791 ትምህርት ቤቶች ጥገና ስራ ተከናዉኗል፣

👉የመውጫ ፈተና አተገባበር ሂደት ፈተናውን ከወሰዱ 97 ሺህ 673 ተማሪዎች ውስጥ 27 ሺህ 035 አልፈዋል፣

👉በ2016ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተናን በወረቀትና በኦንላይን መስጠት የሚቻልበት አቅም ተፈጥሯል፣

👉ከ136 የፌደራል ተቋማት ለ18 ሺህ 326 ሰራተኞች የትምህርት ማስረጃ ትክክለኛነት ተረጋግጧል፣

👉በትርክት ግንባታ የግብረ-ገብ ትምህርት በስርዓተ ትምህርቱ ውስጥ ተካቶ መሰጠት ጀምሯል፣

👉ለጎረቤት ሀገሮች የሚሰጡ የነጻ ትምህርት እድሎችን በማሳደግ በ2016 ዓም 865 ተማሪዎችን እየተማሩ ነው፣

ሰኔ 14 ቀን 2016 ዓም
አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከተ.መ.ድ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ፀሀፊ ጋር ተወያዩ
****************
(ኢ ፕ ድ)
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ፀሀፊ ክላቨር ጋቴትን ዛሬ በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ በመጪው ሀምሌ ወር የምታስተናግደው 4ኛዉ ፋይናንስ ለልማት ጉባዔ የቅድመ ዝግጅት ስብሰባ የተሳካ እንዲሆን ለማድረግ በጋራ መሰራት ባለባቸው ጉዳዮች ላይ ምክክር አድርገዋል፡፡

በቀጣይ መስከረም ወር በኒውዮርክ በሚካሄደው የመጭው ዘመን ስብሰባ (Summit of the Future) ላይ ሊኖሩ በሚገባቸው ተሳትፎዎች ዙሪያም የሀሳብ ልውውጥ አድርገዋል።

አፍሪካ አዳራሽ የተሰኘውን የኮሚሽኑ አዳራሽ የእድሳት ስራ በአዲስ አበባ እየተከናወነ ከሚገኘው የኮሪደር ልማትና ከተገነቡት የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎች ጋር በማስተሳሰር አዳራሹን አንድ የቱሪስት መስህብ ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይም ምክክር ተደርጓል።

ኮሚሽኑና ኢትዮጵያ በልማትና በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ተባብረው መስራት በሚችሉበት አግባብ ላይ መወያየታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

ሰኔ 14 ቀን 2016 ዓም
ኢትዮጵያ ላለፉት አምስት አመታት በ2011 ዓመተ ምህረት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተጠነሰሰው የአረንጓዴ ዓሻራ መርሃ ግብር አማካኝነት በየአመቱ የችግኝ ተከላ ስራ ስታካሂድ ቆይታለች። ዛሬ የባለፉት አመታት ጥረታችንን በማጤን የ2016ቱን ዙር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ቅድመ ጅማሮ መርሃ ግብር አካሂደናል።

በተካሄደውም የአረንጓዴ ዓሻራ ቅድመ መክፈቻ መርሃ ግብር ሁነት የኢትዮጵያ የደን ሽፋን ሪፖርት ይፋ ሆኗል። በመቀጠልም የሀገራዊውን የአረንጓዴ አሻራ ይዘት እና የስራ ውጤት በሰዋዊ ተረክ የሚያቀርብ አለምአቀፍ ዘጋቢ ፊልም የምረቃ እይታ ተካሂዷል።

ይፋ የተደረገው የኢትዮጵያ የደን ሽፋን ሪፖርት እንዳመለከተው የደን ሽፋናችን በ2011 ዓመተ ምህረት ከነበረበት 17.2 በመቶ ወደ 23.6 በመቶ ከፍ ብሏል። ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በመርሃ ግብሩ ባደረጉት ንግግር ይህን የዕድገት ውጤት ማስቀጠል እንደሚገባ ማሳሰባቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።

ሰኔ 14 ቀን 2016 ዓም
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መልዕክት‼️

በአረንጓዴ ዓሻራ ጥረቶቻችን አማካኝነት ልናሳካው ለምንፈልገው ለውጥ የአመለካከት እና የአዕምሮ ውቅር ሽግግር ያስፈልገናል። እንደ ሀገር ልናሳካ ካለምነው 50 ቢሊዮን ችግኞች በያዝነው አመት 40 ቢሊዮን ችግኞች ላይ ለመድረስ እየጣርን በመሆኑ በዘንድሮው የተከላ ዙር 7.5 ቢሊዮን ችግኞችን በጋራ መትከል ይኖርብናል። ለነገው ትውልድ ቅርስ ለመተው የሚሻ ሁሉ ዛሬ ላይ ማዋጣት የግድ ይለዋል።

ሰኔ 14 ቀን 2016 ዓም
የኦዲት ሪፖርትን መሠረት በማድረግ የተጠያቂነትአሠራር እንዲጠናከር ዋና ኦዲተሯ አሳሰቡ
*********************
(ኢ ፕ ድ)
የፌዴራል ዋና ኦዲተር በየዓመቱ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚያቀርበውን የፋይናንስና ሕጋዊነት ኦዲት እና የክዋኔ ኦዲት ሪፖርትን መሠረት በማድረግ ተጠያቂነትን በማስፈን የታዩ ጅምሮች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ዋና ኦዲተር ወይዘሮ መሠረት ዳምጤ ገለጹ፡፡

ዋና ኦዲተር ወይዘሮ መሠረት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡት የ2015/2016 ዓ.ም የኦዲት አፈጻጸም ሪፖርት ዙሪያ ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ፤ የሚመለከታቸው አካላት ተከታትለው ተጠያቂነትን ማስፈን አለባቸው ብለዋል፡፡

ግኝቶችን ለፓርላማ ከማቅረብ በተጨማሪም፤ ችግሮችን በመንቀስ ለጸረ ሙስና ኮሚሽን፣ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት፣ ለፍትህ ሚኒስቴር እንደሚሰጥና ተቋማቱ ለሚዲያ ያልተገለጹ ርምጃዎች እንደሚወስዱ ተናግረዋል፡፡

መሥሪያ ቤታቸው በሕግ የተሰጠው ሥልጣን የፋይናንስና ሕጋዊነት ኦዲት እና የክዋኔ ኦዲት ሪፖርት በመሥራት ለምክር ቤት ማቅረብ ነው ያሉት ሃላፊዋ፤ በ2013 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ በገንዘብ ሚኒስቴር አማካይነት ለ 38 ተቋማት አስተዳደራዊ ርምጃ መሰጠቱን.........

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=130454
በኦሮሚያ በ2016/2017 የምርት ዘመን ከ365 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ይጠበቃል
**************************
(ኢ ፕ ድ)
በ2016/2017 የበልግ እና የመኸር ግብርና የተለያዩ ሰብሎችን በመዝራት ከ365 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት እንደሚጠበቅ የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ።
ከዚህም ውስጥ 106 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የሚሆነው የስንዴ ምርት እንደሚሆን ተገልጿል።

በኦሮሚያ ግብርና ቢሮ ሰብል ምርት ልማት ዳይሬክተር አቶ ጠሃ ሁሴን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ክልሉ በ2016/2017 የተለያዩ ሰብሎችን በመዝራት በበልግ 28 ሚሊዮን ኩንታል፣ በመኸር 337 ኩንታል በድምሩ ከ365 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ እየሠራ ነው።
በሁለቱም ወቅቶች ከሚሰበሰበው ምርት 106 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የሚሆነው የስንዴ ምርት እንደሚሆንም ገልጸዋል።

እንደ እሳቸው ገለጻ፤ ክልሉ በዘንድሮ በልግ ብቻ 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በዘር ለመሸፈን አቅዶ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በዘር መሸፈን ችሏል።
የበልግ ወቅት ዝናብ አጀማመር ጥሩ በመሆኑ ለእርሻ መሬት ዝግጅት ምቹ ሁኔታዎች ተፈጥረዋል። ከዚህ አንጻር የዘንድሮ አፈጻጻም ከባለፈው ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነጻጸር በ200 ሺህ....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=130455
በጋምቤላ ክልል ከ612 ኪሎ ሜትር በላይ ርዝመት ያላቸው ዘጠኝ የመንገድ ፕሮጀክቶች በሥራ ላይ ናቸው
**************
(ኢ ፕ ድ)
በጋምቤላ ክልል ከ612 ኪሎ ሜትር በላይ ርዝመት ያላቸው ዘጠኝ የመንገድ ፕሮጀክቶች በሥራ ላይ መሆናቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አስታወቁ፡፡

ክልሉ ለብሄራዊ ባንክ የሚያቀርበው የወርቅ መጠን እየጨመረ መሆኑንም ርእሰ መስተዳድሩ አስታውቀዋል።

ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ በክልሉ የተገኙ ለውጦችን አስመልክቶ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡመድ ኡጁሉ እንደተናገሩት፤ ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ በኢኮኖሚና መሠረተ ልማት፣ በማህበራዊ ዘርፎች አበረታች ውጤቶች እየተመዘገቡ መሆኑን አስረድተዋል።

በተለይም ደግሞ በዐቢይ የኢኮኖሚ ምሰሶዎች ላይ የተሰጠው ትኩረት ፍሬያማ እንደነበር ጠቁመዋል።

ባለፉት ስድስት ዓመታት በክልሉ ከፍተኛ የሆነ የመሠረተ ልማት ሥራዎች መከናወናቸውንና የሕብረተሰቡ የመልማት ጥያቄዎች ምላሽ እያገኙ መሆኑን ጠቁመው፤ በአሁኑ ሰዓት በፌዴራል መንግሥት የተጀመሩ 612 ነጥብ 24 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያላቸው ዘጠኝ የመንገድ ፕሮጀክቶች በሥራ ላይ መሆናቸውን.....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=130456
ሁሉም አከራይ በ15 ቀናት ተከራያቸውን ይዘው በመምጣት የአከራይ ተከራይ ውል ስምምነት መፈጸም ይጠበቅባቸዋል
**************************
(ኢ ፕ ድ)
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ ወይዘሮ ቅድስት ወ/ ጊዮርጊስ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደገለፁት፤ በከተማው ግልፅና ፍትሀዊ በሆነ መንገድ አከራይና ተከራይን እኩል ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል።

ለዚህም ቢሮው የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥርና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1320/2016 እና መመሪያ ቁጥር 7/2016 ከመጋቢት 24 2016 ጀምሮ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል።

እንዲሁም በከተማው በ11 ክፍለከተሞችና በ120 ወረዳዎች ላይ የአከራይ ተከራይ የውል ስምምነት ከሰኔ 1 ጀምሮ እየተካሄደ ሲሆን እስከ ሰኔ 30 2016 የሚቆይ ይሆናል።

ውሉ ለሁለት አመታት ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን በነዚህ ጊዜያትም ተከራይ ማስወጣት ሆነ የቤት ኪራይ መጨመር የማይቻል መሆኑንም አስታውቀዋል።

ምዝገባውን በተሰጠው ጊዜ ሳይመዘገብ እስከ ሶስት ወራት የቆየ አከራይ የሁለት ወር ኪራይ እንዲሁም ከሶስት ወራት በላይ ካለፈ የሶስት ወር የቤት ኪራይ ቅጣት የሚቀጣ መሆኑም ተገልጿል።

እንዲሁም አዋጁ ከፀደቀበት መጋቢት 24 2016 ጀምሮ የሚደረግ ማንኛውም የቤት ኪራይ ዋጋ ጭማሪ የማይፈቀድ መሆኑን ገልፀዋል።

በመሆኑም በተቀመጠው ጊዜና መመሪያ መሰረት ሁሉም አከራይ ተከራይን ይዘው በመምጣት የአከራይ ተከራይ ውል ስምምነት መፈጸም እንዳለባቸው አስታውቀዋል።

በማህሌት ብዙነህ
ሰኔ 15 ቀን 2016 ዓም