"የምትተክል ሃገር፣ የሚያጸና ትውልድ!"
የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት ‼️
ዛሬ ማለዳ የ5ኛ ዙር አረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብርን በከተማችን ከሚገኙ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች፣ አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች፣ የዓለምአቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አትሌቶች፣ የተለያዩ ስፖርት ቤተሰቦች እንዲሁም ከከተማችን ነዋሪዎች ጋር በመሆን አስጀምረናል።
አረንጓዴና ውብ አካባቢን ለመፍጠር፣ በተፈጥሮ የበለጸገችና ከአየር ብክለት የፀዳች አዲስ አበባን ለትውልዱ ለማዉረስ ቃላችንን በተግባር መንዝረን ከነዋሪዎቻችን ጋር በመሆን ባለፉት የለውጥ ዓመታት ባደረግነው ርብርብ የከተማችንን አረንጓዴ ሽፋን ከነበረበት 2.8 በመቶ ወደ 17 በመቶ ከፍ ማድረግ ችለናል።
በኮሪደር ልማታችንም አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ አበባ ለማድረግ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞችን ስንተክል ከርመናል።
ባለፉት የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻዎቻችን የከተማችን ነዋሪዎች ፆታ፣ እድሜ፣ የፖለቲካ አመለካከት ልዩነት እንዲሁም ሃይማኖት ሳይገድባቸው የከተማዋን ተፈጥሯዊ ሚዛን መጠበቅ የሚችሉ ሀገር በቀል ዛፎችን፣ ለገፅታ ድምቀት የሚሆኑ የውበት እፅዋቶችን እንዲሁም የአትክልትና የፍራፍሬ ችግኞችን ተክለዋል።
ዘንድሮም በከተማችን 20 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ታሪክ ለመስራት የተዘጋጀን ሲሆን መላው የከተማችን ነዋሪዎች እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ በዚህ ታላቅ ሃገራዊ ጥሪ ላይ በመሳተፍ ለትውልድ የሚሆን አሻራችሁን እንድታኖሩ ጥሪ አቀርባለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ሰኔ 29 ቀን 2016 ዓም

በሀረሪ ክልል የዳያስፖራ አባላት የተሳተፉበት የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር ተጀምሯል
***
(ኢ ፕ ድ)
በሀረሪ ክልል የ2016 ዓም ክልል አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ መርሀግብር እየተካሄደ ነው። ዛሬ ከዳያስፖራው ማህበረሰብ ጋር 500 ሺህ ችግኞች ይተከላሉ።
የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በማስጀመሪያ መርሀ ግብሩ እንደተናገሩት፣ እንደ ሀገር የአየር ንብረት ለውጥና የአፈር መሸርሸር ፈተና ሆነው ቆይተዋል። ኢትዮጵያ ከነበራት 40 በመቶ የደን ሽፋን ወደ ሶስት በመቶ ወርዶ የነበረ ሲሆን፣ የለውጡ መንግስት በጀመረው የአረንጓዴ አሻራ የደን ሽፋኑን ወደ 26 ነጥብ ሰባት በመቶ ማሳደግ ተችሏል።
ይህ የንቅናቄ ስራ ጠንካራ የአመራር ቁርጠኝነትና የህዝብ ተሳትፎ የታየበት በመሆኑም እንደ ሀገር አበረታች ውጤት የተመዘገበበትና አለምም ያሞገሰው ነው ብለዋል። ይህ አበረታች ውጤት በክልል ደረጃም በተጨባጭ መታየቱንና ይህ በሌሎች ስራዎችም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።
በክልሉ በዘንድሮ አመት አጠቃላይ ሁለት ነጥብ አምስት ሚሊየን ችግኞች ይተከላሉ። በዛሬው እለት ደግሞ 500ሺህ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች ይተከላሉ።
በችግኝ ተካላ መርሀ ግብሩ የክልሉ ከፍተኛ አመራርን ጨምሮ ከተለያዩ አለማት የመጡ የክልሉ የዲያስፖራ አባላትና የተለያዩ የማህበረሰብ ከፍሎች እየተሳተፉ ነው።
በአዲሱ ገረመው (ሀረር)