Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.76K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በፓሪስ ኦሊምፒክ ጨዋታዎች ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶች‼️

በፓሪስ 2024 ኦሊምፒክ ጨዋታዎች በአትሌቲክስ ስፖርት ኢትዮጵያን የሚወክሉ የመጨረሻ ተሰላፊ አትሌቶች ከነተጠባባቂያቸው መለየታቸውን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

ማራቶን በሴቶችና በወንዶች
✍️ አትሌት ትዕግስት አሰፋ፣አትሌት አማኔ በሪሶ፣አትሌት መገርቱ ዓለሙ፣አትሌት ጎይቶቶም ገ/ስላሴ (ተጠባባቂ)

✍️ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ፣አትሌት ሲሳይ ለማ፣አትሌት ዴሬሳ ገለታ፣ አትሌት ታምራት ቶላ (ተጠባባቂ)

800 ሜትር በሴቶች

✍️ አትሌት ፅጌ ድጉማ፣አትሌት ሐብታም ዓለሙ፣አትሌት ወርቅነሽ መለሰ፣ አትሌት ንግስት ጌታቸው (ተጠባባቂ)

1500 ሜትር በወንዶችና በሴቶች

✍️ አትሌት አብዲሳ ፈይሳ፣አትሌት ሳሙኤል ተፈራ፣አትሌት ኤርሚያስ ግርማ፣አትሌት ታደሰ ለሚ (ተጠባባቂ)

✍️ አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ፣አትሌት ብርቄ ሃየሎም፣አትሌት ድርቤ ወልተጂ፣አትሌት ሂሩት መሸሻ (ተጠባባቂ)

5ሺህ ሜትር ወንዶችና በሴቶች

✍️አትሌት ሀጎስ ገ/ህይወት፣አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ፣አትሌት አዲሱ ይሁኔ፣አትሌት ሰሞን ባረጋ (ተጠባባቂ)

✍️ አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ፣አትሌት መዲና ኢሳ፣አትሌት እጅጋየሁ ታዬ፣አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ (ተጠባባቂ)

10ሺህ ሜትር ወንዶችና በሴቶች

✍️ አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ፣አትሌት በሪሁ አረጋዊ፣አትሌት ሰለሞን በረጋ፣አትሌት ቢኒያም መሀሪ (ተጠባባቂ)

✍️ አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ፣አትሌት ፎቴን ተስፋዬ፣አትሌት ፅጌ ገ/ሰላማ፣አትሌት አይናዲስ መብራቱ (ተጠባባቂ)

3ሺህ ሜትር መሠናክል በወንዶች
✍️ አትሌት ለሜቻ ግርማ፣አትሌት ሳሙኤል ፍሬው፣አትሌት ጌትነት ዋለ፣አትሌት አብርሃም ስሜ (ተጠባባቂ)

20 ኪሎ ሜትር ርምጃ በወንድ አትሌት ምስጋና ዋቁማ ናቸው።

ሰኔ 28 ቀን 2016 ዓም
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
በአርባምንጭ የመስክና ከተማ ጉብኝት እንዲሁም የ#አረንጓዴዓሻራ መርሐ ግብር በምስል‼️
"የምትተክል ሃገር፣ የሚያጸና ትውልድ!"

የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት ‼️

ዛሬ ማለዳ የ5ኛ ዙር አረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብርን በከተማችን ከሚገኙ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች፣ አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች፣ የዓለምአቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አትሌቶች፣ የተለያዩ ስፖርት ቤተሰቦች እንዲሁም ከከተማችን ነዋሪዎች ጋር በመሆን አስጀምረናል።

አረንጓዴና ውብ አካባቢን ለመፍጠር፣ በተፈጥሮ የበለጸገችና ከአየር ብክለት የፀዳች አዲስ አበባን ለትውልዱ ለማዉረስ ቃላችንን በተግባር መንዝረን ከነዋሪዎቻችን ጋር በመሆን ባለፉት የለውጥ ዓመታት ባደረግነው ርብርብ የከተማችንን አረንጓዴ ሽፋን ከነበረበት 2.8 በመቶ ወደ 17 በመቶ ከፍ ማድረግ ችለናል።

በኮሪደር ልማታችንም አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ አበባ ለማድረግ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞችን ስንተክል ከርመናል።

ባለፉት የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻዎቻችን የከተማችን ነዋሪዎች ፆታ፣ እድሜ፣ የፖለቲካ አመለካከት ልዩነት እንዲሁም ሃይማኖት ሳይገድባቸው የከተማዋን ተፈጥሯዊ ሚዛን መጠበቅ የሚችሉ ሀገር በቀል ዛፎችን፣ ለገፅታ ድምቀት የሚሆኑ የውበት እፅዋቶችን እንዲሁም የአትክልትና የፍራፍሬ ችግኞችን ተክለዋል።

ዘንድሮም በከተማችን 20 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ታሪክ ለመስራት የተዘጋጀን ሲሆን መላው የከተማችን ነዋሪዎች እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ በዚህ ታላቅ ሃገራዊ ጥሪ ላይ በመሳተፍ ለትውልድ የሚሆን አሻራችሁን እንድታኖሩ ጥሪ አቀርባለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

ሰኔ 29 ቀን 2016 ዓም