Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
40K photos
303 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ሀብት 1 ነጥብ 7 ትሪሊዮን ደርሷል
**********************
(ኢ ፕ ድ )
የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር የሚያስተዳድራቸው ተቋማት ሀብት 1 ነጥብ 7 ትሪሊዮን ብር መድረሱን አስታወቀ። በበጀት ዓመቱ ስምንት ቢሊዮን ብር ትርፍ ማስመዝገባቸውም ተነግሯል።

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ኃይለሚካኤል የተቋሙን ዓመታዊ አፈፃፀም አስመልክቶ እንደገለፁት፤ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሀብት በየጊዜው አጓጊ ለውጥ እያስመዘገበ ነው።

በዚህም የድርጅቶቹ ይዞታና አስተዳደር ሀብት 1 ነጥብ 7 ትሪሊዮን ደርሷል።

በኪሣራ ውስጥ የነበሩ ተቋማት ወደ ትፋማነት እየተቀየሩ እና ሀገራዊ ኃላፊነትን በአግባቡ እየተወጡ መሆኑን ጠቅሰው፤ ተቋማቱ ካገኙት ትርፍ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ገበታ ለሀገር ጨምሮ 604 ሚሊዮን ብር ወጪ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር የኦፕሬሽ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ትዕግስቱ አምሳሉ በበኩላቸው፤ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር የሀብት መጠን 1 ጥብ 7 ትሪሊዮን የደረሰ መሆኑን.......

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=131621
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
በ32 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ የባህር ዛፍ ተክል እንዲመነጠር ውሳኔ ተላለፈ
********************
(ኢ ፕ ድ)
በሲዳማ ክልል 32 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ የባህርዛፍ ተክል በሦስት ዓመት ውስጥ እንዲመጠነር ውሳኔ መተላለፉን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ገለጸ።

የቢሮው ኃላፊ አቶ መምሩ ሞኬ እንደገለጹት፤ ካለው የመሬት ጥበት አኳያ ለሰብል ልማት የሚውሉ የተለያዩ የመሬት አማራጮችን ተጠቅሞ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እየተሠራ ነው።

በዚህም ለግብርና ልማት መዋል የሚገባው 32 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ የባህርዛፍ ተክል በሦስት ዓመት ውስጥ ተመንጥሮ ለሰብል ልማት እንዲውል የክልሉ ምክር ቤት ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

አዋጅ ወጥቶ ወደ ምንጠራ ሥራም ተገብቷል ብለዋል።

በክልሉ ካለው የሕዝብ ጥግግትና የመሬት ሥሪት አኳያ ሰፊ ያልታረሰ ወይም ያልለማ መሬት የለም የሚሉት አቶ መምሩ፤ ያለውን የመሬት አማራጭ አሟጦ ለመጠቀምና አዳዲስ ለግብርና ልማት የሚውል መሬት ማግኘት የሚያስችል......

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=131607
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#ውብ_አዲስ‼️

አራት ኪሎ ተኳኩሎ፣ ቀበናም ጠረኑ ተቀይሮ፣ ፈካ ብሎ፣ ለህዝብ አገልግሎት ውሎ፣ በማየታችን ደስ ብሎናል"

እኛ ጥረናል፣ ፈጣሪ አከናውኖልናል!

- ከንቲባ አዳነች አቤቤ
#ኦሮሚያ

በኦሮሚያ ክልል በ2016 የበጀት ዓመት ዘርፈ ብዙ አገልግሎት የሚሰጡ ከ79 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው 20 ሺህ 664 ፕሮጀክቶች ለምረቃ ተዘጋጅተዋል።

መንግስት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ መሰረተ ልማቶችን የማስፋፋትና ተደራሽ የማድረግ ስራዎችን በተገባደደዉ የበጀት አመት ሰፊ ትኩረት ሰጥቶ ሲሰራ ቆይቷል።

ሐምሌ 1 ቀን 2016 ዓም
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት‼️

ኩታ ገጠም እርሻ እየተስፋፋ ነው። የዚህ ክረምት የእርሻ ዕቅዳችንን ሊያሳካ የሚችል ሰፊ እንቅስቃሴ ተጀምሯል። እንቅስቃሴውም መጠናከር አለበት። በዚህ ዓመት ከ24 ሚሊዮን ሄክታር በላይ ለማረስ ዕቅድ አለን። ይሄንን ዕቅድ ለማሳካት ከዝናቡ ጋር መሽቀዳደም አለብን። ኩታ ገጠም ማድረግ አለብን፤ ዘመናዊ መንገድ መከተልም አለብን። ይሄ ጥረት ነው በምግብ ራስን ለመቻል የምናደርገውን ጥረት የሚያሳካው።

ሐምሌ 1ቀን 2016 ዐም