Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
40K photos
303 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#ውብ_አዲስ‼️

አራት ኪሎ ተኳኩሎ፣ ቀበናም ጠረኑ ተቀይሮ፣ ፈካ ብሎ፣ ለህዝብ አገልግሎት ውሎ፣ በማየታችን ደስ ብሎናል"

እኛ ጥረናል፣ ፈጣሪ አከናውኖልናል!

- ከንቲባ አዳነች አቤቤ
#ኦሮሚያ

በኦሮሚያ ክልል በ2016 የበጀት ዓመት ዘርፈ ብዙ አገልግሎት የሚሰጡ ከ79 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው 20 ሺህ 664 ፕሮጀክቶች ለምረቃ ተዘጋጅተዋል።

መንግስት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ መሰረተ ልማቶችን የማስፋፋትና ተደራሽ የማድረግ ስራዎችን በተገባደደዉ የበጀት አመት ሰፊ ትኩረት ሰጥቶ ሲሰራ ቆይቷል።

ሐምሌ 1 ቀን 2016 ዓም
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት‼️

ኩታ ገጠም እርሻ እየተስፋፋ ነው። የዚህ ክረምት የእርሻ ዕቅዳችንን ሊያሳካ የሚችል ሰፊ እንቅስቃሴ ተጀምሯል። እንቅስቃሴውም መጠናከር አለበት። በዚህ ዓመት ከ24 ሚሊዮን ሄክታር በላይ ለማረስ ዕቅድ አለን። ይሄንን ዕቅድ ለማሳካት ከዝናቡ ጋር መሽቀዳደም አለብን። ኩታ ገጠም ማድረግ አለብን፤ ዘመናዊ መንገድ መከተልም አለብን። ይሄ ጥረት ነው በምግብ ራስን ለመቻል የምናደርገውን ጥረት የሚያሳካው።

ሐምሌ 1ቀን 2016 ዐም
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ውብ አዲስ አበባ!
አራት ኪሎ ኮከበፅባህ ቀበና
እነሆ ደረሰ ውበት እና ጤና

#PMOEthiopia
የሩሲያ የሳይንስና የባህል ማዕከል በሀገራቱ መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር እየሠራ ነው
****************
(ኢ ፕ ድ)
በአዲስ አበባ የሚገኘው የሩሲያ የሳይንስና የባህል ማዕከል በሩሲያና ኢትዮጵያ መካከል ያለውን የእርስ በእርስ ግንኙነት ለማጠናከር እየሠራ መሆኑን አስታወቀ፡፡

የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር አሌክሳንደር እቪሲትገንቪ ለኢፕድ እንደገለጹት፤ የሩሲያ የሳይንስና የባህል ማዕከል በዋናነት የተቋቋመው በሁለቱ ሀገራት መካከል በባህል፣ በቋንቋ፣ በትምህርትና በሌሎችም ዘርፎች ጠንካራ ግንኙነት እንዲኖረን ለማድረግ ነው።

በዚህም ማዕከሉ ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ በየወቅቱ የሀገራቱን ግንኙነት ወደተሻለ ደረጃ ከፍ ሊያደርጉ የሚችሉ ኮንሰርቶች፣ ኤግዚቢሽኖች፣ ሳይንሳዊ ኮንፈረንሶች፣ የሩስያ ቋንቋ ኮርሶችንና የተለያዩ ባህላዊና ትምህርታዊ ዝግጅቶችን ሲያከናውን ቆይቷል ብለዋል፡፡

ማዕከሉ በርካታ ኢትዮጵያውያን በሩሲያ የስኮላርሺፕ ፕሮግራም በማግኘት ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ምክንያት እየሆነ ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፤ ከዚህ ቀደም በሩሲያ ትምህርታቸውን ይከታተሉ የነበሩ ኢትዮጵያውያን......

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=131654
ሰው ሠራሽ አስተውሎት – የነገዋ ኢትዮጵያ አንዱ ተስፋ
**********************
(ኢ ፕ ድ)
አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ(የሰው ሠራሽ አስተውሎት) ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በሕይወታችን ውስጥ ያለው ወሳኝ ሚና እየጨመረ ይገኛል፡፡

የሶፍትዌር መሐንዲሶች እንደሚገልጹት የሰው ሠራሽ አስተውሎት ኮምፒዩተሮችና ማሽኖች እንደ ሰው ልጅ እንዲያመዛዝኑ፤ ነገሮችን እንዲገነዘቡ፤ ማንኛውንም ነገር እንዲማሩ፤ እንዲያቅዱና ፈጠራዎችን እንዲከውኑ በማድረግ የሚሰጣቸውን ተልዕኮ እንዲያሳኩ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ነው።

ቴክኖሎጂ የራሱ የሆነ አወንታዊና አሉታዊ ተጽዕኖዎች ቢኖሩትም አውንታዊ ጎኑን መረዳትና በአግባቡ መጠቀም ይገባል፡፡

ወጣት ቶማስ ወርቅነህ ይባላል፤ በምስራቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የአይ ሲቲ ትምህርት ክፍል የመጀመሪያ ዓመት ተማሪ ነው፡፡

ወጣቱን ያገኘነው በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል እየተካሄደ በሚገኘው 14ኛው ከተማ አቀፍ የቴክኒክና ሙያ ሳምንት ላይ የምስራቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅን........

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=131653