የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መልዕክት‼️
የወንድም ሱዳን ህዝብ ችግር የኛም ችግር ሰላማቸውም ሰላማችን በመሆኑ ለሱዳን ህዝብ እፎይታ እና የብልፅግና ጉዞ ዛሬም እንደ ትላንቱ ከልብ እንሰራለን።
ሐምሌ 2 ቀን 2016 ዓም

📌 ከተፈቀደ ቦታ ውጪ ቆሻሻ የጣሉ እስከ 100 ሺ ብር ተቀጡ
📌 በመንገድ አካፋይ ላይ ጉዳት ያደረሱ እስከ 300 ሺ ብር ተቀጠዋል
📌 ከተፈቀደው የእግረኞች መንገድ ውጪ የሄዱ እስከ 1000 ብር ተቀጡ
*****
(ኢ ፕ ድ)
በመዲናዋ በበርካቶች የቀን ከሌሊት ልፋት ውብ ተደርገው በተገነቡ መሰረተ ልማቶች ላይ ቆሻሻ የሚጥሉ፣ ከተፈቀደላቸው መንገድ ውጪ የሚሄዱ እንዲሁም ከተማዋን አረንጓዴ ለማድረግ በመንገድ አካፋዮች ላይ የተተከሉ ዛፎችን በግዴለሽነት በተሽከርካሪ በመግጨት ጉዳት ያደረሱ አካላት ተቀጡ።
በዚህም 3 ተቋማት ከተፈቀደ ቦታ ውጪ ቆሻሻ በመጣል እንደየጥፋት ደረጃቸው 100 ሺሕ ፣ 50 ሺ እና 20 ሺሕ ብር የተቀጡ ሲሆን 5 አሽከርካሪዎች በመንገድ አካፋይ ላይ ጉዳት በማድረሳቸው ከ150 እስከ 300 ሺሕ ብር እንዲሁም 11 ሰዎች ከተፈቀደው የእግረኞች መንገድ ውጪ በመሄዳቸው ከ150 እስከ 1000 ብር ተቀጥተዋል።
ነዋሪዎቻችን እነዚህ ደረጃቸውን ጠብቀው የተገነቡ መሰረተ ልማቶችን በተፈቀደው መንገድ ብቻ በመጠቀምና በመንከባከብ እራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ከቅጣትና ከትራፊክ አደጋ እንዲከላከሉ የከተማ አሰተዳደሩ ማሳሰቡን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።
ሐምሌ 3 ቀን 2016 ዓም

ቁጭት የወለደው የ’ገበታ ለትውልድ’ ፕሮጀክት
**************
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያ ከ ‘ገበታ ለሀገር’ ፕሮጀክቶች በተጨማሪ ስምንት የ ‘ገበታ ለትውልድ’ ፕሮጀክቶችን አስጀምራለች።
ፕሮጀክቶቹ የኢትዮጵያን ቱሪዝም እንቅስቃሴ በእጅጉ በማነቃቃት ዜጎችን ከዘርፉ ይበልጥ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መግለጻቸው የሚታወስ ነው።
በመንግሥት ደረጃ ልዩ ትኩረት ከተሰጣቸው ከነዚህ የቱሪዝም ልማት ፕሮጀክቶች መካከል ደግሞ በአርባ ምንጭ አካባቢ የሚገነባው ሰፊ የቱሪዝም ማዕከል ይገኝበታል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሮጀክቱን በጎበኙበት ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት በአርባ ምንጭ የተፈጥሮ ስጦታው ታላቅ ተስፋን የመጫሩን ያህል የአካባቢውን ምሉዕ አቅም ለመጠቀም የሠራነው ጥቂት በመሆኑ ደግሞ ያስቆጫል ሲሉ አመላክተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ይህ ቁጭት የወለደው የ ‘ገበታ ለትውልድ’ ፕሮጀክት ከአርባ ምንጭ አየር ማረፊያ በተሽከርካሪ ጉዞ የአምስት ደቂቃ ርቀት ላይ እንደሚገኝና በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እንዲሳተፉበት ጥሪ አቅርበዋል።
በዚህ “የምድር ገነት” ድርሻ በመግዛት ኢንቨስት ለማድረግ እድል ቀርቧል በማለት ነበር መልዕክት ያስተላለፉት።
በአካባቢው የተጀመረው ሁሉን አቀፍ ኢንቨስትመንት ለአካባቢው ብሎም ለሀገር ቱሪዝም ዘርፍ ዕድገት ምን ፋይዳ ይኖረዋል፤ ምንስ ተጨማሪ ጥረት ይጠይቃል፤ በሚሉ ጉዳዮች ላይ ምሁራን.....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=131707

የሕዝቦችን አንድነት ለማጽናት መገናኛ ብዙኃን የጋራ ትርክቶችን ማስተጋባት አለባቸው
***************************
(ኢ ፕ ድ)
የሕዝቦችን አንድነት ለማጽናት መገናኛ ብዙኃን የጋራ ትርክቶችን ማስተጋባት እንዳለባቸው በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የሚዲያና ማስታወቂያ ክትትል መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዴሬሳ ተረፈ አስታወቁ፡፡
በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የሚዲያና ማስታወቂያ ክትትል መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዴሬሳ ተረፈ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ መገናኛ ብዙኃን በአንድ ሀገር ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ከሕግና ከሞራል አንጻር ትልቅ ሚና አለባቸው፡፡
በተለይ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ዋናው የሚዲያዎች ኃላፊነት ነው፡፡ የሃሳብና የመረጃ ነጻነት ማረጋገጥ፣ መረጃ ላይ የተመሠረተ ውሳኔን የሚሰጥ ዜጋንና በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ንቁ ተሳትፎ የሚያደርግ ዜጋ ከመፍጠር ረገድ ሚዲያዎች ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡
እንደ መሪ ሥራ አስፈጻሚው ገለጻ፤ የሕዝቦች አብሮነትና አንድነት ለማጽናት መገናኛ ብዙኃን በተከታታይ መሥራት ይኖርባቸዋል፡፡
የሕዝቦችንና የሀገርን አንድነት ከማጽናት አንጻርና መግባባት ያልተደረሰባቸው ጉዳዮች ላይ መግባባት እንዲደረስ፣ የተናጠል ትርክቶችን ከማስተጋባት ይልቅ አሰባሳቢ ሃሳቦች ላይ ግንዛቤ መፍጠር ላይ ትልቅ ሚና እንዳላቸው አውቀው ሊሠሩ ይገባል፡፡
እንዲሁም ቁርሾና ቂምን ከመንዛት ይልቅ የወል ትርክቶች ላይ መሥራት......
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=131709

ለችግር የተጋለጡ 105 ሺህ 602 ስደተኞች ወደሀገራቸው ተመልሰዋል
***********************
(ኢ ፕ ድ)
ከጥቅምት 2016 ዓ.ም እስከ ሰኔ 10 ቀን 2016 ዓ.ም በተደረገ ርብርብ 105 ሺህ 602 ለችግር የተጋለጡ ስደተኞች ወደ ሀገራቸው እንዲገቡ ማድረግ መቻሉን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ በተያዘው ዓመት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከሳውዲ አረቢያ፣ ከሱዳን፣ ከየመንና ከኦማን 105 ሺህ 602 ለችግር የተጋለጡ ስደተኞች ወደሀገራቸው ተመልሰዋል።
ከመጋቢት 2014 እስከ መጋቢት 2015 ባለው ጊዜ ከሳውዲ አረቢያ ብቻ 133 ሺህ 103 ዜጎች በመንግሥት ድጋፍ ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን ያነሱት ሚኒስትሯ፤ መንግሥት ባለው ዜጋ ተኮር ፖሊሲ አማካኝነት ወደ ተለያዩ ሀገራት ሄደው ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ በቁርጠኝነት እየሠራ......
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=131724

ኢትዮ ቴሌኮም በ2016 በጀት ዓመት 93 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ገቢ አገኘ
******
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮ ቴሌኮም በተጠናቀቀው የ2016 በጀት ዓመት 93 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ የተቋሙን አፈጻጸም አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፤ ተቋሙ በተጠናቀቀው 2016 በጀት ዓመት 93 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን ገልጸዋል።
ገቢው ካለፈ በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ21 በመቶ ወይም 16 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ጭማሪ አሳይቷል። ገቢው ከእቅድ በላይ 103 ነጥብ 6 በመቶ ሆኗል። በዚህም 21 ነጥብ 79 ቢሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘትም ችሏል ብለዋል።
ከገቢው 39 ነጥብ 4 በመቶው ከድምጽ አገልግሎት የተገኘ መሆኑን ገልጸው፤ 27 ነጥብ 7 በመቶው ከዳታና ኢንተርኔት የተገኘ ነው። ገቢው ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ብልጫ እንዳለው ገልጸዋል።
የተቋሙ ደንበኞች ቁጥር 78 ነጥብ 3 ሚሊዮን መድረሱን ገልጸው፤ ከዚህ ውስጥ 75 ነጥብ 6 ሚሊዮኑ የሞባይል ድምጽ ተጠቃሚ ናቸው። የሞባይል ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ቁጥርም ም 40 ነጥብ 4 ሚሊዮን ደርሰዋል።
በዚህም የደንበኞች ቁጥርን ካለፈው ዓመት በ8 ነጥብ 9 በመቶ ከፍ ማድረግ መቻሉን ጠቁመዋል።
የቴሌብር ደንበኞት ቁጥርም 47 ነጥብ 55 ሚሊዮን መድረሱን የጠቆሙት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ፤ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ብቻ አንድ ነጥብ 81 ትሪሊዮን የኤሌክትሮኒክ ገንዘብ ዝውውር ተከናውኗል።
አገልገሎቱ ወደ ሥራ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ 2ነጥብ55 ትሪሊዮን የኤሌክትሮኒክ ገንዘብ ማንቀሳቀስ መቻሉንም ጠቁመዋል።
በፋንታነሽ ክንዴ

የኮምቦልቻ ከተማ ተለዋጭ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት‼️
በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን የኮምቦልቻ ከተማ ተለዋጭ መንገድ ከፌደራል መንግስት በተመደበ አንድ ቢሊዮን 168 ሚሊዮን ብር ወጪ ግንባታው እየተከናወነ ይገኛል።
የመንገዱ መገንባት ወደ ደረቅ ወደብ የሚገቡና የሚወጡ ከባድ ተሽከርካሪዎች ተለዋጭ መንገዱን ተጠቅመው ወደ መዳረሻቸው በፍጥነት እንዲደርሱ ያስችላል። ከተለያዩ አካባቢዎች የሚመጡ ተሸከርካሪዎች ወደ ከተማው መግባት ሳይጠበቅባቸው አቋርጠው ማለፍ እንደሚያስችል የኢትዮጵያ መንገዶች አሰተዳደር ገልጿል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሚዲያዎች የተዘጋጀውን የዕውቅና ሽልማት አበረከቱ
****
(ኢ ፕ ድ)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን ጨምሮ ለተለያዩ የሚዲያ ተቋማት የተዘጋጀውን የዕውቅና ሽልማቱን አበርክተዋል።
በመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የተዘጋጀው የሚዲያ ዕውቅና መርሐግብር በዓድዋ ሙዚየም ተካሂዷል።
በወቅቱ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ፣ የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክና አማራ ሚዲያ ኮርፖሬት ዕውቅና ከተሰጣቸው መካከል ይገኙበታል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያና ድሬ ቲዩብ ደግሞ በሌላ መድረክ ዕውቅና እንደሚሰጣቸው ተገልጿል።
በሽልማቱ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ሽልማት ውስጥ ባይካተቱም በተለይ የ “ኪንግ ኦፍ ዓባይ ሚዲያ” ባለቤትና የዓባይ ግድብ ተሟጋች ዑስታዝ ጀማል በሽር ለሚያከናውኑት ስራ ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።
ሚዲያዎች የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ባስከበረ መልኩ የኢትዮጵያን ልክ ሊያሳዩ ይገባል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በጌትነት ተስፉማሪያም