የኮምቦልቻ ከተማ ተለዋጭ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት‼️
በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን የኮምቦልቻ ከተማ ተለዋጭ መንገድ ከፌደራል መንግስት በተመደበ አንድ ቢሊዮን 168 ሚሊዮን ብር ወጪ ግንባታው እየተከናወነ ይገኛል።
የመንገዱ መገንባት ወደ ደረቅ ወደብ የሚገቡና የሚወጡ ከባድ ተሽከርካሪዎች ተለዋጭ መንገዱን ተጠቅመው ወደ መዳረሻቸው በፍጥነት እንዲደርሱ ያስችላል። ከተለያዩ አካባቢዎች የሚመጡ ተሸከርካሪዎች ወደ ከተማው መግባት ሳይጠበቅባቸው አቋርጠው ማለፍ እንደሚያስችል የኢትዮጵያ መንገዶች አሰተዳደር ገልጿል።
ሐምሌ 3 ቀን 2016 ዓም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሚዲያዎች የተዘጋጀውን የዕውቅና ሽልማት አበረከቱ
****
(ኢ ፕ ድ)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን ጨምሮ ለተለያዩ የሚዲያ ተቋማት የተዘጋጀውን የዕውቅና ሽልማቱን አበርክተዋል።
በመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የተዘጋጀው የሚዲያ ዕውቅና መርሐግብር በዓድዋ ሙዚየም ተካሂዷል።
በወቅቱ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ፣ የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክና አማራ ሚዲያ ኮርፖሬት ዕውቅና ከተሰጣቸው መካከል ይገኙበታል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያና ድሬ ቲዩብ ደግሞ በሌላ መድረክ ዕውቅና እንደሚሰጣቸው ተገልጿል።
በሽልማቱ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ሽልማት ውስጥ ባይካተቱም በተለይ የ “ኪንግ ኦፍ ዓባይ ሚዲያ” ባለቤትና የዓባይ ግድብ ተሟጋች ዑስታዝ ጀማል በሽር ለሚያከናውኑት ስራ ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።
ሚዲያዎች የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ባስከበረ መልኩ የኢትዮጵያን ልክ ሊያሳዩ ይገባል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በጌትነት ተስፉማሪያም

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መልዕክት‼️
ኢትዮጵያ ለሁለንተናዊ ጉዳዮች ጥንቃቄ የሚያስፈልግበት ወቅት ላይ ትገኛለች። በሚዲያ ሥራ ጥረቶቻችን የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም፣ ሰላም እና ፍቅር ቅድሚያ ሰጥተን መሥራት ይገባናል። ለቀጣዩ ትውልድ የሚሻገር ምን ጠቃሚ ሥራ እየሠራን ነው ብለን ራሳችንን ሳናሰልስ መጠየቅ አለብን። በዛሬው ዕለት ሀገራዊ ልማት እና ኅብረትን በማስተዋወቅ ብሎም ብሔራዊ ጥቅምን በማስጠበቅ ጥረት ረገድ ከፍ ያለ ሥራ በመሥራት ሽልማት ለተበረከተላቸው የሚዲያ ተቋማት እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እፈልጋለሁ።