Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሚዲያዎች የተዘጋጀውን የዕውቅና ሽልማት አበረከቱ
****
(ኢ ፕ ድ)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን ጨምሮ ለተለያዩ የሚዲያ ተቋማት የተዘጋጀውን የዕውቅና ሽልማቱን አበርክተዋል።

በመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የተዘጋጀው የሚዲያ ዕውቅና መርሐግብር በዓድዋ ሙዚየም ተካሂዷል።

በወቅቱ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ፣ የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክና አማራ ሚዲያ ኮርፖሬት ዕውቅና ከተሰጣቸው መካከል ይገኙበታል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያና ድሬ ቲዩብ ደግሞ በሌላ መድረክ ዕውቅና እንደሚሰጣቸው ተገልጿል።

በሽልማቱ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ሽልማት ውስጥ ባይካተቱም በተለይ የ “ኪንግ ኦፍ ዓባይ ሚዲያ” ባለቤትና የዓባይ ግድብ ተሟጋች ዑስታዝ ጀማል በሽር ለሚያከናውኑት ስራ ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።

ሚዲያዎች የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ባስከበረ መልኩ የኢትዮጵያን ልክ ሊያሳዩ ይገባል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በጌትነት ተስፉማሪያም

ሐምሌ 3 ቀን 2016 ዓም
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መልዕክት‼️

ኢትዮጵያ ለሁለንተናዊ ጉዳዮች ጥንቃቄ የሚያስፈልግበት ወቅት ላይ ትገኛለች። በሚዲያ ሥራ ጥረቶቻችን የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም፣ ሰላም እና ፍቅር ቅድሚያ ሰጥተን መሥራት ይገባናል። ለቀጣዩ ትውልድ የሚሻገር ምን ጠቃሚ ሥራ እየሠራን ነው ብለን ራሳችንን ሳናሰልስ መጠየቅ አለብን። በዛሬው ዕለት ሀገራዊ ልማት እና ኅብረትን በማስተዋወቅ ብሎም ብሔራዊ ጥቅምን በማስጠበቅ ጥረት ረገድ ከፍ ያለ ሥራ በመሥራት ሽልማት ለተበረከተላቸው የሚዲያ ተቋማት እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እፈልጋለሁ።

ሐምሌ 3 ቀን 2016 ዓም
በነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ተደረገ‼️

ከዛሬ ከሀምሌ 3 ቀን 2016 ዓም ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ ከአውሮፕላን ነዳጅ በስተቀር በቤንዚን፣ በኬሮሲን፣ በነጭ ናፍጣ፣ በቀላል ጥቁር ናፍጣና በከባድ ጥቁር ናፍጣ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ተደርጎል።

👉 ቤንዚን …… ብር 82.60 በሊትር

👉 ነጭ ናፍጣ…… ብር 83.74 በሊትር

👉 ኬሮሲን …. ብር 83.74 በሊትር

👉 የአውሮፕላን ነዳጅ…… ብር 70.83 በሊትር

👉 ቀላል ጥቁር ናፍጣ…… ብር 65.48 በሊትር

👉 ከባድ ጥቁር ናፍጣ ….ብር 64.22 በሊትር

የአለም ገበያ ላይ እየታየ ያለውን የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ መሠረት ከሀምሌ 3 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ሥራ ላይ የሚውለው የነዳጅ ውጤቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ማሰተካከያ መደረጉን የንግድና ቀጣናዊ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

ሐምሌ 3 ቀን 2016 ዓም
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ለአገር ግንባታ ላበረከተው አስተዋጾ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እጅ እውቅና ተቀብሏል።
#የምትተክል_ሀገር_የሚያፀና_ትውልድ‼️

የ#አረንጓዴዓሻራ የችግኝ ተከላ ወቅት ሥራችን ያስቀመጥነውን ግብ በሚያሳካ መልካም አጀማመር ላይ ይገኛል። የኅብረተሰባችንም የችግኝ ተከላ ተነሳሽነት ከፍተኛ ነው። ዛሬ በጫካ ፕሮጀክት ስፍራ የአፕል ችግኞችን ተክለናል። በአካባቢው የተደረገውን የዘንድሮውን ችግኝ ተከላ ለየት የሚያደርገው ቀድሞ የነበረው የባህርዛፍ ሽፋን ተወግዶ በሀገር በቀል የእርከን ሥራ እና ተክል የተተካ መሆኑ ነው። ከሀረር አካባቢ እና ከኮንሶ የመጡ ህዝቦቻችን አፈር እንዳይሸረሸር የሚያደርገውን ጊዜ የማይሽረውን ክህሎታቸውን አካፍለውናል። በከተሞች የምንሠራውን የአረንጓዴ አሻራ ጥረቶቻችንን በጋራ በማስፋፋት የአዲስ አበባን አረንጓዴ ሽፋን መጨመር እንችላለን።

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)