Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.76K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
እስከ ሦስት ዓመታት የሚጠብቁት የልብ ሕክምና ወረፋ
*****
(ኢ ፕ ድ)

ሕጻን ሐዋርያ ንጉሤ የአራት አመት ታዳጊ ሲሆን ከስድስት ወር እድሜው ጀምሮ የኢትዮጵያ የሕጻናት ልብ ሕክምና ማዕከል ተመላላሽ ታካሚ ሆኖ ቆይቷል፡፡

የሕጻን ሐዋርያ ንጉሤ ታላቅ እህት ገነት ንጉሤ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር ባደረገችው ቆይታ እንደተናገረችው ሐዋርያ በተወለደ በስድስት ወሩ ቤተሰቦቹ ልጃቸው የልብ ክፍተት ሕመም እንዳለበት ይነገራቸዋል፡፡ ይህ ቢያስደነግጣቸውም ነገሩን ይበልጥ ከባድ ያደረገባቸው ሕክምናው በሀገር ውስጥ እንደማይሰጥና ልጃቸው ወደ ውጭ ሄዶ መታከም እንዳለበት መስማታቸው ነበር፡፡

ልጃቸውን ወደ ውጭ ወስዶ ለማሳከም አቅማቸው የማይፈቅደው ቤተሰቦችም ይህንን ሕክምና በነፃ ይሰጣል ወደ ተባለው የኢትዮጵያ ልብ ሕሙማን ሕጻናት መርጃ ማዕከል ልጃቸውን ይዘው ያቀናሉ፡፡ በዚህ የሕክምና ማዕከልም ልጃቸው እየተመላለሰ ክትትል ማድረግ ቢጀምርም ወደ ውጭ ሀገር ሄዶ ለመታከም በርካታ ወረፋ በመኖሩ መጠበቅ ግድ ይላቸዋል፡፡

ወ/ሪት ገነት በማዕከሉ ወደ ውጭ ሄዶ ለመታከም ሕክምናውን የሚጠብቁ በርካታ ሕጻናት በመኖራቸው ሕጻን ሐዋርያ ወደ ውጭ ሄዶ ለመታከም ሦስት ዓመት ወረፋ መጠበቁን ተናግረዋል፡፡

ሐዋርያ ሕክምናውን ባላገኘባቸው ዓመታት ለመጫወት፣ እንዲሁም ምግብ ለመመገብ እጅግ ፈታኝ እንደነበር.....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=131922
የኢትዮጵያ የንግድ ሚዛን መዛባት ኢኮኖሚያዊ ፈተናዎች
*****
(ኢ ፕ ድ)

ኢትዮጵያ ከውጭ የምትቀበላቸው ምርቶች ከምትልካቸው ምርቶች የላቀ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ ይህ የሀገሪቷ ቀጣይነት ያለው የንግድ ሚዛን አለመመጣጠን ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ተግዳሮቶችን ሊፈጥር እንደሚችልም ይነሳል፡፡

በኢትዮጵያ የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት የምጣኔ ሀብት ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ጀማል መሐመድ (ዶ/ር) ስለ ሁኔታው እንደገለጹት፤ አወንታዊ ሚዛን (የንግድ ትርፍ) በመባል የሚታወቀው ሀገር ከምታስገባው

በላይ ወደ ውጭ ስትልክ ሲሆን፤ በተቃራኒው የንግድ ጉድለት በመባል የሚታወቀው አሉታዊ ሚዛን፣ ከውጭ የሚገቡ ምርቶች ወደ ውጭ ከሚላኩ ምርቶች ሲበልጡ ነው፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያ የንግድ ሚዛን ነባራዊ ሁኔታ አሉታዊ ሚዛን ላይ ይገኛል፡፡

እንደ ጀማል (ዶ/ር) ማብራሪያ፤ ባለፈው ዓመት የኢትዮጵያ የወጪ ንግድ ዋጋ ከ4 ቢሊዮን ዶላር በታች ሲሆን፣ ከውጭ የሚገቡት ምርቶች ግን ከ10 ቢሊዮን ዶላር በላይ በመሆናቸው.....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=131923
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ፖርቹጋላዊው ሉዊስ ናኒ እና ናይጄሪያዊው ንዋንኩ ካኑ አዲስ አበባ ገቡ
*****
(ኢ ፕ ድ)

ታዋቂዎቹ የእግር ኳስ ተጫዋቾች የፖርቹጋሉ ሉዊስ ናኒ እና ናይጄሪያዊው ንዋንኩ ካኑ ዛሬ ጠዋት አዲስ አበባ ገብተዋል

ሁለቱ ታዋቂ የእግር ኳስ ተጫዋቾች ወደ ኢትዮጵያ የመጡት የመቻል 80ኛ አመት የምስረታ በዓል ላይ ተካፋይ እንዲሆኑ በተደረገላቸው ግብዣ መሠረት ነው።

ተጫዋቾቹን የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ስለሺ ግርማ ፣የመቻል ስፖርት ክለብ ቦርድ ሰብሳቢ ሰይፈ ጌታሁን (ዶ/ር) እና የመከላከያ ሚዲያ ስራዎች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ብርጋዴር ጄኔራል ኩማ ሚደቅሳ አቀባበል አድርገውላቸዋል ሲል ኤፍቢሲ ዘግቧል።

ሐምሌ 6 ቀን 2016 ዓም