Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40.1K photos
306 videos
7 files
5.76K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ፖርቹጋላዊው ሉዊስ ናኒ እና ናይጄሪያዊው ንዋንኩ ካኑ አዲስ አበባ ገቡ
*****
(ኢ ፕ ድ)

ታዋቂዎቹ የእግር ኳስ ተጫዋቾች የፖርቹጋሉ ሉዊስ ናኒ እና ናይጄሪያዊው ንዋንኩ ካኑ ዛሬ ጠዋት አዲስ አበባ ገብተዋል

ሁለቱ ታዋቂ የእግር ኳስ ተጫዋቾች ወደ ኢትዮጵያ የመጡት የመቻል 80ኛ አመት የምስረታ በዓል ላይ ተካፋይ እንዲሆኑ በተደረገላቸው ግብዣ መሠረት ነው።

ተጫዋቾቹን የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ስለሺ ግርማ ፣የመቻል ስፖርት ክለብ ቦርድ ሰብሳቢ ሰይፈ ጌታሁን (ዶ/ር) እና የመከላከያ ሚዲያ ስራዎች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ብርጋዴር ጄኔራል ኩማ ሚደቅሳ አቀባበል አድርገውላቸዋል ሲል ኤፍቢሲ ዘግቧል።

ሐምሌ 6 ቀን 2016 ዓም