#ገበታ_ለሀገር_ፕሮጀክቶች ‼️
የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ “ገበታ ለሀገር” ውጥን እንደ ሀላላ ኬላ፣ ጨበራ ጩርጩራ፣ ወንጪ እና ጎርጎራ ያሉ የቱሪዝም መዳረሻዎችን በማልማት እና በአከባቢያቸው የሚገኙ ልዩ የተፈጥሮ ሀብቶችን አጉልተው በማሳየት ረገድ ከፍተኛ እመርታን አስመዝግቧል። እነዚህ ጥረቶች ለዘላቂነት እና ለአካባቢ ጥበቃ ቅድሚያ በመሰጠት ቱሪዝምን ለማሳደግ፣ ስራ ለመፍጠር እና በዙሪያው የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎችን የኑሮ ደረጃ ለማሳደግ ያለሙ ናቸው።
ቱሪዝም በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ገቢ በማስገኘት እና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ስራዎችን በመደገፍ በአለም ኢኮኖሚ ውስጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። ለጠቅላላ አገራዊ ምርት (GDP) በሚያደርገው ቀጥተኛ አስተዋፅኦም በጎ የሆነው ኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖው በጉልህ ይታያል።
በአገራችን ኢትዮጵያም ቱሪዝም መንግስት ላስጀመረው የአገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም የማዕዘን ድንጋይ ሲሆን ከአምስቱ ቁልፍ ምሰሶዎች አንዱ ነው። እንደ “ገበታ ለሀገር” ያሉ ሥራዎች የቱሪዝም ዘርፉን ለማዳበር፣ ብዙ ጎብኝዎችን ለመሳብ፣ የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማነቃቃት፣ የስራ እድሎችን ለመፍጠር፤ መዳረሻዎችን ለማልማት እና ለማሻሻል ታልመው በስራ ላይ በመዋል ላይ ይገኛሉ።
የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት ምረቃ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አራት አለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ መዳረሻዎችን በ “ገበታ ለሀገር” ውጥን ስር ለማልማት ያሳዩት ቁርጠኝነት ተጨማሪ ማሳያ ሲሆን በ2012 ቃል በገቡት መሰረት ገንብተው ማስረከባቸውንም ያመላክታል።
በአሁኑ ወቅት ደግሞ ርዕያቸው ተስፋፍቶ በግንባታ ላይ ያሉ ሰባት ተጨማሪ መዳረሻዎችን ለማልማት ያቀደ “ገበታ ለትውልድ” የተሰኘ አዲስ ፕሮጀክትም አስጀምረዋል።
ሐምሌ 10 ቀን 2016 ዓም

የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ጉሮሮ
************
(ኢ ፕ ድ)
ቀይ ባሕር እና የኤደን ባሕረሰላጤ ለዓለም የንግድ እንቅስቃሴ ወሳኝ መስመሮች ናቸው፡፡
በዚህ መስመር በዓመት ከ30 እስከ 50 ሺህ መርከቦች እንደሚተላለፉ መረጃዎች ይጠቁማሉ፤ እንዲሁም ከ700 ቢሊዮን ዶላር በላይ የንግድ እንቅስቃሴን ያስተናግዳል፡፡
ይሁንና አሁን ላይ የንግድ እንቅስቃሴው መቀነሱ እየተነገረ ነው፡፡ ሊቀንስ የቻለውም በቀጣናው የሐውቲ አማፅያን መጨመርና በርካታ የባሕር ላይ ወንበዴዎች መበራከታቸው ዋነኛ ምክንያት እንደሆነ ይነገራል፡፡
የሐውቲ አማፅያን ከቀን ወደ ቀን በንግድ መርከቦች ላይ የሚፈጽሙት ጥቃት በመጨመሩ የዓለም የንግድ እንቅስቃሴ ላይ ተፅዕኖ እያሳደረ መሆኑ ይነገራል።
የቅርብ ጊዜ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት አማፅያኑ በሚፈጽሙት ጥቃት የአካባቢው የንግድና የጂኦፖለቲካ እንቅስቃሴ ትልቅ ተግዳሮት እየገጠመው ነው።
ኢትዮጵያ ለቀይ ባሕር በቅርበት የምትገኝ ሀገር በመሆኗም የውጭ ገቢ ንግዷ ከዚህ መስመር ጋር በቀጥታ የሚገናኝ በመሆኑ በአካባቢው የሚከሰቱ ጉዳዮች ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሞች ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አላቸው።
የአካባቢውን የጂኦፖለቲካ ስትራቴጂ አስፈላጊነት የተገነዘቡት ኃያላን ሀገራት በአካባቢው የጦር ሰፈር ገንብተዋል፤ አሁንም በሩጫ ላይ ያሉት በርካቶች ናቸው።
እ.ኤ.አ በ2017 ቻይና ከሀገሯ ውጭ ለመጀመሪያ ጊዜ በጅቡቲ የወታደራዊ ማዘዣ ጣቢያ አቋቁማለች። መሰል ችግሮችን በራስ አቅም ለመከላከል የባሕር በር አስፈላጊነት......
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=132188

👍1
"ደቡብ ሱዳን የናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነትን ማጽደቋ ለኢትዮጵያ ታሪካዊ ነው"
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
***************
(ኢ.ፕ.ድ)
ደቡብ ሱዳን የናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነትን ማጽደቋ ለኢትዮጵያ ታሪካዊ ነው ሲሉ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታወቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው ላይ ዛሬ ማለዳ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ደቡብ ሱዳን ስምምነቱን ተቀብላ ማጽደቋ ለኢትዮጵያ ብሎም ለአካባቢው አገራት ትልቅ ጠቀሜታ አለው።
እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጻ፤ ይህ ዲፕሎማሲያዊ እመርታ በተፋሰሱ አገራት መካከል ቀጣናዊ ትብብርን ለማሳደግ ላለው ፍላጎት ጉልህ እርምጃ ነው።
"የደቡብ ሱዳን ስምምነቱን ተቀብላ ማፅደቅ የናይል ተፋሰስ ኮሚሽንን በማቋቋም የህዝባችንን የጋራ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ መነቃቃትን ይፈጥራል" ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ መልዕክታቸው።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤቱ ባቀረቡት ሪፓርት ‼️
👉በተጠናቀቀው 2016 በጀት ዓመት 146 ነጥብ 84 ቢሊዮን ብር ገቢ ተሰብስቧል
👉ከ291 ሺህ በላይ ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል ተፈጥሯል
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 3ተኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ እና የበጀት ዓመቱ ማጠቃለያ ጉባኤውን እያካሄደ ይገኛል።
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ሪፓርት እንደገለጹት፤ በበጀት ዓመቱ 151 ነጥብ 68 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 146 ነጥብ 84 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ ተችሏል።
አፈፃፀሙ ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ44 ነጥብ 16 ዕድገት አሳይቷል ብለዋል።
በ2016 በጀት ዓመት ለ291 ሺህ 577 ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል ተፈጥሯል።
በበጀት ዓመቱ ለ300 ሺህ ሥራ ፈላጊዎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ እንደነበር ጠቅሰው ለ291 ሺህ 577 ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል የተፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል።
የሥራ እድል የተፈጠረባቸው ዘርፎች የከተማ ግብርና 9 በመቶ፣ ማኑፋክቸሪንግ 17 ነጥብ 5 በመቶ፣ ኮንስትራክሽን 5 በመቶ፣ ንግድ 19 በመቶ እና አገልግሎት ዘርፍ 49.3 በመቶ ድርሻ እንዳላቸውም ተናግረዋል።
የገቢ አሰባሰብ ንቅናቄ በመፍጠርና ጠንካራ የክትትል ሥርዓት በመዘርጋት የከተማውን የወጪ ፍላጎት ለመሸፈን መሰራቱን ጠቅሰው ዝቅተኛ ገቢ ያለውን ነዋሪ መደጎም የሚያስችል ገቢ በማሰባሰብ የከተማችንን ገቢ ከማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
ምክር ቤቱ የከተማ አስተዳደሩን የ2016 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፓርት ያዳመጠ ሲሆን በቀጣይ የከተማውን ዋና ኦዲተር ሪፓርትን ጨምሮ የተለያዪ ሹመቶችንም ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
በማርቆስ በላይ

"የዋቢ ሸበሌ ወንዝ ውሃን በማጣራት ለመጠጥ ብቁ የሚያደርገውን የጎዴ ከተማ ፕሮጀክትን ዛሬ አይተናል፡፡ በሸበሌ ወንዝ ዙሪያ እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎች የጎዴ ከተማ ዕድገትን እያፋጠኑት ይገኛል"
- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ባቀረቡት ሪፓርት ካነሷቸው ዋና ዋና ሀሳቦች‼️
👉 ለ291 ሺህ 577 ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል ተፈጥሯል፣
👉ለ7 ሺህ 539 ኢንተርፕራይዞችን 2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር የብድር አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፣
👉 5 ነጥብ 17 ሚሊዮን ቶን ምርት በማምረት አንድ ነጥብ 84 ቢሊዮን ዶላር የውጪ ምንዛሪ ማዳን ተችሏል፣
👉 351 ሺህ 549 የንግድ ሥራ ፈቃድ ዕድሳት አገልግሎት ለመስጠት ታቅዶ 330 ሺህ 419 ማከናወን ተችሏል፣
👉 በገበያ ማዕከላት የሰብል፣ የአትክልትና ፍራፍሬ አቅርቦት ላይ በገበያ ካለው ዋጋ ከ15-20 በመቶ ቀንሷል፣
👉አምራችና ሸማቹ በቀጥታ ግብይት የሚፈፅሙባቸው ቅዳሜና እሁድ የገበያ ቦታዎች 193 ደርሰዋል፣
👉በኅብረት ሥራ ማኅበራት በኦዲት ከተገኙ ጉድለቶች ከ78 ሚሊዮን ብር በላይ ተመላሽ ማድረግ ተችሏል፣
👉 የወንጀል ምጣኔ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር እየቀነሰ መጥቷል፣
👉 17 ሺህ 635 ቤቶች ተገንብተው ለልማት ተነሺዎችና ለሌሎች ተጠቃሚዎች ተላልፈዋል፣
👉 በጋራ መኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበር 4 ሺህ 940 ነዋሪዎች በ60 ማህበራት እንዲደራጁ ተደርጓል፣
👉 ከእነዚህ መካከል 54 ማኅበራት ቦታ ተረክበው ሥራ ጀምረዋል፣
👉 የመንገድ ግንባታ ሽፋንን ለማሳደግ 40 ነጥብ 80 ኪሜ አስፋልት መንገድ ግንባታ ማከናወን ተችሏል፣
👉20 ሺህ 595 የመንገድ መብራት መስመርና ፖል ጥገና፣ የመንገድ መብራት አምፖል የቅየራ ሥራ ተከናውኗል፣
👉ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ኅብረተሰብ ክፍሎች ማዕድ ማጋራት ተችሏል፣
👉 በሰው ተኮርና በጎ ፈቃድ አገልግሎት በ12 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር የከተማዋን ነዋሪዎች ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፣
👉 በመንግስትና በግል አጋርነት የቤት ልማት ፕሮግራም 65 ሺህ 817 ቤቶች ግንባታቸው ተጀምሯል፣
👉 የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቅበላን ከ291 ሺህ 392 ወደ 316 ሺህ 931 መፈፀም ተችሏል፣
👉 የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቅበላ ከነበረበት 598 ሺህ 051 ወደ 626 ሺህ 647 ማድረስ ተችሏል፣
👉 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት (9-12ኛ) ቅበላን ከ223 ሺህ 302 ወደ 232 ሺህ 030 ማድረስ ተችሏል፣
👉 የትምህርት ቅበላ ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ62 ሺህ 823 ተማሪዎች ዕድገት አሳይቷል፣
👉 በሁሉም ት/ቤቶች የልዩ ፍላጎት ትምህርትን በማስፋፋት የተማሪዎችን ቁጥር 39 ሺህ 640 ማድረስ ተቸሏል፣
👉 በ“ትምህርት ለትውልድ” ንቅናቄ ከ6 ነጥብ 44 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት ሀብት ማሰባሰብ ተችሏል፣
👉 በፍትሐ-ብሔር ጉዳዮች በፍርድ ቤት ክርክር ከተደረገባቸው 8ሺህ 514 መዝገቦች ውሳኔ ያገኙት 5ሺህ 352 ናቸው፣ በገንዘብ ሲተመን ከ5 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ፣ በዓይነት 257 ቤቶችና 1 የንግድ ሕንጻ፣ 1015 ኮንዶሚኒየም ቤቶች፣ 746 ሼዶች እንዲሁም 1152 ሄክታር መሬት) በመርታት የሕዝቡን ሀብት ከምዝበራ መታደግ ተችሏል፣