ሁለት ትውልድ- አንድ ተልዕኮ
**********
(ኢ.ፕ.ድ)
...አቶ ቶማስ ኃይሌ እና ልጁ ሊዲያ ኃይሌን የሰውና የመኪና ትራፊክ ፍሰት በእጅጉ ከሚበዛባቸው ሥፍራዎች አንዱ በሆነው ፒያሳ እግረኞችን በመንገደኛ ማቋረጫ ለማሻገር ከሰዓት ከአሥር ሰዓት እስከ ምሽቱ አንድ ሰዓት ድረስ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሲሰጡ አይተናቸዋል።
አቶ ቶማስ ኃይሌ ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን የሚያስተዳድሩት በንግድ ሥራ ነው። በሚሠሩት ሥራ ገቢ ለማግኘት የግዴታ በሥራ ቦታቸው ላይ መገኘት እንዳለባቸው ተናግረዋል።
“በክረምት ለአንድ ሰዓትና ለሁለት ሰዓት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራ እሠራለሁ።” ይላሉ አቶ ቶማስ።
በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ መሰማራት የጀመርኩት..
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=132643

በስልጤ ዞን ከ15 ሺህ ሔክታር በላይ መሬት ላይ ፍራፍሬ ለምቷል
*********
(ኢ.ፕ.ድ)
በስልጤ ዞን ከ15 ሺህ ሔክታር በላይ መሬት ላይ የተለያዩ ፍራፍሬዎች መልማታቸውን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ።
የስልጤ ዞን ግብርና መምሪያ ኃላፊ ሙርሰል አማን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በዞኑ ከፍተኛ የሆነ ፍራፍሬ ማምረት የሚያስችል አቅም አለ። በ2016 ዓ.ም ከ15 ሺህ 726 ሔክታር መሬት ላይ የተለያዩ ፍራፍሬዎች ለምተዋል።
በዞኑ ፍራፍሬን ለማምረት የሚያመች የተፈጥሮ ሀብት ቢኖርም ምቹ ሁኔታውን በስፋት የመጠቀም ልምዱ አነስተኛ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=132634

የዓለም አቀፉ የፋይናንስ ለልማት ጉባኤ ቅድመ ዝግጅት ስብሰባ ዛሬ መካሄድ ይጀምራል
*********
(ኢ.ፕ.ድ)
ኢትዮጵያ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጋር በመተባበር የዓለም አቀፉን የፋይናንስ ለልማት ጉባኤ ቅድመ ዝግጅት ስብሰባ ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ አምስት ቀናት ታሥተናግዳለች።
ኢትዮጵያ ከዘጠኝ ዓመት በፊት ሦስተኛውን የፋይናንስ ለልማት ጉባኤ ማስተናገዷ ይታወሳል።
ጉባኤው ለዘላቂ ልማት ግቦች አጀንዳ ማስፈጸሚያ ገንዘብ ለማሰባሰብ ጠቀሜታ እንዳለው ተገልጿል።
የአዲስ አበባው ጉባኤ በቀጣይ ዓመት በስፔን ለሚካሄደው አራተኛው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ለልማት ጉባዔ አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል።
በጉባኤው የአዲስ አበባ የድርጊት መርሃ ግብርን አፈፃፀም የሚገመገም ሲሆን፤ የሀገራት ተወካዮች፣የአለም አቀፍ ተቋማት ሃላፊዎችና የዘርፉ ባለሙያዎች ተገኝተውል።
ሞገስ ጸጋዬ
ሐምሌ 15 ቀን 2016 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሲሞንፒየትሮ ሳሊኒ ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሐዘን ገለፁ
***********
(ኢ.ፕ.ድ)
የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሲሞንፒየትሮ ሳሊኒ ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ልባዊ ጥልቅ ሐዘን ገለፁ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ሲሞንፒየትሮ ሳሊኒ በለገዳዲ ግድብ ፣በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኩላሊት ላይብረሪ፣ በጣና በለስ ፕሮጀክት፣ በግልገል ጊቤ ቁጥር 1፣ 2 እና 3 እንዲሁም ለህዳሴው ግድብ ግንባታ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ገልጸዋል።
ሳሊኒ ለኢትዮጵያ የነበራቸው ፍቅር በተግባር የተገለጠ እንደሆነ ጠቅሰው፥ በሀገር ግንባታ ሂደት የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን ማከናወናቸውን ገልጸዋል። ሥራዎቻቸውም በልጃቸው ፒየትሮ ሳሊኒ የቀጠለ መሆኑንም ጠቁመዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ መልዕክታቸው፤ለሲሞንፒየትሮ ሳሊኒ ቤተሰብና ለመላው ዊቢውልድ ግሩፕ መጽናናትን ተመኝተዋል።
በሙሳ መሀመድ
ሐምሌ 15/2016ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ የተገነባው የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል
**************
(ኢ.ፕ.ድ)
የጨፌ ኦሮሚያ 6ኛ የስራ ዘመን 3ኛ ዓመት 7ኛ መደበኛ ጉባዔ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ገዛሊ አባሲመል ለጨፌ ኦሮሚያ ባቀረቡት ሪፓርት እንደገለጹት፤ በአዲስ አበባ ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።
ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ G+13 እና ባለሁለት የምድር ቤት ህንጻ መሆኑን ጠቅሰው፤ በአጭር ጊዜ ጥራቱን በጠበቀ መልኩ ተገንብቶ ለአገልግሎት መብቃቱን ገልጸዋል።
ፕሮጀክቱ ያረፈበትን አከባቢ ጽዱና ውብ ለማድረግ የማስፋፊያ መሬት ከከተማ አስተዳደሩ መፈቀዱን በመግለጽ አካባቢውን የማስዋብ ስራ መሰራቱንም ተናግረዋል።
በማርቆስ በላይ (አዳማ)

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት !
በሚያዚያ ወር ከፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች ጋር በመገናኘት በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገን ነበር። በወቅቱም በየደረጃው ውይይቶች እንዲቀጥሉ አቅጣጫ ተቀምጦ ነበር። ዛሬ የሚያዚያው ውይይታችን ቀጣይ የሆነና ሁሉን አቀፍ ጠቀሜታ ባላቸው ሀገራዊ ጉዳዮች መግባባት መፍጠርን የተመለከተ ውይይት አድርገናል።

በአፋር ክልል ከ4 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ
****
(ኢ.ፕ.ድ)
በአፋር ክልል በ2016 የበጀት አመት ከ4 ቢሊዮን 228 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የክልሉ ገቢዎች ቢሮ አስታውቋል::
የአፋር ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ አቶ አወል አብዱ እንዳስታወቁት፤ በክልሉ በ2016 የበጀት አመት 5 ቢሊዮን 264 ሚሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ 4 ቢሊዮን 228 ሚሊዮን ብር ተሰብስቧል።ይህም የእቅዱ አፈፃፀም 80 በመቶ ነው::
አቶ አወል አክለውም ገቢው የተሰበሰበው ከቀጥታ ታክስ፣ ቀጥታ ካልሆነ ታክስ፣ ታክስ ነክ ካልሆነ እንዲሁም ከማዘጋጃ ቤታዊ ገቢዎች መሆኑን ተናግረዋል::
በክልሉ ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ አሟጦ በመሰብሰብ የህብረተሰቡን የመልማት ጥያቄ መልስ ለመስጠት የሚያስችል ክልላዊ አቅም ለመፍጠር በትኩረት እንደሚሰራም ቢሮ ሃላፊው ጨምረው ገልጸዋል ሲል የክልሉ ኮምንኬሽን ዘግቧል::

ለተሽከርካሪ የማይፈቀድ ቦታ ላይ መኪናውን ያቆመ አሽከርካሪና ጨምሮ ቆሻሻን በኮሪደር ልማቱ ላይ የጣሉ ተቋማት ተቀጡ
***************
(ኢ.ፕ.ድ)
በአዲስ አበባ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ለተሽከርካሪ በማይፈቀድ ቦታ ላይ መኪናውን ያቆመው ግለሰብ በደንብ ማስከበር ተቀጥቷል።
በፍቅር ባርና ሬስቶራንት ድርጅት በተከለከለ ቦታ ተረፈ ምርትን እና ደረቅ ቆሻሻ በመጣላቸው ብር 50 ሺህ ብር፤ ይደምቃል ወርቅነሽና ጓደኞቿ ቆሻሻን በአግባቡና በወቅቱ ባለማንሳት ብር 20 ሺህ ብር ተቀጥተው ቆሻሻውንም እንዲያነሱ ተደርገዋል።
እንዲሁም በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ኦላ ኢነርጂ የነዳጅ ማደያ ያመነጨውን ቆሻሻ በአግባቡ ባለማስወገዱ 50 ሺህ ብር ተቀጥቷል::
በልማት ኮርደሩ ላይ የደንብ መተላለፍ የፈፀሙ ሁለት ድርጅቶችና አንድ የጽዳት ማህበር በድምሩ 120 ሺህ ብር ተቀጥቷል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከህዝቡ ጋር በመተባበር መሰረተ ልማቶች ተገቢውን ጥበቃ እንዲያገኙ የማድረግ ስራውን በሁሉም አማራጮች ትምህርት መስጠትን ጨምሮ ህጉን የሚተላለፉትን አሽከርካሪዎች እና እግረኞችን በህጉ መሰረት አስፈላጊውን መቀጮ እየሰጠ መሄዱን የሚቀጥል ይሆናል ተብሏል።