Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት !

በሚያዚያ ወር ከፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች ጋር በመገናኘት በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገን ነበር። በወቅቱም በየደረጃው ውይይቶች እንዲቀጥሉ አቅጣጫ ተቀምጦ ነበር። ዛሬ የሚያዚያው ውይይታችን ቀጣይ የሆነና ሁሉን አቀፍ ጠቀሜታ ባላቸው ሀገራዊ ጉዳዮች መግባባት መፍጠርን የተመለከተ ውይይት አድርገናል።

ሐምሌ 15 ቀን 2016 ዓ.ም
በአፋር ክልል ከ4 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ
****
(ኢ.ፕ.ድ)

በአፋር ክልል በ2016 የበጀት አመት ከ4 ቢሊዮን 228 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የክልሉ ገቢዎች ቢሮ አስታውቋል::

የአፋር ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ አቶ አወል አብዱ እንዳስታወቁት፤ በክልሉ በ2016 የበጀት አመት 5 ቢሊዮን 264 ሚሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ 4 ቢሊዮን 228 ሚሊዮን ብር ተሰብስቧል።ይህም የእቅዱ አፈፃፀም 80 በመቶ ነው::

አቶ አወል አክለውም ገቢው የተሰበሰበው ከቀጥታ ታክስ፣ ቀጥታ ካልሆነ ታክስ፣ ታክስ ነክ ካልሆነ እንዲሁም ከማዘጋጃ ቤታዊ ገቢዎች መሆኑን ተናግረዋል::

በክልሉ ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ አሟጦ በመሰብሰብ የህብረተሰቡን የመልማት ጥያቄ መልስ ለመስጠት የሚያስችል ክልላዊ አቅም ለመፍጠር በትኩረት እንደሚሰራም ቢሮ ሃላፊው ጨምረው ገልጸዋል ሲል የክልሉ ኮምንኬሽን ዘግቧል::

ሐምሌ 15 ቀን 2016 ዓ.ም
ለተሽከርካሪ የማይፈቀድ ቦታ ላይ መኪናውን ያቆመ አሽከርካሪና ጨምሮ ቆሻሻን በኮሪደር ልማቱ ላይ የጣሉ ተቋማት ተቀጡ
***************
(ኢ.ፕ.ድ)
በአዲስ አበባ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ለተሽከርካሪ በማይፈቀድ ቦታ ላይ መኪናውን ያቆመው ግለሰብ በደንብ ማስከበር ተቀጥቷል።

በፍቅር ባርና ሬስቶራንት ድርጅት በተከለከለ ቦታ ተረፈ ምርትን እና ደረቅ ቆሻሻ በመጣላቸው ብር 50 ሺህ ብር፤ ይደምቃል ወርቅነሽና ጓደኞቿ ቆሻሻን በአግባቡና በወቅቱ ባለማንሳት ብር 20 ሺህ ብር ተቀጥተው ቆሻሻውንም እንዲያነሱ ተደርገዋል።

እንዲሁም በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ኦላ ኢነርጂ የነዳጅ ማደያ ያመነጨውን ቆሻሻ በአግባቡ ባለማስወገዱ 50 ሺህ ብር ተቀጥቷል::
በልማት ኮርደሩ ላይ የደንብ መተላለፍ የፈፀሙ ሁለት ድርጅቶችና አንድ የጽዳት ማህበር በድምሩ 120 ሺህ ብር ተቀጥቷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከህዝቡ ጋር በመተባበር መሰረተ ልማቶች ተገቢውን ጥበቃ እንዲያገኙ የማድረግ ስራውን በሁሉም አማራጮች ትምህርት መስጠትን ጨምሮ ህጉን የሚተላለፉትን አሽከርካሪዎች እና እግረኞችን በህጉ መሰረት አስፈላጊውን መቀጮ እየሰጠ መሄዱን የሚቀጥል ይሆናል ተብሏል።
ሐምሌ 15 ቀን 2016 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የአረንጓዴ ዐሻራ መርሀ ግብር አካል የሆነውን የችግኝ ተከላ አካሂደዋል
**************
(ኢ.ፕ.ድ)
የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች በሀገራዊ ስትራቲጂያዊ ጉዳዮች ላይ ከኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አሕመድ ጋር ዉይይት ካካሄዱ በሗላ "ኢትዮጵያ ትተክላለች ትውልድ ያፀናል" በሚል መሪ ቃል የተጀመረው የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አካል የሆነውን የችግኝ ተከላ አካሂደዋል።

በሀገሪቷ የፖለቲካ ባህል እኩይ የሆነው በጠላትነት ተፈራርጆ ተቀራርቦ መስራት ነውር የሆነበት ጊዜ አልፎ ገዥው ፓርቲና የተፎካካሪ ፓርቲዎች በጠላትነት የሚተያዩበት ሁኔታ ተቀይሮ ለሀገር እና ለህዝብ በሚጠቅሙ ጉዳዮች ላይ በጋራ መስራት መጀመሩ ወደ ተሟላ የዴሞክራሲ ስርዓት ለሚደረገው ጉዞ ተስፋ ሰጪ ነው።

የፖለቲካ ፓርቲዎች ይህን ምእራፍ በማጠናከር የጋራ በሚያደርጓቸው ጉዳዮች በትብብር በመስራት፤በሀሳብ በመፎካከር ኢትዮጵያን የመገንባት ኃላፊነታቸውን መወጣት መቀጠል እንዳለባቸው በመርሀ ግብሩ ላይ ጥሪ ቀርቧል።

በዴሞክራሲያዊ ፉክክር መንግስት ለመሆን የሚያሸንፈውም ሆነ በውድድሩ የሚፎካከሩ ፓርቲዎች ለአገር ልማት የበኩላቸውን ሚና የመወጣት ኃላፊነታቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ተናግረዋል።

በችግኝ ተከላ መርሃ-ግብሩ የተሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲ አባላቶች የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ለአንድ አካል የሚተው ሳይሆን የሁሉንም ኢትዮጵያውያን ትብብር የሚጠይቅ መሆኑን ገልፀዋል።

በቀጣይም በሀገራዊ የልማት መርሃ ግብሮች ላይ በትብብር እንደሚሰሩ ማረጋገጣቸውን ከብልጽግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
ሐምሌ 15 ቀን 2016 ዓ.ም
በጎፋ ዞን በደረሰ ድንገተኛ የመሬት ናዳ አደጋ የበርካታ ሰዎች ሕይወት አለፈ
************
(ኢ.ፕ.ድ)
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን በደረሰ ድንገተኛ የመሬት ናዳ አደጋ የበርካታ ሰዎች ሕይወት ማላፉን የዞኑ ኮምንኬሽን ቢሮ አስታወቀ።

የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ምስክር ምትኩ አደጋውን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፥ ዛሬ ሌሊት የዘነበውን ከፍተኛ ዝናብ ተከትሎ በደረሰ የናዳ አደጋ እስካሁን በተደረገው ፍለጋ ከ 20 በላይ አስከሬን መገኘቱንና የሟቾች ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችል ገልጸዋል።

በስፍራው ለነፍስ አድን ተግባር የተሰበሰቡ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ የአካባቢው ነዋሪዎች የአደጋው ሰለባ መሆናቸውን አቶ ምስክር ተናግረዋል። በአደጋው የወረዳው ፖሊስ አባላትን ጨምሮ ሴቶችና ሕፃናት እንደሚገኙ ተገልጿል።

በአሁኑ ሰዓት የአስክሬን ፍለጋና የነፍስ አድን ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉንም ዋና አስተዳዳሪው ተናግረዋል።
የዞኑ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ማርቆስ መለሰ በበኩላቸው በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸውን የህብረተሰብ ክፍሎችን በመለየት የነፍስ አድን ሥራ እየተከናወነ መሆኑን መግለፃቸውን ከዞኑ ኮምንኬሽን ቢሮ ገኘነው መረጃ ያለመላክታል።
ሐምሌ 15 ቀን 2016 ዓ.ም