Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የአረንጓዴ ዐሻራ መርሀ ግብር አካል የሆነውን የችግኝ ተከላ አካሂደዋል
**************
(ኢ.ፕ.ድ)
የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች በሀገራዊ ስትራቲጂያዊ ጉዳዮች ላይ ከኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አሕመድ ጋር ዉይይት ካካሄዱ በሗላ "ኢትዮጵያ ትተክላለች ትውልድ ያፀናል" በሚል መሪ ቃል የተጀመረው የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አካል የሆነውን የችግኝ ተከላ አካሂደዋል።

በሀገሪቷ የፖለቲካ ባህል እኩይ የሆነው በጠላትነት ተፈራርጆ ተቀራርቦ መስራት ነውር የሆነበት ጊዜ አልፎ ገዥው ፓርቲና የተፎካካሪ ፓርቲዎች በጠላትነት የሚተያዩበት ሁኔታ ተቀይሮ ለሀገር እና ለህዝብ በሚጠቅሙ ጉዳዮች ላይ በጋራ መስራት መጀመሩ ወደ ተሟላ የዴሞክራሲ ስርዓት ለሚደረገው ጉዞ ተስፋ ሰጪ ነው።

የፖለቲካ ፓርቲዎች ይህን ምእራፍ በማጠናከር የጋራ በሚያደርጓቸው ጉዳዮች በትብብር በመስራት፤በሀሳብ በመፎካከር ኢትዮጵያን የመገንባት ኃላፊነታቸውን መወጣት መቀጠል እንዳለባቸው በመርሀ ግብሩ ላይ ጥሪ ቀርቧል።

በዴሞክራሲያዊ ፉክክር መንግስት ለመሆን የሚያሸንፈውም ሆነ በውድድሩ የሚፎካከሩ ፓርቲዎች ለአገር ልማት የበኩላቸውን ሚና የመወጣት ኃላፊነታቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ተናግረዋል።

በችግኝ ተከላ መርሃ-ግብሩ የተሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲ አባላቶች የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ለአንድ አካል የሚተው ሳይሆን የሁሉንም ኢትዮጵያውያን ትብብር የሚጠይቅ መሆኑን ገልፀዋል።

በቀጣይም በሀገራዊ የልማት መርሃ ግብሮች ላይ በትብብር እንደሚሰሩ ማረጋገጣቸውን ከብልጽግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
ሐምሌ 15 ቀን 2016 ዓ.ም
በጎፋ ዞን በደረሰ ድንገተኛ የመሬት ናዳ አደጋ የበርካታ ሰዎች ሕይወት አለፈ
************
(ኢ.ፕ.ድ)
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን በደረሰ ድንገተኛ የመሬት ናዳ አደጋ የበርካታ ሰዎች ሕይወት ማላፉን የዞኑ ኮምንኬሽን ቢሮ አስታወቀ።

የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ምስክር ምትኩ አደጋውን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፥ ዛሬ ሌሊት የዘነበውን ከፍተኛ ዝናብ ተከትሎ በደረሰ የናዳ አደጋ እስካሁን በተደረገው ፍለጋ ከ 20 በላይ አስከሬን መገኘቱንና የሟቾች ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችል ገልጸዋል።

በስፍራው ለነፍስ አድን ተግባር የተሰበሰቡ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ የአካባቢው ነዋሪዎች የአደጋው ሰለባ መሆናቸውን አቶ ምስክር ተናግረዋል። በአደጋው የወረዳው ፖሊስ አባላትን ጨምሮ ሴቶችና ሕፃናት እንደሚገኙ ተገልጿል።

በአሁኑ ሰዓት የአስክሬን ፍለጋና የነፍስ አድን ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉንም ዋና አስተዳዳሪው ተናግረዋል።
የዞኑ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ማርቆስ መለሰ በበኩላቸው በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸውን የህብረተሰብ ክፍሎችን በመለየት የነፍስ አድን ሥራ እየተከናወነ መሆኑን መግለፃቸውን ከዞኑ ኮምንኬሽን ቢሮ ገኘነው መረጃ ያለመላክታል።
ሐምሌ 15 ቀን 2016 ዓ.ም
“የሠላም ካውንስሉን ጥሪ ተቀብለው ከሚመጡ ታጣቂዎች ጋር ችግሮችን በድርድር ለመፍታት ዝግጁ ነን”
– መንገሻ ፈንታው (ዶ/ር) የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ
*******
(ኢ ፕ ድ)

የክልሉ መንግሥት የሠላም ካውንስሉን ጥሪ ተቀብለው ከሚመጡ የታጠቁ ኃይሎች ጋር ችግሮችን በድርድር ለመፍታት ዝግጁ ነው ሲሉ የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ መንገሻ ፈንታው (ዶ/ር) ገለጹ።

የአማራ ክልል የኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ መንገሻ ፈንታው (ዶ/ር) ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የክልሉ መንግሥት የሠላም ካውንስሉን ጥሪ ተቀብለው ከሚመጡ የታጠቁ ኃይሎች ጋር ችግሮችን በድርድር ለመፍታት ዝግጁ ነው።

በክልሉ የሠላምና ፀጥታ ችግሮችን ተከትሎ የሕግና የፀጥታ ማስከበር ሥራ ሲሠራ ቆይቷል ያሉት ኃላፊው፤ የሠላም ሁኔታው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መጥቶ በርካታ አካባቢዎች ላይ ሕዝቡ የሠላም አየር እየተነፈሰ ይገኛል ብለዋል፡፡

አንጻራዊ ሠላሙን ዘላቂ ለማድረግ ከሕግ ማስከበር ጎን ለጎን መሣሪያ አንግበው የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች የሠላም ጥሪ እየተላለፈ እንደሚገኝ ገልጸዋል። የክልሉ መንግሥት በማንኛውም መንገድ ለሠላም ምን ጊዜም በሩ ክፍት መሆኑን.....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=132725
“ዘመናዊ የፖለቲካና የዲሞክራሲ ሥርዓት ለመገንባት የሚያስችል ምክክር አድርገናል”
– አቶ ደስታ ዲንቃ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ
*******
(ኢ ፕ ድ)

የፖለቲካ ፓርቲዎች ዘመናዊ የፖለቲካና የዲሞክራሲ ሥርዓት ለመገንባት የሚያስችል ምክክር ከኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር አድርገናል ሲሉ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ደስታ ዲንቃ ገለጹ።

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች በሀገራዊ ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች ላይ ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር ትናንት ውይይት አካሂደዋል።

የጋራ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ አቶ ደስታ ዲንቃ ስለውይይቱ ለኢፕድ እንደገለጹት፤ ውይይቱ በተፎካካሪ ፓርቲዎችና በገዢ ፓርቲ መካከል የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን በውይይትና በንግግር ለመፍታት ያለመ ነው። ይህም በገዢው ፓርቲ እና በተፎካካሪ ፓርቲዎች መካከል ያለውን ተግባቦት ለማጠናከር ጉልህ ሚና አለው።

ለሀገርና ለትውልድ የሚያስቡ ፖለቲከኞች ሰከን ብለው ሀገሪቱ ያለፈችበትን የፖለቲካ ጉዞዎች ለመቀየር እና የተሻለ የፖለቲካ ሥርዓት ለመገንባት የተሰባሰቡበት የውይይት መድረክ ነው ያሉት አቶ ደስታ፤ በዚህም ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር ዘመናዊ........

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=132737
ለብዙዎች ተስፋ የሰነቀው – “በፍራ እናት”
***********
(ኢ ፕ ድ)
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቡታጅራ ከተማ ጎራ ብለናል። ከአውራ ጎዳናው ጥቂት ገባ እንዳልን የእናት ጓዳን የሚያስታውስ ድንቅ መዓዛ ተቀበለን።

መልካም መዓዛውን እያጣጣምን ወደ ውስጥ ዘለቅን። በዛም ቆሎ የሚያዘጋጁ፣ ለቆሎው ተጨማሪ ጣዕም የሚሰጡ ቅመማዎችን የሚያሰናዱ እንዲሁም ቆሎውን ለክተው የሚያሽጉ ብርቱ ሴቶችን አገኘን።

እንደ ባሕላችን ሰላምታ አቅርበን ስንቀላቀላቸው በመዓዛው ከሩቅ የጠራንን ቆሎ በግብዣ አቀረቡልን። ጥሬውን እየቆረጠምን ስለ ሥራቸውና ተቋማቸው ያወጉን ዘንድ ጠይቀን ውይይታችን ቀጠልን።

በሦስት ብርቱ ወጣት ሥራ ፈጣሪዎች ተመስርቶ ዛሬ ላይ ለ270 ሴቶችና ለ50 ወንዶች የሥራ ዕድል የፈጠረው ኢንተርፕራይዝ “በፍራ እናት ባልትና” ይሰኛል። በኢንተርፕራይዙ ልብስና ጉርሳቸውን ከማሟላት አልፈው የሙያ ባለቤት በመሆን ነጋቸውን በትልቁ የሚያልሙ ጠንካራ ሠራተኞች አሉ።

በቀን እስከ 35 ኩንታል ቆሎ አምርቶ ለገበያ በሚቀርብበት ኢንተርፕራይዝ በርካታ ወጣቶች ጊዜያቸውን በሥራ ያሳልፋሉ። ሥራ ፈጣሪዎቹ ምርቱን ለማሳደግና ከሀገር ቤት አልፎ ወደአጎራባች ሀገራት ገበያ ለመግባት ያልማሉ።

የምሥራች ሳሙኤል በኢንተርፕራይዙ ምርት በማሸግ ሥራ ላይ ተሰማርታለች። ትምህርቷን አጠናቃ ቤት ቁጭ ለማለት ተገዳ ነበር። ይሁን እንጂ ወደዚህ ኢንተርፕራይዝ ከገባች በኋላ በሕይወቷ ላይ ብዙ ለውጥ መምጣቱን......

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=132763
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
በሰሜን ወሎ ዞን ከስንዴ ልማት 261 ሺህ 300 ኩንታል ምርት ተሰበሰበ
******************
(ኢ ፕ ድ)
በሰሜን ወሎ ዞን በበጋ መስኖና በበልግ ወቅት የለማ 261 ሺህ 300 ኩንታል የስንዴ ምርት መሰብሰቡን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ።

ምርቱ የተሰበሰበው በሰብሉ ከለማ 12 ሺህ 064 ሄክታር መሬት ላይ መሆኑን በመምሪያው የመስኖ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ቡድን መሪ አቶ አለባቸው መራዊ ለኢዜአ ገልጸዋል።

ከተሰበሰበው የስንዴ ምርት ውስጥም 198 ሺህ 573 ኩንታል በመስኖ ቀሪው የስንዴ ምርት ደግሞ በበልግ ዝናብ ከለማው መሬት መሆኑን ተናግረዋል።

ለስንዴ ልማቱ ውጤታማነትም 16 ሺህ 942 ኩንታል ምርጥ ዘር እና 14 ሺ 622 ኩንታል ማዳበሪያ ለአርሶ አደሩ በማቅረብ በወቅቱ ጥቅም ላይ መዋሉን አስረድተዋል።

የስንዴ ምርቱም እንደ አገር ስንዴን በአገር ውስጥ በስፋት በማምረት እራስን ለመቻል የተያዘውን ግብ ለማሳካት እንደሚያግዝ አመልክተዋል።

በልማቱ ከተሳተፉ የዞኑ አርሶ አደሮች መካከል ማርዬ ፀጋው በሰጡት አስተያየት፤ በበጋው ወራት በመስኖ ካለሙት ግማሽ ሄክታር መሬት 13 ኩንታል ምርት ማግኘት እንደቻሉ ተናግረዋል።

የስዴ ምርት አዋጭነቱ ጥሩ መሆኑን ተገንዝበናል፣ ወደ ፊት ከባለሙያዎች ጋር በመመካከር የተሻለ ምርት ለማምረት ጥረት እናደርጋለን ሲሉም ገልጸዋል።

በበጋው ወራት ባደረጉት የመስኖ ልማት እንቅስቃሴ በአንድ ሄክታር ካለሙት መሬት 26 ኩንታል ምርት ማግኘታቸውን የተናገሩት ደግሞ ሌላው አርሶ አደር አበራ ሞሌ ናቸው።

የስንዴ ምርት ማምረት ከጀመሩ ሁለተኛ ዓመት እንደሆናቸው ጠቅሰው፤ የዘንድሮ ምርታቸው ከአምናው በሁለት ኩንታል ጭማሪ ማግኘት እንደቻሉ አመልክተዋል።

ለዚህም የምርጥ ዘርና የማዳበሪያ አጠቃቀምን የተሻለ ከመሆኑም በላይ ስንዴን በማልማት ልምድ በማግኘታቸው የተገኘ ውጤት መሆኑን ገልጸዋል።
ሐምሌ 16 ቀን 2016 ዓም
“የኮሪደር ልማቱ ለዜጎች ምቹ ከተማ በመገንባት ሂደት ምሳሌ መሆን ይችላል”
– ዳንኤል ሊሬቦ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የከተማ ዲዛይንና ፕላን ምሑር
***********************
(ኢ ፕ ድ)
በአዲስ አበባ እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ለዜጎች ምቹ የሆነ ከተማን በመገንባት ሂደት ምሳሌ መሆን የሚችል ሥራ ነው ሲሉ በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የከተማ ዲዛይንና ፕላን ምሑሩ ዳንኤል ሊሬቦ (ዶ/ር) አስታወቁ።

በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው የኮሪደር ልማት ላይ ሃሳባቸውን ለኢፕድ ያጋሩት ዳንኤል ሊሬቦ (ዶ/ር)፤ አዲስ አበባ ከነበረችበት ውስብስብ ችግሮች ተላቃ ደረጃዋን በሚመጥን መልኩ ዳግም እየለማች ነው ብለዋል።

ተገቢ የሆኑ የተሽከርካሪ መንገዶች፣ የእግረኛ መሄጃዎች፣ የፍሳሽና የቆሻሻ ፍሳሽ ማስወገጃ ቱቦዎች፣ የንፁሕ መጠጥ ውሃ መስመር፣ የመብራትና የቴሌ መስመሮች በሙሉ በተናበበ መልኩ እየተሠሩ መሆናቸውን የኮሪደር ልማቱ ውጤታማ መሆኑን ያሳያል ሲሉ ተናግረዋል።

የኮሪደር ልማቱ ዘላቂ የሆነ የተቀናጀ የመሠረተ ልማት ፕላን እንዲዘጋጅ አድርጓል ያሉት ምሑሩ፤ ኮሪደሩ በግራና ቀኝ የኪነ ሕንፃ ጥበባቸውን የተጠበቁ ፣ ለዓይን ማራኪ ….
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=132773
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) አምሰት ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢንሼቲቪን አስጀመሩ
*****
(ኢ ፕ ድ)
የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አምሰት ሚሊዮን ዜጎች የዲጂታል ቴክኖሎጂ ስልጠና ተጠቃሚ የሚሆኑበትን አምሰት ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢንሼቲቪን አስጀምረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በሳይንስ ሙዚየም ኢንሼቲቪን ሲያስጀምሩ እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ የነገ ተስፋዎች የሆኑ ወጣቶች ስልጠናውን በጥሞና በመከታተል ስራ ፈጣሪ፣ኩባንያ ፈጣሪና በዓለም ገበያ ተወዳድረው የሚቀጠሩ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡

ኢንሼቲቩ 5 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያ ዘመኑን በዋጀው የዲጂታል ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑን ገልጸው፤ ይህን ትልቅ ዕድል ወጣቶች በአግባቡ በመጠቀም ለኢትዮጵያ የነገ ተስፋ መሆን ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡

አምሰት ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢንሼቲቪ ከተባበሩት አረብ ኤሜሪትስ ጋር በመተባባር የሚተገበር ሲሆን 5 ሚሊዮን ዜጎች በዲጂታል ቴክኖሎጂ፣ በአርቲፎሻል ኢለጀንሽስና በተያያዥ የዲጂታላዜሽን ክህሎቶች የሚሰለጥኑበት መሆኑ ታውቋል፡፡

በጌትነት ምህረቴ

ሐምሌ 16 ቀን 2016 ዓም
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት የ2017 በጀት ዓመትን ከ17 ቢሊዮን ብር በላይ አድርጎ አጸደቀ
************
(ኢ.ፕ.ድ)
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት የ2017 በጀት ዓመትን 17 ነጽብ ስድስት ቢሊዮን ብር አድርጎ አጸደቀ::

ረቂቅ የበጀት አዋጁን የበጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክብርት ወ/ሮ የኋላሸት በላይነህ ለምክርቤቱ አቅርበዋል።

የቀረበው በጀት ከክልል ገቢ የሚሰበሰብ፣ ከፌዴራል መንግስት ድጎማና ከሌሎች የገቢ ምንጮች የሚገኝ መሆኑን የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አብራርተዋል ።

የበጀት ምንጩ ከፌዴራል መንግስት ግምጃቤት ፣ ከውጭ እርዳታ፣ ከዘላቂ ልማት ግቦች፣ ከመደበኛ ገቢ፣ ከጤና ተቋማት፣ ከማዘጋጃ ቤት ገቢ፣ ከትምህርት ቤቶች ገቢና ከቴሌቶን እንደሚሰበሰብም ሰብሳቢዋ አብራርተዋል።

በቀረበው ዝርዝር የበጀት ረቂቅ አዋጅ ላይ በምክር ቤቱ አባላት አስተያየቶች ተነስተዋል ።
በረቂቅ በጀት አዋጅ ላይ ከምክር ቤት አባላት ለተነሳው ሀሳብ እና አስተያየት የሰጡት የክልሉ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በበኩላቸው የቀረበው የ2017 በጀት ውጤታማ እንዲሆን ክልላዊ የገቢ አማራጮችን በመጠቀም ገቢ መሰብሰብ ይገባል ብለዋል።

በጀቱንም ለሰብዓዊ ጉዳዮች ቅድሚያ በመስጠት እንዲሁም ከሌብነት፣ ከብክነትና ከብልሹ አሰራር በጸዳ መልኩ የፋይናንስ መመሪያና ደንብን ተከትሎ ስራ ላይ ማዋል እንደሚገባ አሳስበዋል ሲል የክልሉ ኮምንኬሽን ቢሮ ዘግቧል።
ሐምሌ 15 ቀን 2016 ዓ.ም