Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
በሰሜን ወሎ ዞን ከስንዴ ልማት 261 ሺህ 300 ኩንታል ምርት ተሰበሰበ
******************
(ኢ ፕ ድ)
በሰሜን ወሎ ዞን በበጋ መስኖና በበልግ ወቅት የለማ 261 ሺህ 300 ኩንታል የስንዴ ምርት መሰብሰቡን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ።

ምርቱ የተሰበሰበው በሰብሉ ከለማ 12 ሺህ 064 ሄክታር መሬት ላይ መሆኑን በመምሪያው የመስኖ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ቡድን መሪ አቶ አለባቸው መራዊ ለኢዜአ ገልጸዋል።

ከተሰበሰበው የስንዴ ምርት ውስጥም 198 ሺህ 573 ኩንታል በመስኖ ቀሪው የስንዴ ምርት ደግሞ በበልግ ዝናብ ከለማው መሬት መሆኑን ተናግረዋል።

ለስንዴ ልማቱ ውጤታማነትም 16 ሺህ 942 ኩንታል ምርጥ ዘር እና 14 ሺ 622 ኩንታል ማዳበሪያ ለአርሶ አደሩ በማቅረብ በወቅቱ ጥቅም ላይ መዋሉን አስረድተዋል።

የስንዴ ምርቱም እንደ አገር ስንዴን በአገር ውስጥ በስፋት በማምረት እራስን ለመቻል የተያዘውን ግብ ለማሳካት እንደሚያግዝ አመልክተዋል።

በልማቱ ከተሳተፉ የዞኑ አርሶ አደሮች መካከል ማርዬ ፀጋው በሰጡት አስተያየት፤ በበጋው ወራት በመስኖ ካለሙት ግማሽ ሄክታር መሬት 13 ኩንታል ምርት ማግኘት እንደቻሉ ተናግረዋል።

የስዴ ምርት አዋጭነቱ ጥሩ መሆኑን ተገንዝበናል፣ ወደ ፊት ከባለሙያዎች ጋር በመመካከር የተሻለ ምርት ለማምረት ጥረት እናደርጋለን ሲሉም ገልጸዋል።

በበጋው ወራት ባደረጉት የመስኖ ልማት እንቅስቃሴ በአንድ ሄክታር ካለሙት መሬት 26 ኩንታል ምርት ማግኘታቸውን የተናገሩት ደግሞ ሌላው አርሶ አደር አበራ ሞሌ ናቸው።

የስንዴ ምርት ማምረት ከጀመሩ ሁለተኛ ዓመት እንደሆናቸው ጠቅሰው፤ የዘንድሮ ምርታቸው ከአምናው በሁለት ኩንታል ጭማሪ ማግኘት እንደቻሉ አመልክተዋል።

ለዚህም የምርጥ ዘርና የማዳበሪያ አጠቃቀምን የተሻለ ከመሆኑም በላይ ስንዴን በማልማት ልምድ በማግኘታቸው የተገኘ ውጤት መሆኑን ገልጸዋል።
ሐምሌ 16 ቀን 2016 ዓም
“የኮሪደር ልማቱ ለዜጎች ምቹ ከተማ በመገንባት ሂደት ምሳሌ መሆን ይችላል”
– ዳንኤል ሊሬቦ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የከተማ ዲዛይንና ፕላን ምሑር
***********************
(ኢ ፕ ድ)
በአዲስ አበባ እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ለዜጎች ምቹ የሆነ ከተማን በመገንባት ሂደት ምሳሌ መሆን የሚችል ሥራ ነው ሲሉ በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የከተማ ዲዛይንና ፕላን ምሑሩ ዳንኤል ሊሬቦ (ዶ/ር) አስታወቁ።

በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው የኮሪደር ልማት ላይ ሃሳባቸውን ለኢፕድ ያጋሩት ዳንኤል ሊሬቦ (ዶ/ር)፤ አዲስ አበባ ከነበረችበት ውስብስብ ችግሮች ተላቃ ደረጃዋን በሚመጥን መልኩ ዳግም እየለማች ነው ብለዋል።

ተገቢ የሆኑ የተሽከርካሪ መንገዶች፣ የእግረኛ መሄጃዎች፣ የፍሳሽና የቆሻሻ ፍሳሽ ማስወገጃ ቱቦዎች፣ የንፁሕ መጠጥ ውሃ መስመር፣ የመብራትና የቴሌ መስመሮች በሙሉ በተናበበ መልኩ እየተሠሩ መሆናቸውን የኮሪደር ልማቱ ውጤታማ መሆኑን ያሳያል ሲሉ ተናግረዋል።

የኮሪደር ልማቱ ዘላቂ የሆነ የተቀናጀ የመሠረተ ልማት ፕላን እንዲዘጋጅ አድርጓል ያሉት ምሑሩ፤ ኮሪደሩ በግራና ቀኝ የኪነ ሕንፃ ጥበባቸውን የተጠበቁ ፣ ለዓይን ማራኪ ….
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=132773
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) አምሰት ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢንሼቲቪን አስጀመሩ
*****
(ኢ ፕ ድ)
የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አምሰት ሚሊዮን ዜጎች የዲጂታል ቴክኖሎጂ ስልጠና ተጠቃሚ የሚሆኑበትን አምሰት ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢንሼቲቪን አስጀምረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በሳይንስ ሙዚየም ኢንሼቲቪን ሲያስጀምሩ እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ የነገ ተስፋዎች የሆኑ ወጣቶች ስልጠናውን በጥሞና በመከታተል ስራ ፈጣሪ፣ኩባንያ ፈጣሪና በዓለም ገበያ ተወዳድረው የሚቀጠሩ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡

ኢንሼቲቩ 5 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያ ዘመኑን በዋጀው የዲጂታል ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑን ገልጸው፤ ይህን ትልቅ ዕድል ወጣቶች በአግባቡ በመጠቀም ለኢትዮጵያ የነገ ተስፋ መሆን ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡

አምሰት ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢንሼቲቪ ከተባበሩት አረብ ኤሜሪትስ ጋር በመተባባር የሚተገበር ሲሆን 5 ሚሊዮን ዜጎች በዲጂታል ቴክኖሎጂ፣ በአርቲፎሻል ኢለጀንሽስና በተያያዥ የዲጂታላዜሽን ክህሎቶች የሚሰለጥኑበት መሆኑ ታውቋል፡፡

በጌትነት ምህረቴ

ሐምሌ 16 ቀን 2016 ዓም
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት የ2017 በጀት ዓመትን ከ17 ቢሊዮን ብር በላይ አድርጎ አጸደቀ
************
(ኢ.ፕ.ድ)
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት የ2017 በጀት ዓመትን 17 ነጽብ ስድስት ቢሊዮን ብር አድርጎ አጸደቀ::

ረቂቅ የበጀት አዋጁን የበጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክብርት ወ/ሮ የኋላሸት በላይነህ ለምክርቤቱ አቅርበዋል።

የቀረበው በጀት ከክልል ገቢ የሚሰበሰብ፣ ከፌዴራል መንግስት ድጎማና ከሌሎች የገቢ ምንጮች የሚገኝ መሆኑን የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አብራርተዋል ።

የበጀት ምንጩ ከፌዴራል መንግስት ግምጃቤት ፣ ከውጭ እርዳታ፣ ከዘላቂ ልማት ግቦች፣ ከመደበኛ ገቢ፣ ከጤና ተቋማት፣ ከማዘጋጃ ቤት ገቢ፣ ከትምህርት ቤቶች ገቢና ከቴሌቶን እንደሚሰበሰብም ሰብሳቢዋ አብራርተዋል።

በቀረበው ዝርዝር የበጀት ረቂቅ አዋጅ ላይ በምክር ቤቱ አባላት አስተያየቶች ተነስተዋል ።
በረቂቅ በጀት አዋጅ ላይ ከምክር ቤት አባላት ለተነሳው ሀሳብ እና አስተያየት የሰጡት የክልሉ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በበኩላቸው የቀረበው የ2017 በጀት ውጤታማ እንዲሆን ክልላዊ የገቢ አማራጮችን በመጠቀም ገቢ መሰብሰብ ይገባል ብለዋል።

በጀቱንም ለሰብዓዊ ጉዳዮች ቅድሚያ በመስጠት እንዲሁም ከሌብነት፣ ከብክነትና ከብልሹ አሰራር በጸዳ መልኩ የፋይናንስ መመሪያና ደንብን ተከትሎ ስራ ላይ ማዋል እንደሚገባ አሳስበዋል ሲል የክልሉ ኮምንኬሽን ቢሮ ዘግቧል።
ሐምሌ 15 ቀን 2016 ዓ.ም
የብልጽግና ፓርቲ መልዕክት
ብልፅግና ፓርቲ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን፣ ገዜ ጎፋ ወረዳ፣ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በተከሰተው የመሬት ናዳ በዜጎች ላይ በደረሰው አደጋ የተሰማውን ጥልቅ ልባዊ ሀዘን ይገልፃል።

በአደጋው ጉዳት ለደረሰባቸው የተጎጂ ቤተሰቦች እና ዘመድ ወዳጆች ሁሉ መፅናናትን ይመኛል።

በቀጣይም በአደጋው ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች መልሶ ለማቋቋም ብልፅግና ፓርቲ ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር የበኩሉን ድርሻ የሚወጣ ይሆናል።
ሐምሌ 16 ቀን 2016 ዓ.ም
በጎፋ ዞን በተከሰተው የመሬት ናዳ ለተጎዱ ወገኖችና ቤተሰቦች የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል
*************
- የሟቾች ቁጥር ከ150 ማለፉ ተገልጿል
(ኢ ፕ ድ)
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ትላንት ረፋድ አካባቢ በተከሰተው የመሬት ናዳ ለተጎዱ ወገኖችና ህይወታቸው ላጡ ቤተሰቦች የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠሉን የክልሉ መንግስት ኮምንኬሽን ቢሮ አስታውቋል፡፡

በአከባቢው በጣለዉ ከፍተኛ ዝናብ ምክንያት በተከሰተዉ የመሬት ናዳ በአንድ የቤተሰብ አባላት ላይ ጉዳት መድረሱን ተከትሎ እነሱን ለማትረፍ በወጡት ተጨማሪ ሰዎች ላይ የመሬት ናዳ በመከሰቱ የሟቾች ቁጥር ከፍ ማለቱን የክልሉ መንግስት ኮምንኬሽን ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሰናይት ሰለሞን ገልፀዋል፡፡

የክልሉ መንግስት በአደጋው የተጎዱ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋምና ለመደገፍ ኮሚቴ አቋቁሞ እየሰራም እደሚገኝ ተናግረዋል ።

የተጎዱ ዜጎችን መደገፍና የነፍስ አድን ስራ ቅድሚያ ተሰጥቶ እየተሰራ ይገኛል ያሉት ወ/ሮ ሰናይት በአከባቢዉ ተጨማሪ ጉዳት እንዳይከሰት ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ እየተሰራ መሆኑንም አስታውቀዋል።

የመንግስት አካላት ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመተባበር በአሁኑ ሰአት የተጎዱ ሰዎችን ነብስ ለማዳን እና ለተጎጂዎች አስፈላጊውን የህክምና የመጠለያ እና ምግብ በማቅረብ በርብርብ ላይ ይገኛል።

በአደጋው እስካሁን ድረስ ከ150 በላይ ሰዎች ህይወታቸውን ማጣቸውም ተገልጿል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን፣ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር፣ እና ከአጎራባች ክልሎች እና ዞኖች የተወጣጡ ባለሞያዎች በሥፍራው በመገኘት ለተጎጂዎች ድጋፍ እያደረጉ እንደሚገኝ ከክልሉ ኮምንኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ሐምሌ 16 ቀን 2016 ዓ.ም
በጎፋ ዞን በመሬት ናዳ አደጋ ለተጎዱ ዜጎች አፋጣኝ ምላሽ እየተሰጠ ነው
****
(ኢ.ፕ.ድ)

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን በደረሰው የመሬት ናዳ አደጋ ለተጎዱና ለተፈናቀሉ ወገኖች አፋጣኝ ምላሽ እየተሰጠ መሆኑን የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።

የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም (ዶ/ር) በሰጡት መግለጫ እንዳሉት በዞኑ በተከሰተው የመሬት ናዳ አደጋ በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል።

ሀምሌ 14 ቀን 2016 ዓ.ም በነበረው ከፍተኛ ዝናብ ምክንያት የመሬት ናዳው ማጋጠሙን ጠቁመዋል።

በመጀመሪያው ናዳ 4 ሰዎች መሞታቸውን እና እነዚህን ለማውጣት የሄዱ ወገኖች የሁለተኛው ናዳ ሰለባ መሆናቸውን አመላክተዋል።

ጉዳቱ ከተከሰተ ጀምሮ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የሚያስችሉ ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል።

በጉዳቱ 400 የሚሆኑ ዜጎች መፈናቀላቸውን ጠቅሰው፤ የሚያስፈልጋቸውን ምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑን አንስተዋል።

አሁንም ተጨማሪ ጉዳት እንዳይፈጠር ከበርካታ ተቋማት የተውጣጡ የባለሙያዎች ቡድን ወደስፍራው መላኩን ገልጸዋል፡፡

ተፈናቃዮችን ወደ ምቹ አካባቢ የማስፈርና አስፈላጊውን ድጋፍ የማቅረብ ስራዎች ጎን ለጎን እየተሰሩ መሆኑን መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ሐምሌ 16 ቀን 2016 ዓ.ም
በ2017 በጀት ዓመት 386 አዳዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ለመስጠት ታቅዷል

4 ነጥብ 52 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል

******************
(ኢ ፕ ድ)
በ2017 በጀት ዓመት 386 አዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ለመስጠት እና ከውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፍሰት አራት ነጥብ 52 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት አቅዶ እየሠራ መሆኑን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ወይዘሮ ሃና አርአያስላሴ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደተናገሩት፣ ኮሚሽኑ በ2017 በጀት ዓመት ኃላፊነቱን ከመወጣት አኳያ በአምስት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ አተኩሮ በመሥራት፣ አዳዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃዶችን በመስጠት ከውጪ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት የሚገኘውን ገቢም ለማሳደግ አቅዶ እየሠራ ነው፡፡

እንደ ወይዘሮ ሃና ገለጻ፣ የኢንቨስትመንት ከባቢ ሁኔታን ማሻሻል፣ በ2016 በጀት ዓመት የወጡ አዳዲስ ሕጎችን ሙሉ ለሙሉ ወደ ሥራ ማስገባት፣ የሎጂስቲክስና የኢንቨስትመንት ማበረታቻ ሥርዓት ማሻሻያዎችን ማድረግ እና የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን ሥራን ……….

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩነ ይጫኑ
https://press.et/?p=132794
ምዘና አልባው የመንጃ ፈቃድ እድሳት
****************
(ኢ.ፕ.ድ)
... መንጃ ፈቃድ ካወጣ ስድስት ዓመታትን ያስቆጠረት ወጣት ሱራፌል አራጌ፣ እስካሁን ድረስ መንጃ ፈቃዴን ከማሳደስ ውጪ መኪና አሽከርክሬ አላውቅም ይላል::

መንጃ ፈቃድ ያለው ሁሉ መኪና ያሽከረክራል ማለት አይደለም የሚለው ወጣቱ፤ በእድሳቱ ወቅት የመንጃ ፈቃዱ ባለቤት መጠነኛ የሙያ ፈተና የሚፈተንበት አሠራር ቢኖር መልካም እንደሆነ ያስረዳል።

መንጃ ፈቃድ ማሳደሻው ጊዜ ካለፈ ግን ግዴታ ለሰዓታት የተግባር ፈተና መውሰድ ይጠይቃል ያለው ወጣቱ፤ የመኪና ማሽከርከር ቴክኒካል እውቀት እንደመሆኑ ከሥራው ጋር መቆየትን የሚጠይቅ በመሆኑ አሠራሩ የማሳደሻ ጊዜ ላለፈበት ብቻ ሳይሆን፣ ሁሉንም የሚያካትት ሊሆን ይገባል ይላል።

ይህን አሠራር በአጭር ጊዜ መተግባር ከባድ ቢሆን እንኳ፣ መንጃ ፈቃድ ይዞ ሲያሽከረክር የቆየውን ሳያሽከረክር ከቆየው የሚለይበት...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=132796