ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) አምሰት ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢንሼቲቪን አስጀመሩ
*****
(ኢ ፕ ድ)
የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አምሰት ሚሊዮን ዜጎች የዲጂታል ቴክኖሎጂ ስልጠና ተጠቃሚ የሚሆኑበትን አምሰት ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢንሼቲቪን አስጀምረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በሳይንስ ሙዚየም ኢንሼቲቪን ሲያስጀምሩ እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ የነገ ተስፋዎች የሆኑ ወጣቶች ስልጠናውን በጥሞና በመከታተል ስራ ፈጣሪ፣ኩባንያ ፈጣሪና በዓለም ገበያ ተወዳድረው የሚቀጠሩ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
ኢንሼቲቩ 5 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያ ዘመኑን በዋጀው የዲጂታል ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑን ገልጸው፤ ይህን ትልቅ ዕድል ወጣቶች በአግባቡ በመጠቀም ለኢትዮጵያ የነገ ተስፋ መሆን ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡
አምሰት ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢንሼቲቪ ከተባበሩት አረብ ኤሜሪትስ ጋር በመተባባር የሚተገበር ሲሆን 5 ሚሊዮን ዜጎች በዲጂታል ቴክኖሎጂ፣ በአርቲፎሻል ኢለጀንሽስና በተያያዥ የዲጂታላዜሽን ክህሎቶች የሚሰለጥኑበት መሆኑ ታውቋል፡፡
በጌትነት ምህረቴ
ሐምሌ 16 ቀን 2016 ዓም

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት የ2017 በጀት ዓመትን ከ17 ቢሊዮን ብር በላይ አድርጎ አጸደቀ
************
(ኢ.ፕ.ድ)
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት የ2017 በጀት ዓመትን 17 ነጽብ ስድስት ቢሊዮን ብር አድርጎ አጸደቀ::
ረቂቅ የበጀት አዋጁን የበጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክብርት ወ/ሮ የኋላሸት በላይነህ ለምክርቤቱ አቅርበዋል።
የቀረበው በጀት ከክልል ገቢ የሚሰበሰብ፣ ከፌዴራል መንግስት ድጎማና ከሌሎች የገቢ ምንጮች የሚገኝ መሆኑን የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አብራርተዋል ።
የበጀት ምንጩ ከፌዴራል መንግስት ግምጃቤት ፣ ከውጭ እርዳታ፣ ከዘላቂ ልማት ግቦች፣ ከመደበኛ ገቢ፣ ከጤና ተቋማት፣ ከማዘጋጃ ቤት ገቢ፣ ከትምህርት ቤቶች ገቢና ከቴሌቶን እንደሚሰበሰብም ሰብሳቢዋ አብራርተዋል።
በቀረበው ዝርዝር የበጀት ረቂቅ አዋጅ ላይ በምክር ቤቱ አባላት አስተያየቶች ተነስተዋል ።
በረቂቅ በጀት አዋጅ ላይ ከምክር ቤት አባላት ለተነሳው ሀሳብ እና አስተያየት የሰጡት የክልሉ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በበኩላቸው የቀረበው የ2017 በጀት ውጤታማ እንዲሆን ክልላዊ የገቢ አማራጮችን በመጠቀም ገቢ መሰብሰብ ይገባል ብለዋል።
በጀቱንም ለሰብዓዊ ጉዳዮች ቅድሚያ በመስጠት እንዲሁም ከሌብነት፣ ከብክነትና ከብልሹ አሰራር በጸዳ መልኩ የፋይናንስ መመሪያና ደንብን ተከትሎ ስራ ላይ ማዋል እንደሚገባ አሳስበዋል ሲል የክልሉ ኮምንኬሽን ቢሮ ዘግቧል።
ሐምሌ 15 ቀን 2016 ዓ.ም

የብልጽግና ፓርቲ መልዕክት
ብልፅግና ፓርቲ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን፣ ገዜ ጎፋ ወረዳ፣ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በተከሰተው የመሬት ናዳ በዜጎች ላይ በደረሰው አደጋ የተሰማውን ጥልቅ ልባዊ ሀዘን ይገልፃል።
በአደጋው ጉዳት ለደረሰባቸው የተጎጂ ቤተሰቦች እና ዘመድ ወዳጆች ሁሉ መፅናናትን ይመኛል።
በቀጣይም በአደጋው ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች መልሶ ለማቋቋም ብልፅግና ፓርቲ ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር የበኩሉን ድርሻ የሚወጣ ይሆናል።
ሐምሌ 16 ቀን 2016 ዓ.ም

በጎፋ ዞን በተከሰተው የመሬት ናዳ ለተጎዱ ወገኖችና ቤተሰቦች የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል
*************
- የሟቾች ቁጥር ከ150 ማለፉ ተገልጿል
(ኢ ፕ ድ)
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ትላንት ረፋድ አካባቢ በተከሰተው የመሬት ናዳ ለተጎዱ ወገኖችና ህይወታቸው ላጡ ቤተሰቦች የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠሉን የክልሉ መንግስት ኮምንኬሽን ቢሮ አስታውቋል፡፡
በአከባቢው በጣለዉ ከፍተኛ ዝናብ ምክንያት በተከሰተዉ የመሬት ናዳ በአንድ የቤተሰብ አባላት ላይ ጉዳት መድረሱን ተከትሎ እነሱን ለማትረፍ በወጡት ተጨማሪ ሰዎች ላይ የመሬት ናዳ በመከሰቱ የሟቾች ቁጥር ከፍ ማለቱን የክልሉ መንግስት ኮምንኬሽን ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሰናይት ሰለሞን ገልፀዋል፡፡
የክልሉ መንግስት በአደጋው የተጎዱ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋምና ለመደገፍ ኮሚቴ አቋቁሞ እየሰራም እደሚገኝ ተናግረዋል ።
የተጎዱ ዜጎችን መደገፍና የነፍስ አድን ስራ ቅድሚያ ተሰጥቶ እየተሰራ ይገኛል ያሉት ወ/ሮ ሰናይት በአከባቢዉ ተጨማሪ ጉዳት እንዳይከሰት ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ እየተሰራ መሆኑንም አስታውቀዋል።
የመንግስት አካላት ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመተባበር በአሁኑ ሰአት የተጎዱ ሰዎችን ነብስ ለማዳን እና ለተጎጂዎች አስፈላጊውን የህክምና የመጠለያ እና ምግብ በማቅረብ በርብርብ ላይ ይገኛል።
በአደጋው እስካሁን ድረስ ከ150 በላይ ሰዎች ህይወታቸውን ማጣቸውም ተገልጿል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን፣ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር፣ እና ከአጎራባች ክልሎች እና ዞኖች የተወጣጡ ባለሞያዎች በሥፍራው በመገኘት ለተጎጂዎች ድጋፍ እያደረጉ እንደሚገኝ ከክልሉ ኮምንኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በጎፋ ዞን በመሬት ናዳ አደጋ ለተጎዱ ዜጎች አፋጣኝ ምላሽ እየተሰጠ ነው
****
(ኢ.ፕ.ድ)
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን በደረሰው የመሬት ናዳ አደጋ ለተጎዱና ለተፈናቀሉ ወገኖች አፋጣኝ ምላሽ እየተሰጠ መሆኑን የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።
የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም (ዶ/ር) በሰጡት መግለጫ እንዳሉት በዞኑ በተከሰተው የመሬት ናዳ አደጋ በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል።
ሀምሌ 14 ቀን 2016 ዓ.ም በነበረው ከፍተኛ ዝናብ ምክንያት የመሬት ናዳው ማጋጠሙን ጠቁመዋል።
በመጀመሪያው ናዳ 4 ሰዎች መሞታቸውን እና እነዚህን ለማውጣት የሄዱ ወገኖች የሁለተኛው ናዳ ሰለባ መሆናቸውን አመላክተዋል።
ጉዳቱ ከተከሰተ ጀምሮ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የሚያስችሉ ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል።
በጉዳቱ 400 የሚሆኑ ዜጎች መፈናቀላቸውን ጠቅሰው፤ የሚያስፈልጋቸውን ምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑን አንስተዋል።
አሁንም ተጨማሪ ጉዳት እንዳይፈጠር ከበርካታ ተቋማት የተውጣጡ የባለሙያዎች ቡድን ወደስፍራው መላኩን ገልጸዋል፡፡
ተፈናቃዮችን ወደ ምቹ አካባቢ የማስፈርና አስፈላጊውን ድጋፍ የማቅረብ ስራዎች ጎን ለጎን እየተሰሩ መሆኑን መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በ2017 በጀት ዓመት 386 አዳዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ለመስጠት ታቅዷል
4 ነጥብ 52 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል
******************
(ኢ ፕ ድ)
በ2017 በጀት ዓመት 386 አዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ለመስጠት እና ከውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፍሰት አራት ነጥብ 52 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት አቅዶ እየሠራ መሆኑን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ገለጸ፡፡
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ወይዘሮ ሃና አርአያስላሴ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደተናገሩት፣ ኮሚሽኑ በ2017 በጀት ዓመት ኃላፊነቱን ከመወጣት አኳያ በአምስት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ አተኩሮ በመሥራት፣ አዳዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃዶችን በመስጠት ከውጪ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት የሚገኘውን ገቢም ለማሳደግ አቅዶ እየሠራ ነው፡፡
እንደ ወይዘሮ ሃና ገለጻ፣ የኢንቨስትመንት ከባቢ ሁኔታን ማሻሻል፣ በ2016 በጀት ዓመት የወጡ አዳዲስ ሕጎችን ሙሉ ለሙሉ ወደ ሥራ ማስገባት፣ የሎጂስቲክስና የኢንቨስትመንት ማበረታቻ ሥርዓት ማሻሻያዎችን ማድረግ እና የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን ሥራን ……….
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩነ ይጫኑ
https://press.et/?p=132794

ምዘና አልባው የመንጃ ፈቃድ እድሳት
****************
(ኢ.ፕ.ድ)
... መንጃ ፈቃድ ካወጣ ስድስት ዓመታትን ያስቆጠረት ወጣት ሱራፌል አራጌ፣ እስካሁን ድረስ መንጃ ፈቃዴን ከማሳደስ ውጪ መኪና አሽከርክሬ አላውቅም ይላል::
መንጃ ፈቃድ ያለው ሁሉ መኪና ያሽከረክራል ማለት አይደለም የሚለው ወጣቱ፤ በእድሳቱ ወቅት የመንጃ ፈቃዱ ባለቤት መጠነኛ የሙያ ፈተና የሚፈተንበት አሠራር ቢኖር መልካም እንደሆነ ያስረዳል።
መንጃ ፈቃድ ማሳደሻው ጊዜ ካለፈ ግን ግዴታ ለሰዓታት የተግባር ፈተና መውሰድ ይጠይቃል ያለው ወጣቱ፤ የመኪና ማሽከርከር ቴክኒካል እውቀት እንደመሆኑ ከሥራው ጋር መቆየትን የሚጠይቅ በመሆኑ አሠራሩ የማሳደሻ ጊዜ ላለፈበት ብቻ ሳይሆን፣ ሁሉንም የሚያካትት ሊሆን ይገባል ይላል።
ይህን አሠራር በአጭር ጊዜ መተግባር ከባድ ቢሆን እንኳ፣ መንጃ ፈቃድ ይዞ ሲያሽከረክር የቆየውን ሳያሽከረክር ከቆየው የሚለይበት...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=132796

በሃዋሳ የተጀመረው የኮሪደር ልማት የቱሪዝም እንቅስቃሴውን ለማሳደግ ያስችላል
*********
(ኢ.ፕ.ድ)
በሐዋሳ ከተማ የተጀመረው የኮሪደር ልማት ሥራ የቱሪዝም እንቅስቃሴውን ለማሳደግ እንደሚያስችል የከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ።
የሃዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ መኩሪያ መርሻዬ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በቅርቡ በከተማዋ የተጀመረው የኮሪደር ልማት የከተማዋን ገጽታ በተሻለ ሁኔታ ለመቀየር ያስችላል።
የኮሪደር ልማቱ የመንገድ ማስዋብ ሥራዎችን ያካተተ፣ የብስክሌት እና የእግረኛ መንገዶችን የለየ እንዲሁም የአካል ጉዳተኞችን ከግምት ባስገባ መልኩ እየተከናወነ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=132847

በሞጆ ከተማ በ2017 በጀት ዓመት ከ75 በላይ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ይገነባሉ
*********
(ኢ.ፕ.ድ)
በ2017 በጀት ዓመት ከ75 በላይ የተለያዩ ፕሮጀክቶች እንደሚገነቡና ለ20 ሺህ ወጣቶች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ እድል እንደሚፈጠሩ የሞጆ ከተማ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።
የሞጆ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ እሸቱ ሹሚ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ ከተማ አስተዳደሩ የከተማውን ሕዝብ የመሠረተ ልማት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት በትኩረት እየተሠራ ይገኛል።
በዚህም በ2017 በጀት ዓመት የከተማውን ሕዝብ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ከ75 በላይ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ይገነባሉ።
ፕሮጀክቶቹን ወደ ሥራ ለማስገባት የዝግጅት ሥራዎች እየተሠሩ ነው ያሉት አቶ እሸቱ፤ በቀጣይም የህብረተሰቡን መሠረታዊ ችግር ሊቀርፉ የሚችሉ ሥራዎች እውን....
https://press.et/?p=132845

የሰነድ መዋዕለ ንዋይ መመሪያ ለካፒታል ገበያ መጠናከር አይነተኛ ሚና ይኖረዋል
*************
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ያዘጋጀውና ለሰነድ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ፈቃድ መስጠት የሚያስችለው መመሪያ ለካፒታል ገበያ መጠናከር ለዘርፉ ዕድገት አይነተኛ ሚና እንደሚኖረው በሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ መመህርና የኢኮኖሚ ተመራማሪ የሆኑት ሞላ አለማየሁ (ዶ/ር) ተናገሩ።
ሞላ አለማየሁ (ዶ/ር) ለኢፕድ እንዳስታወቁት፤ የመዋዕለ ንዋይ መመሪያ አስተዳደር መኖር የካፒታል ኢንቨስትመንት ወደሀገር ሲመጣ እንዴት በአግባቡ ማስተዳደር ይቻላል የሚለውን የሚወስን ሕግ ነው። መመሪያው መዘጋጀቱ የካፒታል ገበያ እድገትን ለማፋጠንና ለማጠናከር ይረዳል።
በተጨማሪ ከፈቃድ አሰጣጡ ጋር ተያይዞ አዳዲስ እውቀትና ቴክኖሎጂዎች እንደሚመጡ ጠቁመው፤ ዘርፉን ለመቆጣጠርና ለማስተዳደር መመሪያው አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል።
ኢንቨስትመንቱም እንዲስፋፋና በተወሰኑ ነገሮች ለይ ብቻ ትኩረት
ሙሉውን ለማነበብ ሊንኩን ይጫኑ …………..
https://press.et/?p=132797