Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
299 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ከስሀላ ሰየምት ወደ ዝቋላ በጀልባ ተሳፍረው ሲጎዙ የነበሩ 19 ሰዎች ሕይወት አለፈ
**************
(ኢ.ፕ.ድ)
ትናንት ከቀኑ 6፡00 ገዳማ ከዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ስሃላ ሰየምት ወረዳ ወደ ዝቋላ ወረዳ በተከዜ ወንዝ በጀልባ ሲጎዙ ከነበሩት በግምት 26 ሰዎች ውስጥ 19 የሚደርሱ ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉን የስሃላ ሰየምት ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪ ሲሳይ ብሩ ገልጸዋል።

ከ26ቱ ሰዎች አንድ ሕጻንን ጨምሮ 7 ሰዎች በአስቸጋሪ ሁኔታ ሕይወታቸው ተርፏል ያሉት አቶ ሲሳይ የሟቾቹ ቁጥር ከዚያ በላይ ሊኾን ይችላል ብለዋል።

አደጋው ከደረሰ በኋላ የሟቾችን አስከሬን ለመፈለግ በተደረገው ጥረት እስከ ዛሬ ድረስ ሁለት ሰዎች ብቻ አስከሬን መገኘቱን ተናግረዋል።

ዋና አሥተዳዳሪው ሕይወቱ የተረፈው አንድ ሕጻን ከፍተኛ ጉዳት ስላስተናገደ ወደ ሰቆጣ ተፈራ ኃይሉ መታሰብያ ጠቅላላ ሆስፒታል ሲላክ የተቀሩት ስድስቱ መሸሀ ጤና ጣብያ ገብተው የህክምና ክትትል እየተደረገባቸው ነው ብለዋል።

ከአራት ዓመታት በላይ ከጥቅም ውጭ የኾነው እና እስከ ሰኔ ወር መጨረሻዎች ድረስ ይጠናቀቃል ተብሎ የነበረው ከስሃላ - ዝቋላ የሚያገናኘው የተከዜ የብረት ድልድይ በተያዘለት ጊዜ አለመጠናቀቁ የሰው ሕይወት መቅጠፉን እንዲቀጥል ምክንያት መኾኑን አቶ ሲሳይ ለአሚኮ ተናግረዋል።

ሐምሌ 21 ቀን 2016 ዓ.ም
አምስት ሚሊዮን ዜጎችን የንፁሕ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዷል
*********
(ኢ.ፕ.ድ)
በ2017 በጀት ዓመት ከአምስት ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያንን የንፁሕ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ለማድረግ መታቀዱን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጅነር ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ በ2017 በጀት ዓመት አጠቃላይ የመጠጥ ውሃ ተጠቃሚ የሆነ ሕዝብ ብዛትን ከነበረበት 74 ሚሊዮን 661 ሺህ 037 ወደ 80 ሚሊዮን ለማሳደግ ታቅዷል።

በዚህም ከአምስት ሚሊዮን በላይ ዜጎች የንፁሕ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት ይሠራል።
በ2017 በጀት ዓመት አጠቃላይ የመጠጥ ውሃ ተጠቃሚ የሆነ የገጠር ሕዝብ ብዛትን ከነበረበት 54 ነጥብ ዘጠኝ...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=133108
“አገልግሎት አሰጣጥን በቴክኖሎጂ በመደገፍ ጊዜና ሀብትን ከብክነት መታደግ ይገባል”
ወርቁ ጋቸና
የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር
***********
(ኢ.ፕ.ድ)
አገልግሎት አሰጣጥና መረጃ አያያዝን በቴክኖሎጂ በመደገፍ የሀገሪቱን ጊዜና ሀብት ከብክነት መታደግ ይገባል ሲሉ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር፤ ኢ/ር) ገለጹ።

ወርቁ ጋቸና ( ዶ/ር፤ኢ/ር) ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዕድሎች በአግባቡ በመጠቀም ወደ ዲጂታላይዜሽን ለመሸጋገር በትብብር መሥራት ይገባል።

በተለይ አገልግሎት አሰጣጥን በቴክኖሎጂ በመደገፍ ጊዜና ሀብትን ከብክነት መታደግ ያስፈልጋል።

ኢትዮጵያ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ካደጉ ሀገራት ተርታ....

https://press.et/?p=133107
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት‼️

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም የፖሊሲ መግለጫ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሬ አስታዳደር ሥርዓት ማሻሻያ አድርጓል።
13ቱ #የውጭ_ምንዛሪ ማሻሻያው ዐበይት አዳዲስ የፖሊሲ ለውጦች‼️

ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረገው የውጭ ምንዛሪ ማሻሻያ የሚከተሉትን 13 ዐበይት አዳዲስ የፖሊሲ ለውጦችን ያካትታል‼️

📌 1. የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ሥርዓቱ የውጭ ምንዛሪ ተመን በባንኮችና በደንበኞቻቸው መካከል ወደሚወስንበት የገበያ ሥርዓት ይሸጋገራል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሚና፣ ገበያውን በማረጋጋት ላይ ያተኮረ ይሆናል፡፡

📌 2. የውጭ ምንዛሪን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የማስተላለፍ ግዴታ ቀሪ ሆኗል፡፡ በመሆኑም፣ ላኪዎችና ንግድ ባንኮች ያፈሩትን የውጭ ምንዛሪ ለራሳቸው ማስቀረት ይችላሉይህም ለግሉ ዘርፍ የሚሰጠውን የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት በእጅጉ ያሻሽላል፡፡

📌 3. ቀደም ሲል በ38 የገቢ ንግድ ሸቀጦች ላይ ተጥሎ የነበረው እግድ ተነሥቷል፡፡ ወደ ውጭ የሚደረግ የካፒታል ሂሳብ ፍሰት እንደ በፊቱ የተገደበ ቢሆንም፣ የውጭ ምንዛሪ ገበያው ለገቢ ሸቀጦችና አገልግሎቶች ነጻ ሆኗል፡፡

📌 4. ምርቶችን ወደ ውጭ የሚልኩ ነጋዴዎች ካፈሩት የውጭ ምንዛሪ ገቢ ለራሳቸው ያስቀሩት የነበረው 40 በመቶ ወደ 50 በመቶ ብሏል፡፡

📌 5. ቀደም ሲል ባንኮች ለተለያዩ ገቢ ሸቀጦች የሚጠቀሙበት የውጭ ምንዛሪ አሠራርና አደላደል ደንቦች ቀሪ ሆነዋል፡፡

📌 6. አሁን በሥራ ካሉና በባንኮች ከተቋቋሙ የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች (Forex Bureaus) በተጨማሪ ባንክ ያልሆኑ የግል የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች ይቋቋማሉ፡፡ ለእነዚህ ባንክ ላልሆኑ የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎችም በገበያ ዋጋ የውጭ ምንዛሪ ጥሬ ገንዘብ እንዲገዙና እንዲሸጡ የሥራ ፈቃድ ይሰጣቸዋል፡፡

📌 7. ሸቀጦችን በፍራንኮ ቫሉታ ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት ረገድ የተጣሉ ክልከላዎች ለማንሳት በቅርብ ጊዜ የማሻሻያ ደንብ ይወጣል፡፡

📌 8. በውጭ ተቋማት፣ በውጭ ኢንቨስተሮች እና በትውልደ ኢትዮጵያውያን (በዳያስፖራዎች) የተከፈቱ የውጭ ምንዛሪ ሂሳቦችን አስተዳደር የሚመለከቱ በርካታ ሕጎች እንዲላሉ ተደርጓል፡፡

📌 9. በኢትዮጵያ ውስጥ ነዋሪ የሆኑ ሰዎች ከውጭ የሚላክላቸውን ሐዋላ፣ በውጭ ምንዛሪ የሚከፈል ደሞዝን/የኪራይ ገቢን እና ሌሎች ገቢዎችን የሚያስቀምጡባቸውን የውጭ ምንዛሪ ሂሳቦች እንዲከፍቱ፣ እንዲሁም እነዚህን የውጭ ምንዛሪ ሂሳቦች ተጠቅመው የውጭ አገልግሎት ክፍያዎችን እንዲፈጽሙ ተፈቅዷል፡፡

📌 10.ቀደም ሲል የግል ኩባንያዎች ወይም ባንኮች በሚወስዷቸው የውጭ ብድሮች ላይ ይከፍሉት የነበረው የወለድ ተመን ጣሪያ ተነሥቷል፡፡

📌 11. መመዘኛውን የሚያሟሉ የውጭ ኢንቨስተሮች በኢትዮጵያ ስነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ (Ethiopian Securities Exchange) እንዲሳተፉ ተፈቅዷል፡፡

📌 12. በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ውስጥ የሚሠሩ ኩባንያዎች የውጭ ምንዛሪ ገቢያቸውን ሙሉ በሙሉ ለራሳቸው መያዝን ጨምሮ ልዩ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀም መብት ተሰጥቷቸዋል፡፡

📌 13. ከኢትዮጵያ ወደ ውጭ ሀገራት የሚጓዙ ወይም ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ መንገደኞች ሊይዙ በሚገባ የውጭ ምንዛሪ ጥሬ ገንዘብ መጠን ላይ ተጥለው የነበሩ የተለያዩ ጥብቅ ደንቦች እንዲላሉ ተደርጓል፡፡

ሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም
👍1
የአንድ አንድ አገራት ገንዘብ የእለቱ የምንዛሬ ዋጋ‼️
የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ሥርዓት ማሻሻያው ፋይዳዎች‼️
#የውጭ_ምንዛሪ አስተዳደር ሥርዓት ማሻሻያ‼️

በገበያ ወደሚወሰን የውጭ ምንዛሪ ሥርዓት መሸጋገር የሚያስገኛቸው ኢኮኖሚያዊ ፋይዳዎች፤

👉 የውጭ ምንዛሪ ገቢ በሚያስገኙ ዘርፎች የተሠማሩ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ይጠቅማል፣

👉 የሀገሪቱ የውጭ ምንዛሪ ገቢ ለነዋሪዎችና ለአምራች ዘርፎች ጥቅም መዋሉን ለማረጋገጥ ይረዳል፣

👉 በኢኮኖሚው ውስጥ ኢ-መደበኛነትንና ሕገ ወጥነትን ሲያበረታቱ የቆዩ በርካታ የንግድ አሠራሮችን ለማስቀረት ይረዳል፣

👉 ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ የሚያመርቱ ኢንዱስትሪዎችን ያበረታታል፣

👉 የግሉን ዘርፍ ለማሳደግና የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ለማዘመን ያግዛል፣

👉 ኢኮኖሚውን ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት ለማድረግ የተወሰዱ የማሻሻያ እርምጃዎችን የሚያጠናክር ይሆናል፤

👉 የውጭ ኢንቨስተሮችን በመሳብ፣ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን በማሳደግ፣ የንግድ ሥርዓታችንን ከአጎራባችና ከአቻ ሀገራት ጋር የተጣጣመ እንዲሆን በማድረግ ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል፣

ኢትዮጵያ በትናንትናው ዕለት መንግሥት አጠቃላይ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራምን አስመልክቶ የሰጠውን መግለጫ ተከትሎ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በዛሬው ዕለት የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ሥርዓት ማሻሻሉ ይታወሳል።

ሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓም
ዲያስፖራው ከሃምሳ አራት ሚሊዮን ብር በላይ ለፅዱና ለአረንጓዴ ዐሻራ አስተዋፅዖ አድርጓል
*****
(ኢ ፕ ድ)

ዲያስፖራው ከሃምሳ አራት ሚሊዮን ብር በላይ በማዋጣት በፅዱ እና አረንጓዴ ዐሻራ ተሳትፎ ማድረጉን የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አገልግሎት አስታወቀ::

የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር አቶ አባይነህ አቅናው ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳሉት፤ ዲያስፖራው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባደረጉት ጥሪ መሠረት ከሠላሳ ሁለት ሚሊዮን ብር በላይ ለፅዱ ጎዳና እና አረንጓዴ መርሐ ግብር መዋጮ አድርጓል:: ሃያ ሁለት ሚሊዮን ብር የሚገመት ብር ወጪ በማድረግ አስራ አምስት መፀዳጃ ቤቶችን ለመሥራት ቃል ተገብቷል::

የዲያስፖራው በተደራጀ መንገድ ያለውን ክህሎት፣ ዕውቀት እና ቴክኖሎጂ ወደ ሀገሩ በመምጣት አስተዋፅዖ እንዲያደርግ የበኩሉን እንዲወጣ የማሳተፍ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን አመልክተዋል:: እስከ አሁን ተስፋ ቴክ ኤንድ ሰርቭ ፎር አርቲካል የሚባል የቴክኖሎጂ ካምፓኒ በየጊዜው እየመጣ ሰዎችን በቴክኖሎጂ ዘርፍ ሥልጠና ይሰጣል፤ እንዲሁም ብራይት ኦፍ ቴክኖሎጂ የሚባል ካምፓኒ በቋሚነት በሚባል ደረጃ የተለያዩ የቴክኖሎጂ ልምምዶች እየሰጠ.....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=133184
👍1
በቀጣይ አራት ዓመታት ምን ይጠበቃል⁉️

👉 የኢትዮጵያ ኢከኖሚ በአማካይ በ8 በመቶ ያህል ያድጋል፤

👉 የዋጋ ንረት ወደ 10 በመቶ የተጠጋ ይሆናል፤

👉 የታክስ ገቢ ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ያለው ድርሻ 11 በመቶ ይደርሳል፣

👉 የመንግሥት ዕዳ ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ያለው ድርሻ ወደ 35 በመቶ ዝቅ ይላል፤

👉 የወጪና የገቢ ንግድ ዋጋ ወደ 20 ቢሊዮን ዶላር ያድጋል፤

👉 ቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንት ወደ 8 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ይላል፤

👉 ዓለም አቀፍ የመጠባበቂያ ክምችት ከ10 ቢሊዮን ዶላር በላይ ይሆናል፣
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት‼️

የሉሲ(ድንቅነሽ) ግኝት የሳይንሱን ማኅበረሰብ ብሎም መላውን አለም ስለምድራችን እና ስላሳለፈችው የሕይወት መልክ ለማወቅ ያስቻለ መሥራች ሁነት ነበር። ግኝቱ ብዙ ጥያቄዎችን የመለሰ ብዙ አዳዲስ ጥያቄዎችን ያነሳሳ ሲሆን በጥያቄዎቹም ለብዙ ምርምሮች መነሻ መሆኑ እስከዛሬ እንደቀጠለ ነው።

ሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓም