Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
40K photos
301 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እስካሁን የ231 ዜጎችን ሕይወት እንደቀጠፈ በተረጋገጠው የጎፋ ዞን የመሬት መንሸራተት አደጋ የተጎዱ ቤተሰቦችና ማኅበረሰብ በአካል ለማፅናናት በስፍራው ተገኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ከቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ፣ ከቀድሞ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አባዱላ ገመዳ እንዲሁም ከሌሎች ከፍተኛ የፌደራል መንግሥት አመራሮች ጋር በስፍራው ሲገኙ በክልል ሃላፊዎች እና በማህበረሰቡ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ሐምሌ 20 ቀን 2016 ዓ.ም
የጎርጎራ ፕሮጀክት ለሀገር የሀብት ምንጭ መሆን በሚችል መልኩ ተሠርቷል
*********
(ኢ.ፕ.ድ)
ጣናን ተንተርሶ የተሠራው የጎርጎራ ፕሮጀክት ለሀገርና ለአካባቢው ሕዝብ የገቢ ምንጭ መሆን በሚችል መልኩ ተሠርቷል ሲሉ የአማራ ክልል የኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ መንገሻ ፈንታው (ዶ/ር) ገለጹ።

የአማራ ክልል የኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ መንገሻ ፈንታው (ዶ/ር) ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፡- ጣናን ተንተርሶ የተሠራው የጎርጎራ ፕሮጀክት ለአካባቢው ሕዝብና ለሀገር ከፍተኛ የሆነ የሀብት ምንጭ መሆን በሚችል መልኩ ተሠርቷል።

በገበታ ለሀገር ፕሮጀክት ተካተው በሀገሪቱ ከተሠሩ ፕሮጀክቶች የጎርጎራ ፕሮጀክት በጥራቱ፣ በውበቱ፣ በስፋቱ፣ ባሉት ፀጋዎች አንዱ ነው ያሉት ኃላፊው፤ ፕሮጀክቱ ጣናን....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=133112
ከስሀላ ሰየምት ወደ ዝቋላ በጀልባ ተሳፍረው ሲጎዙ የነበሩ 19 ሰዎች ሕይወት አለፈ
**************
(ኢ.ፕ.ድ)
ትናንት ከቀኑ 6፡00 ገዳማ ከዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ስሃላ ሰየምት ወረዳ ወደ ዝቋላ ወረዳ በተከዜ ወንዝ በጀልባ ሲጎዙ ከነበሩት በግምት 26 ሰዎች ውስጥ 19 የሚደርሱ ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉን የስሃላ ሰየምት ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪ ሲሳይ ብሩ ገልጸዋል።

ከ26ቱ ሰዎች አንድ ሕጻንን ጨምሮ 7 ሰዎች በአስቸጋሪ ሁኔታ ሕይወታቸው ተርፏል ያሉት አቶ ሲሳይ የሟቾቹ ቁጥር ከዚያ በላይ ሊኾን ይችላል ብለዋል።

አደጋው ከደረሰ በኋላ የሟቾችን አስከሬን ለመፈለግ በተደረገው ጥረት እስከ ዛሬ ድረስ ሁለት ሰዎች ብቻ አስከሬን መገኘቱን ተናግረዋል።

ዋና አሥተዳዳሪው ሕይወቱ የተረፈው አንድ ሕጻን ከፍተኛ ጉዳት ስላስተናገደ ወደ ሰቆጣ ተፈራ ኃይሉ መታሰብያ ጠቅላላ ሆስፒታል ሲላክ የተቀሩት ስድስቱ መሸሀ ጤና ጣብያ ገብተው የህክምና ክትትል እየተደረገባቸው ነው ብለዋል።

ከአራት ዓመታት በላይ ከጥቅም ውጭ የኾነው እና እስከ ሰኔ ወር መጨረሻዎች ድረስ ይጠናቀቃል ተብሎ የነበረው ከስሃላ - ዝቋላ የሚያገናኘው የተከዜ የብረት ድልድይ በተያዘለት ጊዜ አለመጠናቀቁ የሰው ሕይወት መቅጠፉን እንዲቀጥል ምክንያት መኾኑን አቶ ሲሳይ ለአሚኮ ተናግረዋል።

ሐምሌ 21 ቀን 2016 ዓ.ም
አምስት ሚሊዮን ዜጎችን የንፁሕ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዷል
*********
(ኢ.ፕ.ድ)
በ2017 በጀት ዓመት ከአምስት ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያንን የንፁሕ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ለማድረግ መታቀዱን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጅነር ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ በ2017 በጀት ዓመት አጠቃላይ የመጠጥ ውሃ ተጠቃሚ የሆነ ሕዝብ ብዛትን ከነበረበት 74 ሚሊዮን 661 ሺህ 037 ወደ 80 ሚሊዮን ለማሳደግ ታቅዷል።

በዚህም ከአምስት ሚሊዮን በላይ ዜጎች የንፁሕ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት ይሠራል።
በ2017 በጀት ዓመት አጠቃላይ የመጠጥ ውሃ ተጠቃሚ የሆነ የገጠር ሕዝብ ብዛትን ከነበረበት 54 ነጥብ ዘጠኝ...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=133108
“አገልግሎት አሰጣጥን በቴክኖሎጂ በመደገፍ ጊዜና ሀብትን ከብክነት መታደግ ይገባል”
ወርቁ ጋቸና
የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር
***********
(ኢ.ፕ.ድ)
አገልግሎት አሰጣጥና መረጃ አያያዝን በቴክኖሎጂ በመደገፍ የሀገሪቱን ጊዜና ሀብት ከብክነት መታደግ ይገባል ሲሉ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር፤ ኢ/ር) ገለጹ።

ወርቁ ጋቸና ( ዶ/ር፤ኢ/ር) ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዕድሎች በአግባቡ በመጠቀም ወደ ዲጂታላይዜሽን ለመሸጋገር በትብብር መሥራት ይገባል።

በተለይ አገልግሎት አሰጣጥን በቴክኖሎጂ በመደገፍ ጊዜና ሀብትን ከብክነት መታደግ ያስፈልጋል።

ኢትዮጵያ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ካደጉ ሀገራት ተርታ....

https://press.et/?p=133107
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት‼️

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም የፖሊሲ መግለጫ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሬ አስታዳደር ሥርዓት ማሻሻያ አድርጓል።
13ቱ #የውጭ_ምንዛሪ ማሻሻያው ዐበይት አዳዲስ የፖሊሲ ለውጦች‼️

ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረገው የውጭ ምንዛሪ ማሻሻያ የሚከተሉትን 13 ዐበይት አዳዲስ የፖሊሲ ለውጦችን ያካትታል‼️

📌 1. የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ሥርዓቱ የውጭ ምንዛሪ ተመን በባንኮችና በደንበኞቻቸው መካከል ወደሚወስንበት የገበያ ሥርዓት ይሸጋገራል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሚና፣ ገበያውን በማረጋጋት ላይ ያተኮረ ይሆናል፡፡

📌 2. የውጭ ምንዛሪን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የማስተላለፍ ግዴታ ቀሪ ሆኗል፡፡ በመሆኑም፣ ላኪዎችና ንግድ ባንኮች ያፈሩትን የውጭ ምንዛሪ ለራሳቸው ማስቀረት ይችላሉይህም ለግሉ ዘርፍ የሚሰጠውን የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት በእጅጉ ያሻሽላል፡፡

📌 3. ቀደም ሲል በ38 የገቢ ንግድ ሸቀጦች ላይ ተጥሎ የነበረው እግድ ተነሥቷል፡፡ ወደ ውጭ የሚደረግ የካፒታል ሂሳብ ፍሰት እንደ በፊቱ የተገደበ ቢሆንም፣ የውጭ ምንዛሪ ገበያው ለገቢ ሸቀጦችና አገልግሎቶች ነጻ ሆኗል፡፡

📌 4. ምርቶችን ወደ ውጭ የሚልኩ ነጋዴዎች ካፈሩት የውጭ ምንዛሪ ገቢ ለራሳቸው ያስቀሩት የነበረው 40 በመቶ ወደ 50 በመቶ ብሏል፡፡

📌 5. ቀደም ሲል ባንኮች ለተለያዩ ገቢ ሸቀጦች የሚጠቀሙበት የውጭ ምንዛሪ አሠራርና አደላደል ደንቦች ቀሪ ሆነዋል፡፡

📌 6. አሁን በሥራ ካሉና በባንኮች ከተቋቋሙ የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች (Forex Bureaus) በተጨማሪ ባንክ ያልሆኑ የግል የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች ይቋቋማሉ፡፡ ለእነዚህ ባንክ ላልሆኑ የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎችም በገበያ ዋጋ የውጭ ምንዛሪ ጥሬ ገንዘብ እንዲገዙና እንዲሸጡ የሥራ ፈቃድ ይሰጣቸዋል፡፡

📌 7. ሸቀጦችን በፍራንኮ ቫሉታ ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት ረገድ የተጣሉ ክልከላዎች ለማንሳት በቅርብ ጊዜ የማሻሻያ ደንብ ይወጣል፡፡

📌 8. በውጭ ተቋማት፣ በውጭ ኢንቨስተሮች እና በትውልደ ኢትዮጵያውያን (በዳያስፖራዎች) የተከፈቱ የውጭ ምንዛሪ ሂሳቦችን አስተዳደር የሚመለከቱ በርካታ ሕጎች እንዲላሉ ተደርጓል፡፡

📌 9. በኢትዮጵያ ውስጥ ነዋሪ የሆኑ ሰዎች ከውጭ የሚላክላቸውን ሐዋላ፣ በውጭ ምንዛሪ የሚከፈል ደሞዝን/የኪራይ ገቢን እና ሌሎች ገቢዎችን የሚያስቀምጡባቸውን የውጭ ምንዛሪ ሂሳቦች እንዲከፍቱ፣ እንዲሁም እነዚህን የውጭ ምንዛሪ ሂሳቦች ተጠቅመው የውጭ አገልግሎት ክፍያዎችን እንዲፈጽሙ ተፈቅዷል፡፡

📌 10.ቀደም ሲል የግል ኩባንያዎች ወይም ባንኮች በሚወስዷቸው የውጭ ብድሮች ላይ ይከፍሉት የነበረው የወለድ ተመን ጣሪያ ተነሥቷል፡፡

📌 11. መመዘኛውን የሚያሟሉ የውጭ ኢንቨስተሮች በኢትዮጵያ ስነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ (Ethiopian Securities Exchange) እንዲሳተፉ ተፈቅዷል፡፡

📌 12. በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ውስጥ የሚሠሩ ኩባንያዎች የውጭ ምንዛሪ ገቢያቸውን ሙሉ በሙሉ ለራሳቸው መያዝን ጨምሮ ልዩ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀም መብት ተሰጥቷቸዋል፡፡

📌 13. ከኢትዮጵያ ወደ ውጭ ሀገራት የሚጓዙ ወይም ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ መንገደኞች ሊይዙ በሚገባ የውጭ ምንዛሪ ጥሬ ገንዘብ መጠን ላይ ተጥለው የነበሩ የተለያዩ ጥብቅ ደንቦች እንዲላሉ ተደርጓል፡፡

ሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም
👍1
የአንድ አንድ አገራት ገንዘብ የእለቱ የምንዛሬ ዋጋ‼️