ማርሽ ቀያሪው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ
********************
(ኢ ፕ ድ)
መንግሥት አጠቃላይ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራምን አስመልክቶ ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ሥርዓት ማሻሻሉን አስታውቋል።
ከትናንት ጀምሮ ሥራ ላይ የዋለው ይህ ማሻሻያ ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ ልማትን ከማረጋገጥ እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ከማድረግ አኳያ ምን ፋይዳ ይኖረዋል?
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ሰነድ እንደሚያትተው፤ እስካሁን የነበረው የውጭ ምንዛሪ ሥርዓት የተረጋጋ የውጭ ምንዛሪ ተመንና ዝቅተኛ የዋጋ ንረት መኖሩን ለማረጋገጥ የታለመ ቢሆንም፣ በሂደት ግን ለጥቁር ገበያ መስፋፋት፣ ለከፍተኛ የዋጋ ንረት፣ በከበሩ ማዕድናት ለሚደረግ ሰፊ የኮንትሮባንድ ንግድ እንዲሁም የውጭ ምንዛሪ ከባንክ ሥርዓት ውጭ እንዲሆንና ከሀገር እንዲሸሽ አንዱና ዋነኛ ምክንያት ሆኗል።
ይህ ሁሉ ከአምራች ዘርፎች ይልቅ ጥቂት ሕገወጦችና ደላሎች ተጠቃሚ እንዲሆኑና ሥር የሰደደ የውጭ ምንዛሪ እጥረት እንዲከሰት አድርጓል።
በዚህ የተነሣ በርካታ የንግድ ድርጅቶችና ባለሀብቶች ተጎጂ ሆነዋል፤ የወጪ ንግድንና የፋብሪካ ምርቶችን ለማስፋፋት፣ የውጭ ኢንቨስትመንትን ለመሳብና የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሪ ክምችት ለማሳደግ የተቀመጡ.......
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=133251

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መልዕክት‼️
በጎንደር ከተማ የፋሲል ቤተመንግስት እድሳት ተጀምሯል። በጣም ጥሩ ሁኔታ ላይም ይገኛል። በአጭር ጊዜ ውስጥ ፋሲልን ወደ ቀደመ ግርማ ሞገሱ እንመልሰዋለን።

በቢሾፍቱ የሚገነባውን ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በ18 ወራት ለማጠናቀቅ ታቅዷል
***************************
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቢሾፍቱ የሚገነባውን ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በሚቀጥሉት 18 ወራት ለማጠናቀቅ ማቀዱን አስታወቀ።
በአየር መንገዱ ላይ የቀረቡት ክሶች መሠረተ ቢስ መሆናቸውንም አስታውቋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው የ2016 በጀት ዓመት አፈጻጸምን አስመልክተው ትናንት በሰጡት መግለጫ፣ የቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ላለፉት በርካታ ዓመታት ማስፋፊያ እየተደረገለት ቢቆይም እየጨመረ የመጣውን ዓለም አቀፍ መንገደኛ ማስተናገድ ወደማይችልበት ደረጃ እየደረሰ ነው።
ይህን ችግር በዘላቂነት ለመፍታትም አየር መንገዱ በቢሾፍቱ ተጨማሪ አየር ማረፊያ ለመገንባት እየሠራ ነው።
እንደ ሥራ አስፈጻሚው ገለጻ፣ ተጨማሪ አየር ማረፊያው የሚገነባው ቢሾፍቱ አካባቢ ሲሆን አየር ማረፊያውን ዲዛይን የሚያደርግ ዓለም አቀፍ ተቋራጭ ተመርጧል። ዲዛይኑንና ግንባታውን የሚሠሩት ሥራ ተቋራጮች በሚቀጥሉት 18 ወራት እንዲያጠናቅቁ ስምምነት ላይ ተደርሶ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ተጀምሯል።
አየር ማረፊያው የሚገነባበት ቦታ ላይ ያረፉትን አርሶ አደሮች ወደ ሌላ ቦታ ለማዘዋወር የሚያስችል ቦታ በቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ተለይቶልናል ያሉት አቶ መስፍን፣ የተለየው ቦታ ላይ ኑሯቸውን የሚመሩበት መኖሪያ ቤት.....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=133253

የወንጀል መከላከል፣ የምርመራና የመረጃ አሰባሰብ አሰራሮች በቴክኖሎጂ በታገዘ መንገድ እየተከናወኑ ይገኛሉ
********************
(ኢ ፕ ድ)
የወንጀል መከላከል፣ የምርመራና የመረጃ አሰባሰብ አሰራሮች በቴክኖሎጂ በታገዘ መንገድ እያከናወነ መሆኑን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ።
በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ የኦፕሬሽን ምክትል ዋና መምሪያ ኃላፊ ሙሊሳ አብዲሳ፤ በወንጀል መከላከልና በምርመራ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በተመለከተ ከኢዜአ ጋር ቆይታ አድርገዋል።
በወንጀል ምርመራና በመከላከል ረገድም በቴክኖሎጂ የተደገፉ ቀልጣፋና ዘመናዊ አሰራሮች በስፋት እየተተገበሩ መሆኑን ገልጸዋል።
የፖሊስና ህብረተሰቡ የወንጀል መከላከል ጠንካራ ቁርኝትም ሌላ ተጨማሪ እድል መሆኑን ጠቅሰው በዚሁ ቅንጅታዊ አሰራር ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት ተችሏል ብለዋል።
በአዲስ አበባ የተለያዩ የወንጀል ሙከራዎችን በማክሸፍ አጥፊዎችንም በፍጥነት በቁጥጥር ስር አውሎ ለህግ ማቀረብ የተቻለው በፖሊስና ህብረተሰቡ የተባበረ ስራ መሆኑን ተናግረዋል።
በወንጀል መከላከል፣ በምርመራና በመረጃ አሰባሰብ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዙ አሰራሮች በስፋት እየተተገበሩ መሆኑም የፖሊስን አሰራር ፈጣንና ዘመናዊ አድርጎታል ብለዋል።
በቀጣይነትም የፖሊስን አሰራር ይበልጥ የማዘመን ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ጠቅሰው የሕብረተሰቡም ትብብርና ተሳትፎ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
በወንጀል ተግባር ላይ የሚሰማሩ አካላትን በቁጥጥር ስር አውሎ በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ስራ በተጠናከረ መልኩ የሚቀጥል መሆኑንም ሃላፊው አረጋግጠዋል።
በሃሳብ የበላይነት በውይይትና በሰለጠነ መንገድ ችግሮችን በመፍታት ዘላቂ ሰላም ማምጣት የሁሉም ሃላፊነት ሊሆን እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት‼️
የፀሀፊን መንፈስ የሚያድሱ ሀይቆች፣ የተፈጥሮን ዚቅ አድምጦ ጥዑም ዜማ ለመቀመር የሚያስችል ድንቅ መልክዓ ምድር፣ የተፈጥሮን ስክነት ማሳያ ስፍራ፣ የውሀዋ ከተማ ቢሾፍቱ።
የምትተክል ሀገር፣ የሚያጸና ትውልድ" በሚል መሪ ቃል የጀመርነውን የዘንድሮውን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐግብር በቢሾፍቱም ቀጥለናል፡፡ በአረንጓዴ ዐሻራ ለአካባቢ ተስማሚ የሆኑ ተነሳሽነቶችን በማስተዋወቅ ለመጪው ትውልድ አረንጓዴ ተፈጥሮና ጤናማ ምድርን እናስረክባለን፡፡
ሐምሌ 23 ቀን 2016 ዓም

በአጥር መደርመስ ምክንያት በደረሰ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን ፖሊስ ገልፀ
*******************
(ኢ ፕ ድ)
በድሬዳዋ ከተማ ወረዳ 4 በተለምዶ ገንደቦዬ ጋራ ላይ እየተባለ በሚጠራው አካበቢ በአጥር መደርመስ ምክንያት በአራት ግለሰቦች ላይ በደረሰ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን ፖሊስ ገልፀ።
የግለሰብ ቤት ተከራይተው የሚኖሩ የድሬዳዋ መምህራን ኮሌጅ የክረምት ተማሪዎች ላይ የጎረቤት አጥር ተደርምሶ የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉንና ሁለት ተጎጂዎች በድልጮራ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ አየተደረገላቸው መሆኑን በድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የወንጀል ምርመራ የታክቲክ ዳሬክቶሬት ኮማንደር መሀመድ ኢብራሂም ገልፀፀዋል።
ሰሞኑን በተደጋጋሚ እየጣለ የሚገኘው ዝናብ ጋር በተያያዘ በጋራ ላይ ሚገኙ መኖሪያ ቤቶች መሰል አደጋዎች እንዳይከሰቱ ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ጉዳቱ በደረሰበት አካባቢ የሚኖሩ ቤተሰቦች ለአደጋ እንዳይጋለጡ ጊዜያዊ ማረፊያ ቦታ መሰጠቱን የከተማዋ ኮሙዩኒኬሽን መረጃ ያመለክታል።