በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን፣ ገዜ ጎፋ ወረዳ፣ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ ሐምሌ 15 ቀን 2016 ዓ.ም በደረሰዉ የመሬት መንሸራተት አደጋ ህይወታቸዉ ላጡ ወገኖች የሻማ ማብራት ስነ-ስርዓት በጎፋ ዞን ሳዉላ ከተማ ተካሄደ።
ሐምሌ 2 ቀን 2016 ዓም
ሐምሌ 2 ቀን 2016 ዓም
የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት ለኢትዮጵያ የ3 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር ብድር አጸደቀ
**-
(ኢ.ፕ.ድ)
የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት አስፍጻሚ ቦርድ ለኢትዮጵያ ለአራት ዓመት የ3 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር የተራዘመ ብድር አገልግሎት አቅርቦትን አጽድቋል፡፡
አይ ኤም ኤፍ ጉዳዩን አስመልክቶ ያወጣው መግለጫ ሙሉ ቃል...!!
የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት አስፈጻሚ ቦርድ ለኢትዮጵያ የሚሆንና መጠኑም 2.556 ቢሊየን SDR (የኮታው 850% ወይም ወደ 3.4 ቢሊየን ዶላር የሚጠጋ) የሆነ፤ የማክሮ ኢኮኖሚ ሚዛን መፋለስን መፍታትን እና በግል ዘርፉ ለሚመራ እድገት መሠረት መጣልን አላማው ያደረገውን የመንግሥትን የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ አፈጻጸም የሚደግፍ የአራት ዓመት የተራዘመ የብድር አገልግሎት አቅርቦት(ECF) አጽድቋል።
የአስፈጻሚ ቦርዱ ውሳኔም ኢትዮጵያ ከባላንስ ኦፍ ፓይመንት ጋር የተያያዙ ፍላጎቶቿን እንድታሟላ የሚረዳትን እንዲሁም በጀቷን የሚደግፈውን የ766.75 ሚሊየን SDR ወይም 1 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር አካባቢ የሚሆን ገንዘብ ክፍያ ወዲያውኑ እንዲለቀቅ የሚያስችል ይሆናል።
በአራት ዓመቱ የተራዘመ የብድር አገልግሎት አቅርቦት የሚደገፈው የመንግሥት የኢኮኖሚ ፕሮግራም የግል ዘርፉን እንቅስቃሴ የሚያነቃቃ ሁለገብ የፖሊሲ ፓኬጅን እንዲሁም የላቀ እና በይበልጥ አካታች የሆነ እድገትን ማምጣትይቻል ዘንድ ኢኮኖሚውን ክፍት ማድረግን ኢላማው ያደረገ ነው።
ማሻሻያው ተጋላጭ በሆኑ ቤተሰቦች/አባዎራዎች ላይ የሚኖረውን ተጽእኖ ለማለዘብ ይቻል ዘንድ የማህበራዊ ሴፍቲ ኔቶችን ማጠናከርም የመንግሥት የማሻሻያ ፕሮግራም አንድ ወሳኝ ክፍለአካል ነው። ቁልፍ የሚባሉት ፖሊሲዎችም የሚከተሉትን ያካትታሉ፡
1) ውጫዊ ኢሚዛናዊንትን ለመፍታት እና የውጭ ምንዛሪ እጥረትን ለማስታገስ በገበያ ወደሚወሰን የምንዛሪ ዋጋ መሄድ፤
2) የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፍን በማዘመን የዋጋ ግሽበትን መዋጋት፤
3) የሀገር ውስጥ የገንዘብ ምንጮችን በማሰባብሰብ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ሕዝባዊ ወጪዎች ማዋል፤
4) ከውጪአበዳሪዎች ጋር የሚደረጉ ወቅታዊ የእዳ ሪስትረክቸሪንግ ስምምነቶችን በመፈጸም ጭምር የእዳ አከፋፈል ዘላቂነትን መመለስ እንዲሁም
5) ወሳኝ የሆኑ የማክሮ ፋይናንሺያል ተጋላጭነቶችን ለመቀነስ የመንግሥት ኢንተርፕራይዞችን የገንዘብ አቋም ማጠናከር።
ፕሮግራሙ ከልማት አጋሮች የሚገኝ ተጨማሪ የገንዘብ አቅርቦትን በማፋጠን እንዲሁም በመካሄድ ላይ ያለው የእዳ ሪስትረክቸሪንግ በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የሚያደርግ ማዕቀፍ በመስጠት ረገድ እንደሚያግዝ ይጠበቃል።

ከ7 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ብሄራዊ መታወቂያ ለመውሰድ ተመዝግበዋል
******
(ኢ ፕ ድ)
በኢትዮጵያ ብሄራዊ መታወቂያ ለመውሰድ የተመዘገቡ ሰዎች ቁጥር ከ7 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ መድረሱን የኢትዮጵያ ብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም አስታወቀ። በ364 የምዝገባ ጣቢያዎች አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑም ተገልጿል።
በኢትዮጵያ ብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ወ/ሪት ቃልኪዳን አብርሃም ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም በኢትዮጵያ የዲጂታል መታወቂያ ሥርዓትን በመዘርጋት ዜጎች እና ሕጋዊ ነዋሪዎች የመታወቅ መብታቸው እንዲረጋገጡ እና አገልግሎቶችን በተቀላጠፈ መንገድ ማግኘት እንዲችሉ የሚያደርግ ነው። በአሁኑ ጊዜም አገልግሎቱን ለሕዝቡ ተደራሽ ለማድረግ በ364 ጣቢያዎች ምዝገባ እየተካሄደ ይገኛል።
ብሄራዊ መታወቂያ አገልግሎቶችን በተቀላጠፈ መንገድ ማግኘት ከማስቻል ባለፈ በአገልግሎት ሰጪና ተቀባይ መካከል በሚኖር ግንኙነት ላይ እምነት እንዲዳብር፣ በግል እና በመንግሥት ተቋማት የማንነት ማረጋገጥ ሂደት በተቀላጠፈ መንገድ እንዲከናወን.....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=133254

በ2017 ጎንደር ከተማን
******
(ኢ ፕ ድ)
በ2017 ጎንደር ከተማን
የጎንደር ከተማ ከንቲባ አቶ ባዩህ አቡሀይ ለኢፕድ እንደገለጹት፤ በከተማዋ በተፈጠረው አንጻራዊ ሰላም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ማንሠራራት ጀምረዋል።
በከተማዋ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴውን ወደነበረበት ለመመለስ በርካታ ሥራዎች ተሠርተዋል ያሉት ከንቲባው በተያዘው በጀት አመትም ከተማዋን
እስካሁን በነበረው ሂደት መከላከያ ሠራዊት፣ የአካባቢው የጸጥታ ኃይልና ማህበረሰቡ በሰሩት የቅንጅት ሥራ በከተማዋ አንጻራዊ ሰላም ከመስፈኑም ባለፈ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ከነበሩበት ማንሠራራት እንደጀመሩ ተናግረዋል።
በአካባቢው በተፈጠሩ ችግሮች ከወልቃይትና በዙሪያው ካሉ አካባቢዎች የንግድ ትስስሩ ተስተጓጉሎ እንደነበር አስታውሰው፤ አሁን በተገኘው አንጻራዊ ሰላም ምርትና ሸቀጦች ወደ ከተማው እየገቡ በመሆኑ የከተማዋ የንግድ እንቅስቃሴ ከነበረበት......
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=133256
ስማርት ሲቲ ለማድረግና ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን እየተሠራ ነው******
(ኢ ፕ ድ)
በ2017 ጎንደር ከተማን
ስማርት ሲቲ ለማድረግ እና ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን እየተሠራ መሆኑን የከተማዋ ከንቲባ ተናገሩ። የጎንደር ከተማ ከንቲባ አቶ ባዩህ አቡሀይ ለኢፕድ እንደገለጹት፤ በከተማዋ በተፈጠረው አንጻራዊ ሰላም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ማንሠራራት ጀምረዋል።
በከተማዋ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴውን ወደነበረበት ለመመለስ በርካታ ሥራዎች ተሠርተዋል ያሉት ከንቲባው በተያዘው በጀት አመትም ከተማዋን
ስማርት ሲቲ ለማድረግ እና ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን እየተሠራ ነው ብለዋል። እስካሁን በነበረው ሂደት መከላከያ ሠራዊት፣ የአካባቢው የጸጥታ ኃይልና ማህበረሰቡ በሰሩት የቅንጅት ሥራ በከተማዋ አንጻራዊ ሰላም ከመስፈኑም ባለፈ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ከነበሩበት ማንሠራራት እንደጀመሩ ተናግረዋል።
በአካባቢው በተፈጠሩ ችግሮች ከወልቃይትና በዙሪያው ካሉ አካባቢዎች የንግድ ትስስሩ ተስተጓጉሎ እንደነበር አስታውሰው፤ አሁን በተገኘው አንጻራዊ ሰላም ምርትና ሸቀጦች ወደ ከተማው እየገቡ በመሆኑ የከተማዋ የንግድ እንቅስቃሴ ከነበረበት......
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=133256
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ለጎፋ ዞን አምሰት ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ
****************
(ኢ ፕ ድ)
በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጃዋር የተመራ ልዑክ በጎፋ ዞን በደረሰው ድንገተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች 5 ሚሊዬን ብር ድጋፍ አደረገ።
ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ለተደረገው ድጋፍ አመስግነው የፍቅር ተምሳሌት የሆነው የድሬዳዋ ህዝብ በሀዘናችን ሰዓት ከጎናችን ስለሆናችሁ ምስጋና ይገባችዋል ብለዋል።
ሁሉም ኢትዮጵያዊ በዘላቂነት ችግሩን ለመፍታት የሚያደርገውን ጥረት በመደገፍ ትብብሩን እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።
ድጋፉን ያስረከቡት የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጀዋር በአደጋው የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን በድሬዳዋ ህዝብ ስም ገልፀው ለተጎዱ ወገኖች መፅናናትን መመኘታቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት ገልጿል።
ሐምሌ 23 ቀን 2016 ዓም

ማርሽ ቀያሪው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ
********************
(ኢ ፕ ድ)
መንግሥት አጠቃላይ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራምን አስመልክቶ ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ሥርዓት ማሻሻሉን አስታውቋል።
ከትናንት ጀምሮ ሥራ ላይ የዋለው ይህ ማሻሻያ ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ ልማትን ከማረጋገጥ እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ከማድረግ አኳያ ምን ፋይዳ ይኖረዋል?
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ሰነድ እንደሚያትተው፤ እስካሁን የነበረው የውጭ ምንዛሪ ሥርዓት የተረጋጋ የውጭ ምንዛሪ ተመንና ዝቅተኛ የዋጋ ንረት መኖሩን ለማረጋገጥ የታለመ ቢሆንም፣ በሂደት ግን ለጥቁር ገበያ መስፋፋት፣ ለከፍተኛ የዋጋ ንረት፣ በከበሩ ማዕድናት ለሚደረግ ሰፊ የኮንትሮባንድ ንግድ እንዲሁም የውጭ ምንዛሪ ከባንክ ሥርዓት ውጭ እንዲሆንና ከሀገር እንዲሸሽ አንዱና ዋነኛ ምክንያት ሆኗል።
ይህ ሁሉ ከአምራች ዘርፎች ይልቅ ጥቂት ሕገወጦችና ደላሎች ተጠቃሚ እንዲሆኑና ሥር የሰደደ የውጭ ምንዛሪ እጥረት እንዲከሰት አድርጓል።
በዚህ የተነሣ በርካታ የንግድ ድርጅቶችና ባለሀብቶች ተጎጂ ሆነዋል፤ የወጪ ንግድንና የፋብሪካ ምርቶችን ለማስፋፋት፣ የውጭ ኢንቨስትመንትን ለመሳብና የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሪ ክምችት ለማሳደግ የተቀመጡ.......
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=133251

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መልዕክት‼️
በጎንደር ከተማ የፋሲል ቤተመንግስት እድሳት ተጀምሯል። በጣም ጥሩ ሁኔታ ላይም ይገኛል። በአጭር ጊዜ ውስጥ ፋሲልን ወደ ቀደመ ግርማ ሞገሱ እንመልሰዋለን።

በቢሾፍቱ የሚገነባውን ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በ18 ወራት ለማጠናቀቅ ታቅዷል
***************************
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቢሾፍቱ የሚገነባውን ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በሚቀጥሉት 18 ወራት ለማጠናቀቅ ማቀዱን አስታወቀ።
በአየር መንገዱ ላይ የቀረቡት ክሶች መሠረተ ቢስ መሆናቸውንም አስታውቋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው የ2016 በጀት ዓመት አፈጻጸምን አስመልክተው ትናንት በሰጡት መግለጫ፣ የቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ላለፉት በርካታ ዓመታት ማስፋፊያ እየተደረገለት ቢቆይም እየጨመረ የመጣውን ዓለም አቀፍ መንገደኛ ማስተናገድ ወደማይችልበት ደረጃ እየደረሰ ነው።
ይህን ችግር በዘላቂነት ለመፍታትም አየር መንገዱ በቢሾፍቱ ተጨማሪ አየር ማረፊያ ለመገንባት እየሠራ ነው።
እንደ ሥራ አስፈጻሚው ገለጻ፣ ተጨማሪ አየር ማረፊያው የሚገነባው ቢሾፍቱ አካባቢ ሲሆን አየር ማረፊያውን ዲዛይን የሚያደርግ ዓለም አቀፍ ተቋራጭ ተመርጧል። ዲዛይኑንና ግንባታውን የሚሠሩት ሥራ ተቋራጮች በሚቀጥሉት 18 ወራት እንዲያጠናቅቁ ስምምነት ላይ ተደርሶ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ተጀምሯል።
አየር ማረፊያው የሚገነባበት ቦታ ላይ ያረፉትን አርሶ አደሮች ወደ ሌላ ቦታ ለማዘዋወር የሚያስችል ቦታ በቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ተለይቶልናል ያሉት አቶ መስፍን፣ የተለየው ቦታ ላይ ኑሯቸውን የሚመሩበት መኖሪያ ቤት.....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=133253

የወንጀል መከላከል፣ የምርመራና የመረጃ አሰባሰብ አሰራሮች በቴክኖሎጂ በታገዘ መንገድ እየተከናወኑ ይገኛሉ
********************
(ኢ ፕ ድ)
የወንጀል መከላከል፣ የምርመራና የመረጃ አሰባሰብ አሰራሮች በቴክኖሎጂ በታገዘ መንገድ እያከናወነ መሆኑን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ።
በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ የኦፕሬሽን ምክትል ዋና መምሪያ ኃላፊ ሙሊሳ አብዲሳ፤ በወንጀል መከላከልና በምርመራ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በተመለከተ ከኢዜአ ጋር ቆይታ አድርገዋል።
በወንጀል ምርመራና በመከላከል ረገድም በቴክኖሎጂ የተደገፉ ቀልጣፋና ዘመናዊ አሰራሮች በስፋት እየተተገበሩ መሆኑን ገልጸዋል።
የፖሊስና ህብረተሰቡ የወንጀል መከላከል ጠንካራ ቁርኝትም ሌላ ተጨማሪ እድል መሆኑን ጠቅሰው በዚሁ ቅንጅታዊ አሰራር ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት ተችሏል ብለዋል።
በአዲስ አበባ የተለያዩ የወንጀል ሙከራዎችን በማክሸፍ አጥፊዎችንም በፍጥነት በቁጥጥር ስር አውሎ ለህግ ማቀረብ የተቻለው በፖሊስና ህብረተሰቡ የተባበረ ስራ መሆኑን ተናግረዋል።
በወንጀል መከላከል፣ በምርመራና በመረጃ አሰባሰብ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዙ አሰራሮች በስፋት እየተተገበሩ መሆኑም የፖሊስን አሰራር ፈጣንና ዘመናዊ አድርጎታል ብለዋል።
በቀጣይነትም የፖሊስን አሰራር ይበልጥ የማዘመን ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ጠቅሰው የሕብረተሰቡም ትብብርና ተሳትፎ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
በወንጀል ተግባር ላይ የሚሰማሩ አካላትን በቁጥጥር ስር አውሎ በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ስራ በተጠናከረ መልኩ የሚቀጥል መሆኑንም ሃላፊው አረጋግጠዋል።
በሃሳብ የበላይነት በውይይትና በሰለጠነ መንገድ ችግሮችን በመፍታት ዘላቂ ሰላም ማምጣት የሁሉም ሃላፊነት ሊሆን እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት‼️
የፀሀፊን መንፈስ የሚያድሱ ሀይቆች፣ የተፈጥሮን ዚቅ አድምጦ ጥዑም ዜማ ለመቀመር የሚያስችል ድንቅ መልክዓ ምድር፣ የተፈጥሮን ስክነት ማሳያ ስፍራ፣ የውሀዋ ከተማ ቢሾፍቱ።
የምትተክል ሀገር፣ የሚያጸና ትውልድ" በሚል መሪ ቃል የጀመርነውን የዘንድሮውን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐግብር በቢሾፍቱም ቀጥለናል፡፡ በአረንጓዴ ዐሻራ ለአካባቢ ተስማሚ የሆኑ ተነሳሽነቶችን በማስተዋወቅ ለመጪው ትውልድ አረንጓዴ ተፈጥሮና ጤናማ ምድርን እናስረክባለን፡፡