Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.76K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ኢትዮጵያና ኡጋንዳ በቀጣናዊ የደኅንነትና ጸጥታ ጉዳዮች በጋራ እያከናወኗቸው ባሉ የትብብር ሥራዎችን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታወቁ
*******
(ኢ ፕ ድ)

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት እና የኡጋንዳ የውጭ ደኅንነት ተቋማት በቀጣናዊ የደኅንነትና ጸጥታ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ እያከናወኗቸው ያሉ የትብብር ሥራዎችን በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ገምግመዋል፡፡

የኢትዮጵያና ኡጋንዳ የመረጃና ደኅንነት ተቋማት ቀደም ሲል በምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና የደኅንነትና የጸጥታ ስጋት የሆኑትን ሽብርተኝነት፣ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን፣ ሕገወጥ ታጣቂዎችንና ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል የደረሱትን የሁለትዮሽ ስምምነት በመተግበር የተገኙ ውጤቶችና ቀጣይ መጠናከር ባሉባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል።

በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት በኩል የውጭ መረጃ ዘርፍ ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ታዜር ገብረ እግዚአብሔር እንዲሁም በኡጋንዳ በኩል ደግሞ የውጭ ደኅንነት ተቋም ዳይሬክተር ጀነራል ጆሴፍ ኦኬሎ የጋራ ውይይቱን መርተዋል፡፡

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ታዜር ገብረ እግዚአብሔር ኡጋንዳ ቀጣናዊና አካባቢያዊ ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር በመሥራት ታሪካዊ ወዳጅ መሆኗን ገልፀው፤ የሀገሪቱ የውጭ አቻ የመረጃ ተቋም ከመረጃ ልውውጥና ከደኅንነት አኳያ ከአገልግሎት መሥሪያ ቤቱ ጋር የጀመረውን አጋርነት አጠናክሮ ለመቀጠል እያሳያ ያለው ቁርጠኝነት የሚደነቅ ነው ብለዋል፡፡

የኡጋንዳ የውጭ ደኅንነት ተቋም ዳይሬክተር ጀነራል ጆሴፍ ኦኬሎ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በጎረቤት ሀገራት እና በቀጣናው ዘለቂ ሰላም እንዲረጋገጥ እየሠራች መሆኑ፤ የሁለቱ ሀገራት የመረጃ ተቋማት ሕገወጦችን ተከታትለውና ለይተው ተጠያቂ በማድረግ ለዘላቂ ሰላም ምቹ መደላድል ለመፍጠር የጀመሩትን ትብብር አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል፡፡

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ለመገናኛ ብዙኃን በላከው መረጃ ፤ ሁለቱ አቻ የመረጃ ተቋማት የዛሬ ሁለት ዓመት በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸውን አስታውሷል፡፡

ሐምሌ 23 ቀን 2016 ዓም
የዓለም ባንክ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ማሻሻያ ለመደገፍ የሚውል ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ አጸደቀ
***
(ኢ.ፕ.ድ)

የዓለም ባንክ የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ዛሬ ባካሄደው ስብሰባው ኢትዮጵያ የጀመረችውን ዘላቂ እና ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲ ለመደገፍ የሚረዳ ውሳኔን አጽድቋል።

ባንኩ ዛሬ ማምሻውን ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረትም ከዓለም አቀፉ የልማት ማህበር የ1 ቢሊዮን ዶላር ዕርዳታና 500 ሚሊዮን ዶላር የብድር ድጋፍ ለኢትዮጵያ ለመስጠት ወስኗል።

ይህ ውሳኔ የኢትዮጵያ መንግስት ድህነት ቅነሳን ለማፋጠን እና ሁሉን አሳታፊና ዘላቂ የሆነ እድገትን ለማረጋገጥ በጀመረው እርምጃ ወቅት የተሰጠ ወሳኝ ድጋፍ መሆኑን ባንኩ አስታውቋል።

የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ትልቁ የልማት አጋር መሆኑን የጠቀሰው የባንኩ መግለጫ፤ ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በየአመቱ ከ2 ቢሊዮን ዶላር በላይ የገንዘብ ድጋፍ የምታገኝ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ግማሽ ያህሉ በእርዳታ መልክ የሚሰጥ መሆኑንም ገልጿል።

ሐምሌ 23 ቀን 2016 ዓ.ም
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት ‼️
በምስሎቹ የምንመለከተው በመልማት ላይ ያለ የሻይ ተክል ማሳ ነው። በቡና ያሳካነውን አመርቂ ድል በሻይ ምርትም እንደግመዋለን።
በትግራይ በውጭ ሀገራት ዜጎች ትብብር ወርቅ በሕገወጥ መንገድ እየወጣ ነው
***************
(ኢ ፕ ድ)
በትግራይ ክልል ከውጭ ሀገራት ዜጎች ጋር በመሆን በሕገወጥ መልኩ የወርቅ ማዕድን እየወጣ እንደሚገኝ የጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ጌታቸው ረዳ ተናገሩ፡፡ በክልሉ የሰፈነውን ሕገወጥነት ለመከላከል እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል።

የክልሉ ፕሬዚዳንት ለክልሉ መገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ እንዳሉት፤ በክልሉ ያለውን አለመረጋጋት በመጠቀም ከውጭ ኃይሎች ጋር በመተባበር የወርቅ ማዕድን በሕገወጥ መንገድ እየወጣ ይገኛል፡፡

የናይጄሪያ፣ የቻይና እና የሴኔጋል ዜጎች በሕገወጥ ሥራው ላይ የተሰማሩ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ የወርቅ ማዕድኑን ለማውጣት አደገኛ ኬሚካሎች ጥቅም ላይ እየዋሉ ይገኛል በተለይ ደግሞ ሳይናይድና ሜርኩሪ የተሰኙት ኬሚካሎቹ ደኖችና እንስሳት ላይ ጉዳት እያደረሱ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ወርቅ በተደራጀ መልኩ የሚያወጡ ሰዎች ኢኮኖሚውን ብቻ የሚጎዱ ሳይሆኑ የፀጥታ ችግርም እየተፈጠረ እንደሚገኝ …
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=133333
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በ38ኛ መደበኛ ስብሰባው የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳለፈ
**********
(ኢ.ፕ.ድ)

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 38ኛ መደበኛ ስብሰባው ዓለም ዐቀፍ የልማት ማህበር ጋር የተደረገውን የፋይናንስ ድጋፍ ስምምነት ለማፅደቅ በተዘጋጀው አዋጅ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

ከዓለም ዐቀፍ የልማት ማህበር ጋር የተደረገው የፋይናንስ ድጋፍ ስምምነት የ1.5 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚያስገኝ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 1 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በእርዳታ፣ 500 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ደግሞ በብድር መልክ የተገኘ ነው፡፡

የፋይናንስ ድጋፉ የኢትዮጵያ መንግሥት የማክሮ ኢኮኖሚውን ለማረጋጋት የጀመራቸውን የሪፎርም ሥራዎች ለማስፈጸም በተለይም ለሥራ ፈጠራ፣ የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር፣ የውጭ ምንዛሪ እጥረትን ለመቅረፍ፣ የመዋቅር ማስተካከያ ለማድረግ እንዲሁም የፌደራል መንግሥት የ2ዐ17 ዓ.ም በጀትን በቀጥታ ለመደገፍ የሚውል ነው፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሰነዱ ላይ ከተወያየ በኋላ ብድሩ ከወለድ ነፃ ፣ የ6 ዓመት የችሮታ ጊዜን ጨምሮ በ38 ዓመታት ውስጥ ተከፍሎ የሚጠናቀቅ እንዲሁም ከአገራችን የብድር አስተዳደር ስትራቴጂ ጋር የሚጣጣም መሆኑን በማረጋገጥ ስምምነቱን አጽድቆ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል።
ሐምሌ 24 ቀን 2016 ዓ.ም
ፖሊሲው የመንግሥትን የዕዳ ጫና እንዴት ይቀንሰዋል?
**************************
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያ ፈጣንና ተወዳዳሪ ኢኮኖሚን ለመገንባት የጀመረችውን የለውጥ ጉዞ የሚደግፍ አዲስ የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ሥርዓት ማሻሻያ ይፋ አድርጋለች፡፡

ፖሊሲው ይዞት ከሚመጣው ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች መካከልም የመንግሥት እዳ ጫና ቅነሳ አንዱ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡ ለመሆኑ አዲሱ ውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ሥርዓት የመንግሥትን ዕዳ ጫና በምን መልኩ ይቀንሰው ይሆን?

በፕላንና ልማት ሚኒስቴር የልማት እቅድና የመንግሥት ኢንቨስትመንት አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ በረከት ፍስሀጽዮን እንደሚሉት፤ ባለፉት ዓመታት ቀደም ብለው የነበሩ የማክሮ ኢኮኖሚ መዛባቶችን ለማረምና በኢኮኖሚው ያጋጠሙትን መዋቅራዊ ችግሮች ለመፍታት መጠነ ሰፊ የሆኑ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ተግባራዊ ሲደረጉ ቆይተዋል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ የ 10 ዓመት የልማት…
ሙሉውን ለማንበብ
https://press.et/?p=133328
በአዲሱ የውጪ ምንዛሬ አስተዳደር ስርአት ዙሪያ ከአምራች ኢንዱስትሪ ባለቤቶችና የዘርፍ ማህበራት ተወካዮች ጋር ውይይት ተካሄደ
****************
(ኢ.ፕ.ድ)

በአዲሱ የውጪ ምንዛሬ አስተዳደር ስርአት ዙሪያ ከአምራች ኢንዱስትሪ ባለቤቶችና የዘርፍ ማህበራት ተወካዮች ጋር ውይይት መካሄዱን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ውይይቱን ላይ የኢንዱሰትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ ስለ አዲሱ የውጪ ምንዛሬ አሰተዳደር ስርአት ገለፃ ሰጥተው ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ አበረታች እንደሆነ አንስተዋል።

የአምራች ኢንዱስትሪ ባለቤቶችና የዘርፍ ማህበራት ተወካዮች እንደአገር የማክሮ ኢኮኖሚ ስብራቶችን ለመጠገን ከተወሰዱ ማሻሻያዎች መካከል የውጪ ምንዛሬ በገበያ እንዲመራ የማድረግ ስርአት አስፈላጊ እንደሆነም አንስተዋል።

በቂ የሆነ የዉጪ ምንዛሪ ክምችትና አቅርቦት ከመኖሩ ጋር በተያያዘ፣ በምርቶች ላይ ስለሚኖር እጥረትና የዋጋ ጭማሪ ፣ የተዘረጋው ስርአት መስመር ከማስያዝ አንጻር በመንግስት በኩል የተደረጉ የቅድመዝግጅት ስራዎች ፣በዘርፉ የተለያየ የታሪፍ ሰርአት መኖሩና የአደረጃጀት ችግሮች ያሉበት መሆኑ እና ሌሎችም በስጋት የሚሆኑ ነገሮች በውይይቱ ላይ ተነስተዋል።

ከመጀመሪያው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ጀምሮ በመንግስት በኩል አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን የገለፁት የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታረቀኝ የአምራች ኢንዱስሪው ዘርፍ በአገራዊ የኢኮኖሚ እድገት ላይ የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ ለማሳደግ መንግስት የጀመራቸውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል፡፡
የዘርፉ ተዋናዮችም የበኩላቸው ሚና እንዲወጡ ጥሪ ማስተላለፋቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡