Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.76K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት‼️

የፀሀፊን መንፈስ የሚያድሱ ሀይቆች፣ የተፈጥሮን ዚቅ አድምጦ ጥዑም ዜማ ለመቀመር የሚያስችል ድንቅ መልክዓ ምድር፣ የተፈጥሮን ስክነት ማሳያ ስፍራ፣ የውሀዋ ከተማ ቢሾፍቱ።

የምትተክል ሀገር፣ የሚያጸና ትውልድ" በሚል መሪ ቃል የጀመርነውን የዘንድሮውን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐግብር በቢሾፍቱም ቀጥለናል፡፡ በአረንጓዴ ዐሻራ ለአካባቢ ተስማሚ የሆኑ ተነሳሽነቶችን በማስተዋወቅ ለመጪው ትውልድ አረንጓዴ ተፈጥሮና ጤናማ ምድርን እናስረክባለን፡፡

ሐምሌ 23 ቀን 2016 ዓም
በአጥር መደርመስ ምክንያት በደረሰ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን ፖሊስ ገልፀ
*******************
(ኢ ፕ ድ)
በድሬዳዋ ከተማ ወረዳ 4 በተለምዶ ገንደቦዬ ጋራ ላይ እየተባለ በሚጠራው አካበቢ በአጥር መደርመስ ምክንያት በአራት ግለሰቦች ላይ በደረሰ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን ፖሊስ ገልፀ።

የግለሰብ ቤት ተከራይተው የሚኖሩ የድሬዳዋ መምህራን ኮሌጅ የክረምት ተማሪዎች ላይ የጎረቤት አጥር ተደርምሶ የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉንና ሁለት ተጎጂዎች በድልጮራ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ አየተደረገላቸው መሆኑን በድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የወንጀል ምርመራ የታክቲክ ዳሬክቶሬት ኮማንደር መሀመድ ኢብራሂም ገልፀፀዋል።

ሰሞኑን በተደጋጋሚ እየጣለ የሚገኘው ዝናብ ጋር በተያያዘ በጋራ ላይ ሚገኙ መኖሪያ ቤቶች መሰል አደጋዎች እንዳይከሰቱ ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ጉዳቱ በደረሰበት አካባቢ የሚኖሩ ቤተሰቦች ለአደጋ እንዳይጋለጡ ጊዜያዊ ማረፊያ ቦታ መሰጠቱን የከተማዋ ኮሙዩኒኬሽን መረጃ ያመለክታል።
ሐምሌ 23 ቀን 2016 ዓም
ኢትዮጵያና ኡጋንዳ በቀጣናዊ የደኅንነትና ጸጥታ ጉዳዮች በጋራ እያከናወኗቸው ባሉ የትብብር ሥራዎችን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታወቁ
*******
(ኢ ፕ ድ)

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት እና የኡጋንዳ የውጭ ደኅንነት ተቋማት በቀጣናዊ የደኅንነትና ጸጥታ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ እያከናወኗቸው ያሉ የትብብር ሥራዎችን በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ገምግመዋል፡፡

የኢትዮጵያና ኡጋንዳ የመረጃና ደኅንነት ተቋማት ቀደም ሲል በምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና የደኅንነትና የጸጥታ ስጋት የሆኑትን ሽብርተኝነት፣ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን፣ ሕገወጥ ታጣቂዎችንና ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል የደረሱትን የሁለትዮሽ ስምምነት በመተግበር የተገኙ ውጤቶችና ቀጣይ መጠናከር ባሉባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል።

በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት በኩል የውጭ መረጃ ዘርፍ ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ታዜር ገብረ እግዚአብሔር እንዲሁም በኡጋንዳ በኩል ደግሞ የውጭ ደኅንነት ተቋም ዳይሬክተር ጀነራል ጆሴፍ ኦኬሎ የጋራ ውይይቱን መርተዋል፡፡

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ታዜር ገብረ እግዚአብሔር ኡጋንዳ ቀጣናዊና አካባቢያዊ ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር በመሥራት ታሪካዊ ወዳጅ መሆኗን ገልፀው፤ የሀገሪቱ የውጭ አቻ የመረጃ ተቋም ከመረጃ ልውውጥና ከደኅንነት አኳያ ከአገልግሎት መሥሪያ ቤቱ ጋር የጀመረውን አጋርነት አጠናክሮ ለመቀጠል እያሳያ ያለው ቁርጠኝነት የሚደነቅ ነው ብለዋል፡፡

የኡጋንዳ የውጭ ደኅንነት ተቋም ዳይሬክተር ጀነራል ጆሴፍ ኦኬሎ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በጎረቤት ሀገራት እና በቀጣናው ዘለቂ ሰላም እንዲረጋገጥ እየሠራች መሆኑ፤ የሁለቱ ሀገራት የመረጃ ተቋማት ሕገወጦችን ተከታትለውና ለይተው ተጠያቂ በማድረግ ለዘላቂ ሰላም ምቹ መደላድል ለመፍጠር የጀመሩትን ትብብር አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል፡፡

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ለመገናኛ ብዙኃን በላከው መረጃ ፤ ሁለቱ አቻ የመረጃ ተቋማት የዛሬ ሁለት ዓመት በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸውን አስታውሷል፡፡

ሐምሌ 23 ቀን 2016 ዓም
የዓለም ባንክ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ማሻሻያ ለመደገፍ የሚውል ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ አጸደቀ
***
(ኢ.ፕ.ድ)

የዓለም ባንክ የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ዛሬ ባካሄደው ስብሰባው ኢትዮጵያ የጀመረችውን ዘላቂ እና ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲ ለመደገፍ የሚረዳ ውሳኔን አጽድቋል።

ባንኩ ዛሬ ማምሻውን ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረትም ከዓለም አቀፉ የልማት ማህበር የ1 ቢሊዮን ዶላር ዕርዳታና 500 ሚሊዮን ዶላር የብድር ድጋፍ ለኢትዮጵያ ለመስጠት ወስኗል።

ይህ ውሳኔ የኢትዮጵያ መንግስት ድህነት ቅነሳን ለማፋጠን እና ሁሉን አሳታፊና ዘላቂ የሆነ እድገትን ለማረጋገጥ በጀመረው እርምጃ ወቅት የተሰጠ ወሳኝ ድጋፍ መሆኑን ባንኩ አስታውቋል።

የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ትልቁ የልማት አጋር መሆኑን የጠቀሰው የባንኩ መግለጫ፤ ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በየአመቱ ከ2 ቢሊዮን ዶላር በላይ የገንዘብ ድጋፍ የምታገኝ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ግማሽ ያህሉ በእርዳታ መልክ የሚሰጥ መሆኑንም ገልጿል።

ሐምሌ 23 ቀን 2016 ዓ.ም
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት ‼️
በምስሎቹ የምንመለከተው በመልማት ላይ ያለ የሻይ ተክል ማሳ ነው። በቡና ያሳካነውን አመርቂ ድል በሻይ ምርትም እንደግመዋለን።
በትግራይ በውጭ ሀገራት ዜጎች ትብብር ወርቅ በሕገወጥ መንገድ እየወጣ ነው
***************
(ኢ ፕ ድ)
በትግራይ ክልል ከውጭ ሀገራት ዜጎች ጋር በመሆን በሕገወጥ መልኩ የወርቅ ማዕድን እየወጣ እንደሚገኝ የጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ጌታቸው ረዳ ተናገሩ፡፡ በክልሉ የሰፈነውን ሕገወጥነት ለመከላከል እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል።

የክልሉ ፕሬዚዳንት ለክልሉ መገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ እንዳሉት፤ በክልሉ ያለውን አለመረጋጋት በመጠቀም ከውጭ ኃይሎች ጋር በመተባበር የወርቅ ማዕድን በሕገወጥ መንገድ እየወጣ ይገኛል፡፡

የናይጄሪያ፣ የቻይና እና የሴኔጋል ዜጎች በሕገወጥ ሥራው ላይ የተሰማሩ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ የወርቅ ማዕድኑን ለማውጣት አደገኛ ኬሚካሎች ጥቅም ላይ እየዋሉ ይገኛል በተለይ ደግሞ ሳይናይድና ሜርኩሪ የተሰኙት ኬሚካሎቹ ደኖችና እንስሳት ላይ ጉዳት እያደረሱ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ወርቅ በተደራጀ መልኩ የሚያወጡ ሰዎች ኢኮኖሚውን ብቻ የሚጎዱ ሳይሆኑ የፀጥታ ችግርም እየተፈጠረ እንደሚገኝ …
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=133333
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በ38ኛ መደበኛ ስብሰባው የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳለፈ
**********
(ኢ.ፕ.ድ)

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 38ኛ መደበኛ ስብሰባው ዓለም ዐቀፍ የልማት ማህበር ጋር የተደረገውን የፋይናንስ ድጋፍ ስምምነት ለማፅደቅ በተዘጋጀው አዋጅ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

ከዓለም ዐቀፍ የልማት ማህበር ጋር የተደረገው የፋይናንስ ድጋፍ ስምምነት የ1.5 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚያስገኝ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 1 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በእርዳታ፣ 500 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ደግሞ በብድር መልክ የተገኘ ነው፡፡

የፋይናንስ ድጋፉ የኢትዮጵያ መንግሥት የማክሮ ኢኮኖሚውን ለማረጋጋት የጀመራቸውን የሪፎርም ሥራዎች ለማስፈጸም በተለይም ለሥራ ፈጠራ፣ የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር፣ የውጭ ምንዛሪ እጥረትን ለመቅረፍ፣ የመዋቅር ማስተካከያ ለማድረግ እንዲሁም የፌደራል መንግሥት የ2ዐ17 ዓ.ም በጀትን በቀጥታ ለመደገፍ የሚውል ነው፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሰነዱ ላይ ከተወያየ በኋላ ብድሩ ከወለድ ነፃ ፣ የ6 ዓመት የችሮታ ጊዜን ጨምሮ በ38 ዓመታት ውስጥ ተከፍሎ የሚጠናቀቅ እንዲሁም ከአገራችን የብድር አስተዳደር ስትራቴጂ ጋር የሚጣጣም መሆኑን በማረጋገጥ ስምምነቱን አጽድቆ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል።
ሐምሌ 24 ቀን 2016 ዓ.ም