በትምህርት ዘመኑ የተሻለ ውጤት የማስመዝገብ ውጥን
******
(ኢ ፕ ድ)
...........በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተማሪዎች የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ የዝግጀት ሥራ መሠራታቸውን የደጅ አዝማች በላይ ዘለቀ 2ኛ ደረጃና የብሔራዊ ቤተ መንግሥት አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ገልጸዋል።
የደጅ አዝማች በላይ ዘለቀ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አዲስዓለም ታዬ እንዳሉት፤ በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተማሪዎች የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ከወላጆች፣ ከመምህራንና ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በመወያየት የዝግጅት ሥራዎች ተከናውነዋል።
በትምህርት ቤቱ በባለፈው የትምህርት ዘመን 94 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች የክፍል ውጤታቸው ከግማሽ በላይ መሆኑን ገልጸው፤ በ2017 የትምህርት ዘመን ውጤቱን በማሻሻል 97 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎችን ለማሳለፍና ጥሩ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ታቅዷል ይላሉ።
የመማር ማስተማር ሥራዎችን የሚያሳልጡ የተማሪዎች የደንብ ልብስ (ዩኒፎርም)ና የትምህርት ቁሳቁሶችን የማሟላት ሥራዎች መሠራታቸውን ጠቁመው፤ የተማሪ ወላጆች በትምህርት ቤት ሁለንተናዊ.....
https://press.et/?p=136884

የሚኒስቴሩ ተግባር በፈተና የወደቁ ተማሪዎችን በመቶኛ ከመግለጽ የዘለለ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል ‼️
....ከሦስት ዓመታት በላይ የተጓዘው የትምህርት ዘርፉን ስብራት ለይቶ የማከም ጉዞ ግን፤ ዛሬም ላይ ይሄ ነው የሚባል ለውጥ ሳይታይበት በየዓመቱ ፈተና ያላለፉ ተማሪዎች ቁጥር በመቶኛ እያሰሉ በማቅረብ የታጀበ አካሄድ ላይ ተቸክሎ ቆሟል፡፡
ምክንያቱም ዛሬም ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ከተፈታኝ ተማሪዎች 97 በመቶዎቹ አላለፉም ከሚለው የመጀመሪያ መግለጫው፤ ዘንድሮ ከተፈታኝ ተማሪዎች 94 ነጥብ ስድስት በመቶዎቹ አላለፉም የሚል መጠነኛ የቁጥር ማሻሻያ ላይ ደርሶ ከመገለጥ የዘለለ የሚጨበጥ ርምጃ አልታየበትም፡፡
ይሄ ደግሞ ፖሊሲ ለውጦና አዲስ የትምህርት ፍኖተ ካርታም ቀርጾ ላለፉት ሦስትና አራት ዓመታት እየተገበረ እንዳለም ሆነ፤ የትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን አጣምሮ በዘርፉ ውጤት ማሳየት ሥራው እንደሆነ አንድ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ቆም ብሎ ራሱን እንዲፈትሽ፤ እየተመዘገበ ባለው ውጤትም ተማሪዎችን ተጠያቂ ሊያደርግ ሳይሆን የራሱን የሥራ ውጤት ሊገመገምበት የሚገባው ነው...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=136905

ለቱሪዝም ማስተር ፕላን ተግባራዊነት ኢትዮጵያ በቁርጠኝነት እንደምትሰራ አስታወቀች
👉 አባል ሀገራቱ ያዘጋጁት የ10 ዓመት ዘላቂ የቱሪዝም ማስተር ፕላን ይፋ ሆነ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
የኢጋድ አባል ሀገራት ያዘጋጁት የቱሪዝም ማስተር ፕላን ተግባራዊ እንዲሆን ኢትዮጵያ በቁርጠኝነት እንደምትሰራ አስታወቀች።
ኢጋድና አባል ሀገራቱ ዘላቂ የቱሪዝም ልማትን እውን ለማድረግ ያዘጋጁት የ10 ዓመት ዘላቂ የቱሪዝም ማስተር ፕላን በአድዋ ድል መታሰቢያ ዛሬ ይፋ ተደርጓል።
እኤአ ከ2024 እሰከ 2030 የሚተገበር ሲሆን፤ ለቱሪዝም መሰረተ ልማት ልማትና መስፋፋት፣ ለመረጃ ልውውጥጥ፣ የዘርፉን ተግዳሮት ለመፍታት፣ በአባል ሀገራቱ መካከል ነጻ የቪዛ ስርዓት፣ ወጥ የሆነ የቱሪዝም ፖሊሲና አሰራር እንዲኖሮ ያስችላል ተብሏል።
በመድረኩ የኢጋድ ዋና ጸሀፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር)፣ የቀጣናው ሀገራት ያላቸውን እምቅ የቱሪስት መዳረሻ በማልማት ለተተኪው ትውልድ ለማስተላለፍ የተዘጋጀው ማስተር ፕላን ተፈጻሚ እንዲሆን በትብብር መስራት ይገባል ብለዋል።
የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ የኢጋድና አባል ሀገራቱን የ10 ዓመት ዘላቂ የቱሪዝም ማስተር ፕላንን ለማዘጋጀት ስትሰራ መቆየቷን ጠቅሰው ለተግባራዊነቱ ኢትዮጵያ በቁርጠኝነት እንደምትሰራ አስታውቀዋል።
ከቱሪዝም ዘርፉ ተጠቃሚ ለመሆን የቱሪዝም መሰረተ ልማትን በማስፋፋ፣ መዳረሻዎችን በማልማትና በማስተዋወቅየሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ጎብኝዎችን ለመሳብ በትብብር መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል።
በሄለን ወንድምነው
መስከረም 9 ቀን 2017 ዓም

ኢትዮቴሌኮም በ2017 በጀት ዓመት‼️
👉 ገቢውን 163 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ለማድረስ አቅዷል፣
👉 የደበኞቹን ቁጥር 83 ሚሊየን ለማድረስ አቅዷል፣
👉 282 ነጥብ 85 ሚሊየን ዶላር ለማግኘት አቅዷል፣
*****
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት፣ በ2017 በጀት ዓመት አጠቃላይ ገቢውን 163 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ለማድረስ አቅዷል።
የደበኞችን ቁጥር ከ78 ሚሊየን ወደ 83 ሚሊየን፤ የቴሌብር ተጠቃሚዎችን ቁጥር ከ47 ነጥብ 5 ሚሊየን ወደ 55 ሚሊየን ለማድረስ ማቀዱን ገልጸዋል።
በበጀት ዓመቱ 1 ሺህ 298 አዲስ የሞባይል ጣቢያዎች እንደሚገነቡ ጠቅሰው በ500 ከተሞች 4ጂ እና በ15 ከተሞች 5ጂ የሞባይል ኔትወርክ ማስፋፊያ ይደረጋል ብለዋል።
በተጨማሪም 282 ነጥብ 85 ሚሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬን ለማስገኘት መታቀዱንም ገልጸዋል።
ኩባንያው በ2016 በጀት ዓመት 93 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱም ይታወሳል።
በማርቆስ በላይ

ኢትዮጵያ መርህን መሠረት ያደረገ ዲፕሎማሲ ላይ አትኩራ ትሰራለች - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
*****************************
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያ መርህን መሠረት ያደረገ ዲፕሎማሲ ላይ አትኩራ ትሰራለች ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ዛሬ በሰጡት መግለጫ፣ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ለጎረቤት ሀገራት ልዩ ትኩረት እንደሚሰጥ ጠቁመው፣ መርህን መሠረት ያደረገ በበጎ መንፈስ የተቃኘ ዘላቂ ዲፕሎማሲ ላይ አተኩራ ትሰራለች ብለዋል።
የአፍሪካ ቀንድ ቀጣናን የትርምስ ማዕከል ለማድረግ የሚደረግ እንቅስቃሴም ሊቆም ይገባል ብለዋል።
ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር የሚደረጉ የዲፕሎማሲ ግንኙነቶችን በቅርበት እንደምትከታተልና አስፈላጊ በሆነበት ጊዜም ተገቢውን ምላሽ እንደምትሰጥ ገልፀዋል።
ከአውሮፓ ህብረት፣ ከአሜሪካና ከተመድ ልዩ መልዕክተኞች ጋር ውይይቶች መካሄዳቸውን ያነሱት አምባሳደር ነብያት፤ ለሁሉም መልዕክተኞች ኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት የሰፈነበት ሆኖ የኢኮኖሚ ሽግግር እንዲኖር ለማድረግ የምታደርገውን ጥረት ላይ ማብራሪያ ተሰጥቷል ብለዋል።
ኢትዮጵያ ከመስከረም 14 እስከ 20 ቀን 2017 ዓም በኒውዮርክ በሚካሄደው 79ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ መሳተፍ የሚያስችላትን ዝግጅት ማጠናቀቋንም ገልጸዋል።
በተስፋ ፈሩ

👍1
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዛምቢያ ኤርፖርቶች ኮርፖሬሽን የእውቅና ሽልማት ተበረከተለት።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዛምቢያ ኤርፖርቶች ኮርፖሬሽን ላባረከተው የላቀ አገልግሎትና የላቀ የስራ አጋርነት የእውቅና ሽልማት ተበረከተለት።
ሽልማቱ ዛምቢያ ኤርፖርቶች ኮርፖሬሽን 35ኛ ዓመቱን ባከበረበት መርሐግብር ላይ እንደተበረከተለት ተገልጿል።
ለዛምቢያ ኤርፖርት ዕድገት በመንገደኛና በዕቃ ጭነት የአገልግሎት ዘርፎች የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያበረከተው አስተዋፅዖ እና ያልተቋረጠ ድጋፍ ማሳያ መሆኑን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የበየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር) ስርዓተ ቀብር ተፈፀመ
***
(ኢ ፕ ድ)
የሰላማዊ ትግል ተምሳሌት የነበሩት የበየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር) ስርዓተቀብር በጴጥሮስ ወጳውሎስ መካነ መቃብር ተፈፅሟል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት በሚሊኒየም አዳራሽ ሽኝት ከተደረገላቸው በኋላ ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች፣ ቤተሶቦቻቸውና ወዳጆቻቸው በተገኙበት ሥርዓተ ቀብራቸው ተፈጽሟል።
በየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር) ጳጉሜን 4 ቀን 2012 ዓ.ም የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት በዋና ዳይሬክተርነት ሲያገለግሉ መቆየታቸው ይታወሳል። በየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር) ባደረባቸው ህመም ምክንያት በሕክምና ሲረዱ ቆይተው መስከረም 7 ቀን 2017 ዓ.ም ሕይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።
በፋንታነሽ ክንዴ