ለቱሪዝም ማስተር ፕላን ተግባራዊነት ኢትዮጵያ በቁርጠኝነት እንደምትሰራ አስታወቀች
👉 አባል ሀገራቱ ያዘጋጁት የ10 ዓመት ዘላቂ የቱሪዝም ማስተር ፕላን ይፋ ሆነ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
የኢጋድ አባል ሀገራት ያዘጋጁት የቱሪዝም ማስተር ፕላን ተግባራዊ እንዲሆን ኢትዮጵያ በቁርጠኝነት እንደምትሰራ አስታወቀች።
ኢጋድና አባል ሀገራቱ ዘላቂ የቱሪዝም ልማትን እውን ለማድረግ ያዘጋጁት የ10 ዓመት ዘላቂ የቱሪዝም ማስተር ፕላን በአድዋ ድል መታሰቢያ ዛሬ ይፋ ተደርጓል።
እኤአ ከ2024 እሰከ 2030 የሚተገበር ሲሆን፤ ለቱሪዝም መሰረተ ልማት ልማትና መስፋፋት፣ ለመረጃ ልውውጥጥ፣ የዘርፉን ተግዳሮት ለመፍታት፣ በአባል ሀገራቱ መካከል ነጻ የቪዛ ስርዓት፣ ወጥ የሆነ የቱሪዝም ፖሊሲና አሰራር እንዲኖሮ ያስችላል ተብሏል።
በመድረኩ የኢጋድ ዋና ጸሀፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር)፣ የቀጣናው ሀገራት ያላቸውን እምቅ የቱሪስት መዳረሻ በማልማት ለተተኪው ትውልድ ለማስተላለፍ የተዘጋጀው ማስተር ፕላን ተፈጻሚ እንዲሆን በትብብር መስራት ይገባል ብለዋል።
የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ የኢጋድና አባል ሀገራቱን የ10 ዓመት ዘላቂ የቱሪዝም ማስተር ፕላንን ለማዘጋጀት ስትሰራ መቆየቷን ጠቅሰው ለተግባራዊነቱ ኢትዮጵያ በቁርጠኝነት እንደምትሰራ አስታውቀዋል።
ከቱሪዝም ዘርፉ ተጠቃሚ ለመሆን የቱሪዝም መሰረተ ልማትን በማስፋፋ፣ መዳረሻዎችን በማልማትና በማስተዋወቅየሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ጎብኝዎችን ለመሳብ በትብብር መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል።
በሄለን ወንድምነው
መስከረም 9 ቀን 2017 ዓም

ኢትዮቴሌኮም በ2017 በጀት ዓመት‼️
👉 ገቢውን 163 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ለማድረስ አቅዷል፣
👉 የደበኞቹን ቁጥር 83 ሚሊየን ለማድረስ አቅዷል፣
👉 282 ነጥብ 85 ሚሊየን ዶላር ለማግኘት አቅዷል፣
*****
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት፣ በ2017 በጀት ዓመት አጠቃላይ ገቢውን 163 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ለማድረስ አቅዷል።
የደበኞችን ቁጥር ከ78 ሚሊየን ወደ 83 ሚሊየን፤ የቴሌብር ተጠቃሚዎችን ቁጥር ከ47 ነጥብ 5 ሚሊየን ወደ 55 ሚሊየን ለማድረስ ማቀዱን ገልጸዋል።
በበጀት ዓመቱ 1 ሺህ 298 አዲስ የሞባይል ጣቢያዎች እንደሚገነቡ ጠቅሰው በ500 ከተሞች 4ጂ እና በ15 ከተሞች 5ጂ የሞባይል ኔትወርክ ማስፋፊያ ይደረጋል ብለዋል።
በተጨማሪም 282 ነጥብ 85 ሚሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬን ለማስገኘት መታቀዱንም ገልጸዋል።
ኩባንያው በ2016 በጀት ዓመት 93 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱም ይታወሳል።
በማርቆስ በላይ

ኢትዮጵያ መርህን መሠረት ያደረገ ዲፕሎማሲ ላይ አትኩራ ትሰራለች - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
*****************************
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያ መርህን መሠረት ያደረገ ዲፕሎማሲ ላይ አትኩራ ትሰራለች ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ዛሬ በሰጡት መግለጫ፣ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ለጎረቤት ሀገራት ልዩ ትኩረት እንደሚሰጥ ጠቁመው፣ መርህን መሠረት ያደረገ በበጎ መንፈስ የተቃኘ ዘላቂ ዲፕሎማሲ ላይ አተኩራ ትሰራለች ብለዋል።
የአፍሪካ ቀንድ ቀጣናን የትርምስ ማዕከል ለማድረግ የሚደረግ እንቅስቃሴም ሊቆም ይገባል ብለዋል።
ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር የሚደረጉ የዲፕሎማሲ ግንኙነቶችን በቅርበት እንደምትከታተልና አስፈላጊ በሆነበት ጊዜም ተገቢውን ምላሽ እንደምትሰጥ ገልፀዋል።
ከአውሮፓ ህብረት፣ ከአሜሪካና ከተመድ ልዩ መልዕክተኞች ጋር ውይይቶች መካሄዳቸውን ያነሱት አምባሳደር ነብያት፤ ለሁሉም መልዕክተኞች ኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት የሰፈነበት ሆኖ የኢኮኖሚ ሽግግር እንዲኖር ለማድረግ የምታደርገውን ጥረት ላይ ማብራሪያ ተሰጥቷል ብለዋል።
ኢትዮጵያ ከመስከረም 14 እስከ 20 ቀን 2017 ዓም በኒውዮርክ በሚካሄደው 79ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ መሳተፍ የሚያስችላትን ዝግጅት ማጠናቀቋንም ገልጸዋል።
በተስፋ ፈሩ

👍1
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዛምቢያ ኤርፖርቶች ኮርፖሬሽን የእውቅና ሽልማት ተበረከተለት።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዛምቢያ ኤርፖርቶች ኮርፖሬሽን ላባረከተው የላቀ አገልግሎትና የላቀ የስራ አጋርነት የእውቅና ሽልማት ተበረከተለት።
ሽልማቱ ዛምቢያ ኤርፖርቶች ኮርፖሬሽን 35ኛ ዓመቱን ባከበረበት መርሐግብር ላይ እንደተበረከተለት ተገልጿል።
ለዛምቢያ ኤርፖርት ዕድገት በመንገደኛና በዕቃ ጭነት የአገልግሎት ዘርፎች የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያበረከተው አስተዋፅዖ እና ያልተቋረጠ ድጋፍ ማሳያ መሆኑን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የበየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር) ስርዓተ ቀብር ተፈፀመ
***
(ኢ ፕ ድ)
የሰላማዊ ትግል ተምሳሌት የነበሩት የበየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር) ስርዓተቀብር በጴጥሮስ ወጳውሎስ መካነ መቃብር ተፈፅሟል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት በሚሊኒየም አዳራሽ ሽኝት ከተደረገላቸው በኋላ ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች፣ ቤተሶቦቻቸውና ወዳጆቻቸው በተገኙበት ሥርዓተ ቀብራቸው ተፈጽሟል።
በየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር) ጳጉሜን 4 ቀን 2012 ዓ.ም የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት በዋና ዳይሬክተርነት ሲያገለግሉ መቆየታቸው ይታወሳል። በየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር) ባደረባቸው ህመም ምክንያት በሕክምና ሲረዱ ቆይተው መስከረም 7 ቀን 2017 ዓ.ም ሕይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።
በፋንታነሽ ክንዴ

ከበዓላት ጋር የተያያዙ የጉብኝት ጥቅሎች መዘጋጀታቸውን የቱሪዝም ሚኒስቴር አሳወቀ
******************
(ኢ ፕ ድ)
በመስከረም ወር የሚከበሩ የአደባባይ በዓላትን መሠረት ያደረጉ የጉብኝት ጥቅሎች (ፓኬጆች) መዘጋጀታቸውን ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ።
የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ስለሺ ግርማ ለኢፕድ እንደገለጹት፤ በመስከረም ወር ቀጣይ ቀናት መስቀል፣ ኢሬቻና የዓለም ቱሪዝም ቀን እንዲሁም የተለያዩ አካባቢዎች የዘመን መለወጫ በዓላት ይከበራሉ።
በመስከረም ወር የሚከናወኑ የተለያዩ በዓላት ለቱሪዝም ገቢ ዕድገት ያላቸውን ሰፊ ጠቀሜታ በመረዳትና ከክልሎች ጋር በመነጋገር የተለያዩ የጉብኝት ጥቅሎችን.....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=136968

በመዲናዋ ከቱሪዝም ዘርፍ ከ119 ቢሊዮን ብር በላይ ወደኢኮኖሚው ፈሰስ ለማድረግ እየተሠራ ነው
********************
(ኢ ፕ ድ)
በአዲስ አበባ ከተማ በ2017 በጀት ዓመት ከቱሪዝም ዘርፍ ከ119 ቢሊዮን በላይ ብር ወደ ከተማው ኢኮኖሚ ፈሰስ ለማድረግ መታቀዱን የአዲስ አበባ ባሕል፣ ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ፡፡
በአዲስ አበባ ባሕል፣ ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ የቱሪዝም መዳረሻ ልማትና የሀገር ውስጥ ቱሪዝም ማስፋፊያ ዳይሬክተር አቶ ሳምሶም አይናቸው ለኢፕድ እንደገለጹት፤ በ2017 ከተማዋን የቱሪዝም መዳረሻ በማድረግ ከሀገር ውስጥና ከውጪ ቱሪስቶች 119 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ወደከተማው ኢኮኖሚ ፈሰስ ለማድረግ ታቅዷል፡፡
የ2017 በጀት ዓመት የዝግጅት ምዕራፍ ላይ የሚገኝ መሆኑን ጠቅሰው፤ ባለፈው ዓመት የነበሩ ጥንካሬ እና ድክመቶችን....
https://press.et/?p=136961