Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ከንቲባ አዳነች አቤቤ የ12ኛ ከፍል ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች እውቅና ሰጡ
********************
(ኢ ፕ ድ)
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሃገር አቀፍ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎችና ተማሪዎቻቸውን ሙሉ በሙሉ ላሳለፉ ትምህርት ቤቶች እውቅና ሰጡ።

በእውቅና ሽልማት መርጋግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግርም በ12 ኛ ክፍል ፈተና ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የከተማዋም የሃገርም ኩራት ናቸው ብለዋል።

የምመጣው ውጤት ባጋጣሚ የመጣ ሳይሆን በብዙ ልፋትና ትጋት የተገኘ ነው ያሉ ከንቲባዋ ውጤቱ ከተማዋንም ሆነ ሃገራችንን ያኮራ ነው ብለዋል።

ባለፉት ዓመታት የ12ኛ ክፍል ውጤት በአስደንጋጭ ሁኔታ ማሽቆልቆሉን አንስተው መንግስት ለትምህርት ዘርፉ በሰጠው ትኩረት ዘንድሮ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን ተናግረዋል።

ከንቲባዋ ይህ እንዲመዘገብ አስተዋጽኦ ላረጉ ወላጆች መምህራንና ትምህርትቤቶች ምስጋና አቅርበው፤ ከተማ አስተዳደሩ ከአንድ እስከ ሶስት ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ሴት ተማሪዎች የስኮላርሺፕ እድል እንዳመቻቸ አሳውቀዋል ።

በዳግማዊት አበበ
መስከረም 27 ቀን 2017 ዓም
👍5
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን አርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ የሙዝ፣ ፓፓያ እና አቮካዶ ፍራፍሬ ልማት‼️
👍9👎1
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
👍2🔥1
በመኖሪያ ቤት ተጀምሮ አደባባይ የወጣው የኦሮሞ ባሕላዊ አልባሳት ማምረት ሥራ

. . . ምንም ዓይነት የስፌት ስልጠና ሳትወስድ ባለቤቷ የጻፏቸውን የኦሮሞ ባሕላዊና ታሪካዊ እሴቶችን ብቻ በማንበብ የኦሮሞ ባሕላዊ አልባሳት ምን እንደሚመስሉ ተረድታለች።

አልባሳቱ ላይ የሚደረጉ ጌጣጌጦችንም እንዲሁ በንባብና ከባለቤቷ ታሪኩን በመረዳት ወደ ሥራው የገባችው ወይዘሮ አይሻ፤ ከልጆቿ ጋር በመኖሪያ ቤቷ ውስጥ የጀመረችው ሥራም ወደ ቢዝነስ ተቀይሮ ኑሮዋን መደገፍ ችሏል።

ለኦሮሞ ባሕል ካላት ቅርበት የተነሳ መደበኛ ሥራዋን ቀን ቀን እየሰራች ሌሊት ደግሞ ባሕላዊ አልባሳቱን እየሰራች ገበያ ውስጥ መግባት ችላለች።

የኦሮሞ ባሕላዊ አልባሳት ከቁርበትና ቆዳ ይሰራ እንደነበር ያስታወሰችው ወይዘሮ አይሻ፤ የዘመኑ ሰው አልባሳቱን በቀላሉ መጠቀም እንዲችልና ከትውልድ ወደ ትውልድ በቀላሉ እንዲተላለፍ ለማድረግ በካባና ተቀራራቢ በሆኑ ጨርቆች ላይ እንዲሰራ ማድረግ የቻሉ ባለቤቷ እንደሆኑ ...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=137965
👍2😁2
አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ
*************
(ኢ ፕ ድ)
የመክፈቻ ጉባኤያቸወን እያደረጉ ያሉት ሁለቱ ምክር ቤቶች የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴን በአምስት ድምጸ ተአቅቦ የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት አድርገው ሰይመዋል።

ፕሬዝዳንቱ በምክር ቤቱ ቃለ መሀላ ፈጽመዋል።

መስከረም 27 ቀን 2017 ዓም
🔥72
የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ማን ናቸው?
***********
(ኢ.ፕ.ድ)
የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ የተወለዱት በደባርቅ ሰሜን ጎንደር ነው፡፡
የመጀመሪያ ድግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት አግኝተዋል።

እንግሊዝ ከሚገኘው ላንክስተር ዩኒቨርሲቲ ደግሞ በዓለም አቀፍ ግንኙነት እና በስትራቴጂ ጥናት ሁለተኛ ድግሪያቸውን ወስደዋል።

በተለያዩ ሀገራት አጫጭር የዓለም አቀፍ ግንኙነት እና ፖለቲካል ሳይንስ ሥልጠናዎችን እና ኮርሶችን ወስደዋል።

አምባሳደር ታዬ፤ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአውሮፓ መምሪያ የሥራ ክፍል ፣የምዕራብ አውሮፓ ዋና ክፍል ኃላፊ፣የኢንፎርሜሽን ተጠባባቂ ዳይሬክተር፣ስቶክሆልም የኢፌዲሪ ኤምባሲ በአማካሪነት፣በዋሽንግተን የኢፌዲሪ ኤምባሲ በአማካሪነት።

በሎስአንጀለስ ቆንስል ጀነራል፣ በ1998ዓ.ም ባለሙሉሥልጣን አምባሳደርነት ተሹመዋል፣
በሎስአንጀለስ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደርነት ማዕረግ የቆንስላ ጽ/ቤት ኃላፊ፣ በአውሮፓ እና አሜሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀኔራል፣ በ2008 ዓ.ም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ሰርተዋል።

በግብፅ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደርነት፣ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ ተጠሪ ሆነው አገልግለዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ አማካሪ ሚኒስትር ሆነው ሰርተዋል፤
አምባሳደር ታዬ እስከዛሬዋ ዕለት ድረስም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ሠርተዋል።
👍10🔥21
የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ባደረጉት ንግግር ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች ‼️

👉 ኢኮኖሚያችን አዲስ የታሪክ እጥፋት ላይ ነው

👉 በግብርና መስክ ባለፈው አመት 6 ነጥብ 9 በመቶ እድገት ተመዝግቧል

👉በ2016 በጀት አመት 230 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ተመርቷል

👉 በ2016 በጀት አመት 26 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት ታርሷል፤

👉 በሌማት ቱሩፋት በሁሉም ክልሎች ከፍተኛ ምርት ተገኝቷል፤

👉በአረንጓዴ ዐሻራ ባለፉት ስድስት አመታት 40 ቢሊዮን ችግኝ ተተክሏል፤

👉 በኢንዱስትሪው መስክ 9 ነጥብ 2 በመቶ እድገት ተመዝግቧል፤

👉 የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ምርታማነት እድገት 59 በመቶ ደርሷል፤

👉 395 ኢንዱስትሪዎች ወደ ስራ ተመልስዋል፤

👉በአገልግሎት መስክ 7 ነጥብ 9 በመቶ እድገት ተመዝግቧል፤

👉 737 የመንግስት አገልግሎቶች በኤሌክትሮኒክስ እየተሰጡ ነው፤

👉 የሁሉም ባንኮች ሀብት 2 ነጥብ 5 ትሪሊዮን ብር ደርሷል፤

👉የሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚዎች 39 ነጥብ 6 ሚሊዮን ደርሷል፤

👉 በዲጂታል የተላለፈ የብር መጠን 9 ነጥብ 6 ትሪሊዮን ብር ደርሷል፤

👉የመንገድ ሽፋን 169 ሺ 600 ደርሷል፤

👉 የሞባይል ስልክ ተጠቃሚ ቁጥር 83 ነጥብ 3 ሚሊዮን ደርሷል፤

👉የንጹህ ውሃ ተጠቃሚዎች ቁጥር 74 ነጥብ 8 ሚሊዮን ደርሷል፤

👉 የአባይ ግድብ አጠቃላይ ግንባታ 96 ነጥብ 7 በመቶ በላይ ተጠናቋል
👍19🕊6😁2🤔1
"በ2017 በጀት አመት 8 ነጥብ 4 በመቶ እድገት ለማስመዝገብ ጥረት ይደረጋል"
- አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት
🔥11👍2
በሊባኖስ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን አስመልክቶ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተሰጠ መግለጫ‼️
👍2😁1
የአፍሪካ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኮንፈረንስ ዛሬ በአዲስ አበባ ይካሄዳል
**************
(ኢ ፕ ድ)
የአፍሪካ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኮንፈረንስ ዛሬ በአዲስ አበባ በዓድዋ ድል መታሰቢያ “አፍሪካን በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ማላቅ” በሚል ይካሄዳል፡፡

በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት አዘጋጅነት የሚካሄደዉ 3ኛው ዙር ፓን አፍሪኮን ኤ.አይ 2024 ኮንፈረንስ ለሁለት ቀናት መስከረም 28 እና 29፣ 2017 ዓ.ም እንደሚካሄድ ኢንሰቲትዩት አሰታውቋል።

መስከረም 28 ቀን 2017 ዓም
👍2
በአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ውስጥ የኢትዮጵያን ተሳትፎ ለማሳደግ የንግድ ማህበራት በትኩረት ሊሠሩ ይገባል
******************
(ኢ ፕ ድ)
በአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ውስጥ የኢትዮጵያን ተሳትፎ ለማሳደግ የንግድ ማህበራት በትኩረት ሊሠሩ እንደሚገባ ተገለጸ።

የዓለም አቀፍ ንግድ ፖሊሲ ባለሙያ አቶ ጃሌቶ ገመዲ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳስታወቁት፤ በቅርቡ በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ዙሪያ ሊኖሩ የሚችሉ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ ውጤታማ ትግበራ እንዲኖር ለማስቻል እንዲሁም የግሉ ሴክተር እና ላኪዎችን ተደራሽነት ለማሳደግ ያለመ ጥናት መካሄዱን ጠቁመው፤ በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ዙሪያ የንግዱ ማህበረሰብ ግንዛቤ አናሳ መሆኑን አንስተዋል።

በአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ውስጥ የኢትዮጵያን ተሳትፎ ለማሳደግም የንግድ ማህበራት በትኩረት ሊሠሩ እንደሚገባም ገልጸዋል።

በጉዳዩ ዙሪያ የተቀመጡ አሠራሮችና ሕጎች፣ ውስብስብ የፈቃድ አሰጣጥ ሥርዓቶችና የቁጥጥር ማነቆዎች ተግዳሮት እየፈጠሩ መሆኑን የጠቀሱት ባለሙያው፤ ወጥነት የጎደለው የአፈፃፀምና የአሰራር ቅልጥፍናም ተጽዕኖ እየፈጠረ ይገኛል።

ኢትዮጵያ በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ላይ ያላትን ግንዛቤ የተመለከተውን ጥናት መነሻ አድርገው እንደገለጹት፤ በተለይም ከአፈፃፀሙ ጋር በተያያዙ የተለያዩ ተግዳሮቶች መኖራቸውን....

https://press.et/?p=138142
1👍1👎1
የማህበረሰቡ ልሳናት
************
(ኢ ፕ ድ)
ሀገራዊ እሴቶችን በማህበረሰቡ ቋንቋ ለየአካባቢው ማህበረሰብ ተደራሽ ለማድረግ የማህበረሰብ መገናኛ ብዙኃን የሚጫወቱት ሚና ከፍተኛ መሆኑ እሙን ነው።

በሌሎች መገናኛ ብዙኃን የማይሸፈኑ አካባቢያዊ መረጃዎችን ለማህበረሰቡ በማድረስ የማህበረሰቡ ወግ፣ ባህልና ቋንቋ እንዲዳብር ከመስራት በተጨማሪ የማህበረሰቡ ትስስር እንዲጠናከርና ሰላም እንዲሰፍን በየአካባቢው ቋንቋ በማህበረሰቡ ዘንድ ግንዛቤ ሊፈጥሩ እንደሚገባ ይገለጻል።

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ ተኮር ሬዲዮ ጣቢያ ጊዜያዊ ተጠሪ አቶ ኤፍሬም አክሊሉ እንደሚገልጹት፤ የሬዲዮ ጣቢያው በድሬዳዋ ከተማና አካባቢው ለሚኖሩ ዜጎች መረጃን ተደራሽ ለማድረግ በ2014 ዓ.ም የተቋቋመ ሲሆን፤ ለአንድ ዓመት የሙከራ ስርጭት ካከናወነ በኋላ ወደ መደበኛ ስርጭት መግባት ችሏል።

በአካባቢው የተለያዩ የሬዲዮ ጣቢያዎች ቢኖሩም ከእነኝህ ጣቢያዎች በተለየ መልኩ ታችኛውን የማህበረሰብ ክፍል አጠቃላይ እንቅስቃሴ የሚዳሰሱባቸውን መሰናዶዎች......
https://press.et/?p=138139
👍2
በሊባኖስ የተፈጠረውን ወቅታዊ ሁኔታ ተከትሎ በችግር ላይ የነበሩ 51 ዜጎች ወደሀገራቸው ገቡ
****************
(ኢ ፕ ድ)
በሊባኖስ የተፈጠረውን ወቅታዊ ሁኔታ ተከትሎ በችግር ላይ የነበሩ 51 ዜጎች በሁለት በረራዎች ዛሬ ማለዳ ወደሀገራቸው ገብተዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው እና የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም (ዶ/ር) ለዜጎቹ አቀባበል አድርገዋል።

አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው እንደገለፁት፤ በሊባኖስ በተከሰተው ወቅታዊ ሁኔታ ለአደጋ ተጋላጭ ዜጎችን ወደሀገራቸው ለመመለስ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ነው።

በዚህም ዜጎቹን ለመመለስ እየተደረገ ባለው ጥረት የሚያስተባብር አመራር ወደ ሊባኖስ ተልኮ ሥራውን ጀምሯል።

በአካል እና በዲጂታል የምዝገባ ስርዓት ተዘርግቶ ዜጎች እየተመዘገቡ ይገኛሉ ያሉት አምባሳደር ነቢያት፤ ዜጎች ሊባኖስ በሚገኘው ቆንስላ ጽህፈት ቤት አማካኝነት በፈለጉት አማራጭ ተመዝግበው ወደሀገራቸው እንዲመለሱ ጥሪ አቅርበዋል።

በመጀመሪያው ዙር 51 ዜጎች በዛሬው ዕለት ወደሀገራቸው መመለስ መቻሉን አምባሳደሩ ጠቁመዋል።

አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ መንግስት እያከናወነ በሚገኘው የዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ ተግባር በዬትኛውም ሁኔታ በችግር ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ህይወት ለመታደግ በአትኩሮት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ይህ ተግባር መንግስት በሀገር ውስጥ የሚገኙ ዜጎች ጉዳይ የሚያሳስበውን ያህል በተለያዩ ሁኔታዎች ከሀገራቸው የወጡ ዜጎችም ሁኔታ እንደሚያሳስበው ማሳያ መሆኑን በመግለፅ በቀጣይም መንግሥት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ለዜጎቹ የክትትል እና ድጋፍ ስራ እንደሚያከናውን ኮሚሽነሩ ጠቁመዋል።

በቃልኪዳን አሳዬ
መስከረም 28 ቀን 2017
👍6👏2