Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የ10 ኪሜ ሩጫ የውድድር ደረጃዎች ውስጥ ተካተተ
*****
(ኢ ፕ ድ)
የዓለም አትሌቲክስ አስተዳዳሪ ዎርልድ አትሌቲክስ የ2017 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ 10 ኪሜ ሩጫን የሌብል ደረጃ ያለው የጎዳና ላይ ውድድር ሲል ዕውቅና ሰጥቶታል።

የአለም አትሌቲክስ የሌብል ደረጃ ሲል የሰየማቸው ውድድሮች በጥራት ዝግጅቶችን ከማድረግ፣ ደህንነታቸው የተጠበቀ ከመሆን እና የተሳታፊዎች ውድድሩ ላይ የነበራቸው ቆይታ፣ የከተማ አስተዳደሮች ለዝግጅቱ ያላቸውን ድጋፍ፣ ዝግጅቱ በአትሌቲክስ ውድድር ዘርፍ አበረታች መድኃኒት ላይ ለመስራት ያለውን ቁርጠኝነት ከግምት ውስጥ ያስገባ መሆኑ ተጠቅሷል።

እጅግ በርካታ የሩጫ ውድድሮች ባሉበት ዓለም ይህንን የሌብል ደረጃ ማግኘት ዝግጅቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ ያሳየውን ዕድገት እና በዓለማችን ካሉ ቀዳሚ እና ተመራጭ የጎዳና ላይ ውድድሮች መሀከል መሆኑንም እንደሚያሳይ ተጠቁሟል።

የአለም አትሌቲክስ አስተዳዳሪው አካል (World Athletics) ውድድሮችን በመመዘን በየአመቱ ደረጃዎችን የሚሰጥ ሲሆን፤ የመሮጫ ኮርስ ልኬት፣ የውድድር ሰዓት ምዝገባ እና የኤሊት አትሌቶች ተሳትፎ ከግምት ውስጥ የሚገቡ ጉዳዮች ናቸው።

24ኛው ዙር ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10ኪሜ ህዳር 8 ቀን 2017 በ50ሺ ተሳታፊዎች እንደሚካሄድ ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

መስከረም 28 ቀን 2017 ዓም
🙏31
የምግብ ዘይትን በሀገር ውስጥ ምርት የመተካት ተግባር ውጤት አስገኝቷል
************************
(ኢ ፕ ድ)
የምግብ ዘይትን በሀገር ውስጥ ምርት የመተካት ተግባር ከጊዜ ወደ ጊዜ በመሻሻሉ ተጨባጭ ውጤት እያስገኘ መሆኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ።

በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የምግብና መጠጥ ምርምርና ልማት ማዕከል ሥራ አስኪያጅ አቶ በቀለ መኩሪያ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳስታወቁት፤የምግብ ዘይትን በሀገር ውስጥ ምርት የመተካት ተግባር ውጤት እያስገኘ ነው።

የምግብ ዘይት ፍጆታን በሀገር ውስጥ ምርቶች ለመተካት ወደ ሥራ ከገቡት በተጨማሪ በሰፊው የማምረት አቅም ያላቸው አዳዲስ የዘይት ፋብሪካዎች እየተቋቋሙ ነው ያሉት አቶ በቀለ፤ በጥሬ እቃ አቅርቦት፣ ፋብሪካዎቹን በማስፋፋትና በሙሉ አቅማቸው እንዲያመርቱ የድጋፍ ክትትል እንዲሁም የተለያዩ የአቅም ግንባታ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።

እንደ አቶ በቀለ ገለጻ፤ ከሦስትና አራት ዓመት በፊት ከ95 በመቶ በላይ የሚሆነው የምግብ ዘይት ፍጆታ ከውጭ የሚገባ ነበር። አሁን ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባው የምግብ ዘይት መጠን 81 በመቶ ዝቅ.....

https://press.et/?p=138174
👍2👏1😁1
ችግሮችን ለመፍታትና ሕይወትን ለማቅለል ወሳኝ የሆነውን የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ አቅምና አጠቃቀም ማሳደግ ይገባል
******************
(ኢ ፕ ድ)
ችግሮችን ለመፍታትና ሕይወትን ለማቅለል ወሳኝ የሆነውን የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ አቅምና አጠቃቀም ማሳደግ እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

3ኛው ፓን አፍሪኮን ኤአይ 2024 "አፍሪካን በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ማላቅ" በሚል ሀሳብ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ።

በመድረኩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ እንደገለጹት፤ ኤአይ የአፍሪካን ችግሮች ለመፍታት፣ የማህበረሰቡን ኑሮ ለማቃለል፣ ለኢኮኖሚያዊ እድገት፣ ለስራ እድል ፈጠራ፣ ለግብርና፣ ለጤና እና ለሌሎች ዘርፎች የሚያበረክተው ሚና ከፍተኛ ነው።

ችግሮችን ለመፍታትና ሕይወትን ለማቅለል ወሳኝ የሆነውን የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ አቅምና አጠቃቀም ለማሳደግ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የመረጃ አያያዝ ቴክኖሎጂን ማሳደግ፣ ብቁ የሰው ኃይል ማፍራት፣ የማሽን ቋንቋ ያልሆኑ ሀገረኛ ቋንቋዎችን ማሽን እንዲያውቃቸው የማድረግ እንዲሁም የግብርናውን ዘርፍ ችግሮች ከመፍታት አንጻር በርካታ ስራዎችን ማከናወኑን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢኒስቲቲዩት ያዘጋጀው 3ተኛው ዙር ፓን አፍሪኮን ኤ.አይ 2024 ኮንፈረንስ መካሄድ የጀመረ ሲሆን፤ ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት ይቆያል ተብሏል።

በኮንፈረንሱ የኢፌደሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ቴድሮስ ምህረት፣ የድሬዳዋ ከንቲባ ከድር ጀዋርን ጨምሮ የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

በሄለን ወንድምነው
መስከረም 28 ቀን 2017 ዓም
👍61🤝1
የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት ‼️

በሰው ሰራሽ አስተውሎት የፈጠራ ማዕከል የሆነች አፍሪካን እንፈጥራለን፡፡

ዛሬ "አፍሪካን በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ማላቅ" በሚል መሪ ሀሳብ ላይ አትኩሮቱን ባደረገው 3ኛው የፓን አፍሪኮን አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ጉባኤ ላይ ታድመናል፡፡

ጉባኤው ትብብሮች የሚጠናከሩበት እና ችግር ፈቺ ሀሳቦች የሚፈልቁበት በመሆኑ አፍሪካዊ አንድነትን በማምጣቱ ረገድ የሚኖረው ሚና የላቀ ነው፡፡

አፍሪካ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ብቻ መሆን የለባትም፡፡

ይልቁኑ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ አብዮት ውስጥ ግንባር ቀደሟ አህጉር ለማድረግ መስራት ይኖርብናል፡፡
ይህ የእኛ ጊዜ ነው።

አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ያለውን የለውጥ ሃይል በመጠቀም የአህጉራችንን መንገድ ማስተካከል ይገባናል፡፡

ይህንን ጉባኤ በማዘጋጀት ረገድ ቁልፍ ሚና ለተወጡት የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት አመራሮች እና ሠራተኞች እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ፡፡
👍8😁3
በአዲስ አበባ በሁለተኛ ምዕራፍ #የኮሪደር_ልማት ፕሮጀክት ስምንት ኮሪደሮች ይለማሉ

👉 ካዛንቺስ፣መስቀል አደባባይ፣ ሜክሲኮ፣ ቸርችል፣ አራት ኪሎ፣ እስጢፋኖስ

👉 ሳውዝጌት፣ መገናኛ፣ ሃያሁለት፣ መስቀል አደባባይ፣

👉 ሲኤምሲ፣ ሰሚት ጎሮ፣ ቦሌ አየር ማረፊያ ቪአይፒ ተርሚናል፣ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽንና ኤግዚብሽን ማዕከል፣

👉 ሳር ቤት፣ ካርል አደባባይ፣ ብስራተ ገብርኤል፣ አቦ ማዞሪያ፣ ላፍቶ አደባባይ፣ ፉሪ አደባባይ

👉 አንበሳ ጋራዥ፣ጃክሮስ ጎሮ፣

👉 አራት ኪሎ፣ ሽሮ ሜዳ እንጦጦ ማርያም፣ ጉለሌ እጸዋት ማዕከል

👉 የቀበና ወንዝ ዳርቻ ኮሪደር ልማት

👉 እንጦጦ፣ ፒኮክ ፓርክ የወንዝ ዳርቻ ልማት ኮሪደር ልማት

መስከረም 28 ቀን 2017 ዓም
👍11
የሁለተኛ ምዕራፍ #የኮሪደር_ልማት ፕሮጀክት‼️

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ‼️

✍️ የሁለተኛው ምዕራፍ  የኮሪደር ልማት ስራ በዚህ ሳምንት ይጀመራል፣

✍️ በአጠቃላይ 2817 ሄክታር የቦታ ስፋት ሲኖረው 132 ኪሎሜትር ርዝመት ይሸፍናል፣

✍️ ለቀበሌ ቤት ተነሺዎች ምትክ ቤቶች ተዘጋጅተዋል፣

✍️ ተነሺዎች ያላቸው ማህበራዊ ትስስር እንዳይበተን በአንድ አካባቢ እንዲሰፍሩ ይደረጋል፣

✍️ከ500 በላይ የሚሆኑ የንግድ ሱቆችን ለነዋሪዎቻችን ዝግጁ ተደርገዋል፣

✍️ በአዲስ አበባ የሁለተኛ ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ስምንት ኮሪደሮች ይለማሉ፣

መስከረም 28 ቀን 2017 ዓም
👍4👎2
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መልዕክት ‼️

በብዙ የሀገራችን ክፍል እንደሚታየው የደቡብ ክልል በተፈጥሮ ሀብት የበለፀገ ነው። በያዝነው የምርት ዘመን የፍራፍሬና አትክልት ምርት በተለየ ሁኔታ አጥጋቢ ሆኗል።

34 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል ፍራፍሬና 7ነጥብ 6 ኩንታል አትክልት ተመርቷል።

ይህን በደቡብ ክልል የታየ ስኬት በሌሎች ክልሎችም ለማስፋፋት የጋራ እድገት ለማስገኘትና የምግብ ዋስትና ትልማችንን አሳክቶ ዘላቂ ልማትን በሚያረጋግጥ መልክ ጠንክረን መስራት ይገባል።

መስከረም28 ቀን 2017 ዓም
👍14😢21🤨1