Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት ‼️

በሰው ሰራሽ አስተውሎት የፈጠራ ማዕከል የሆነች አፍሪካን እንፈጥራለን፡፡

ዛሬ "አፍሪካን በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ማላቅ" በሚል መሪ ሀሳብ ላይ አትኩሮቱን ባደረገው 3ኛው የፓን አፍሪኮን አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ጉባኤ ላይ ታድመናል፡፡

ጉባኤው ትብብሮች የሚጠናከሩበት እና ችግር ፈቺ ሀሳቦች የሚፈልቁበት በመሆኑ አፍሪካዊ አንድነትን በማምጣቱ ረገድ የሚኖረው ሚና የላቀ ነው፡፡

አፍሪካ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ብቻ መሆን የለባትም፡፡

ይልቁኑ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ አብዮት ውስጥ ግንባር ቀደሟ አህጉር ለማድረግ መስራት ይኖርብናል፡፡
ይህ የእኛ ጊዜ ነው።

አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ያለውን የለውጥ ሃይል በመጠቀም የአህጉራችንን መንገድ ማስተካከል ይገባናል፡፡

ይህንን ጉባኤ በማዘጋጀት ረገድ ቁልፍ ሚና ለተወጡት የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት አመራሮች እና ሠራተኞች እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ፡፡
👍8😁3
በአዲስ አበባ በሁለተኛ ምዕራፍ #የኮሪደር_ልማት ፕሮጀክት ስምንት ኮሪደሮች ይለማሉ

👉 ካዛንቺስ፣መስቀል አደባባይ፣ ሜክሲኮ፣ ቸርችል፣ አራት ኪሎ፣ እስጢፋኖስ

👉 ሳውዝጌት፣ መገናኛ፣ ሃያሁለት፣ መስቀል አደባባይ፣

👉 ሲኤምሲ፣ ሰሚት ጎሮ፣ ቦሌ አየር ማረፊያ ቪአይፒ ተርሚናል፣ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽንና ኤግዚብሽን ማዕከል፣

👉 ሳር ቤት፣ ካርል አደባባይ፣ ብስራተ ገብርኤል፣ አቦ ማዞሪያ፣ ላፍቶ አደባባይ፣ ፉሪ አደባባይ

👉 አንበሳ ጋራዥ፣ጃክሮስ ጎሮ፣

👉 አራት ኪሎ፣ ሽሮ ሜዳ እንጦጦ ማርያም፣ ጉለሌ እጸዋት ማዕከል

👉 የቀበና ወንዝ ዳርቻ ኮሪደር ልማት

👉 እንጦጦ፣ ፒኮክ ፓርክ የወንዝ ዳርቻ ልማት ኮሪደር ልማት

መስከረም 28 ቀን 2017 ዓም
👍11
የሁለተኛ ምዕራፍ #የኮሪደር_ልማት ፕሮጀክት‼️

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ‼️

✍️ የሁለተኛው ምዕራፍ  የኮሪደር ልማት ስራ በዚህ ሳምንት ይጀመራል፣

✍️ በአጠቃላይ 2817 ሄክታር የቦታ ስፋት ሲኖረው 132 ኪሎሜትር ርዝመት ይሸፍናል፣

✍️ ለቀበሌ ቤት ተነሺዎች ምትክ ቤቶች ተዘጋጅተዋል፣

✍️ ተነሺዎች ያላቸው ማህበራዊ ትስስር እንዳይበተን በአንድ አካባቢ እንዲሰፍሩ ይደረጋል፣

✍️ከ500 በላይ የሚሆኑ የንግድ ሱቆችን ለነዋሪዎቻችን ዝግጁ ተደርገዋል፣

✍️ በአዲስ አበባ የሁለተኛ ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ስምንት ኮሪደሮች ይለማሉ፣

መስከረም 28 ቀን 2017 ዓም
👍4👎2
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መልዕክት ‼️

በብዙ የሀገራችን ክፍል እንደሚታየው የደቡብ ክልል በተፈጥሮ ሀብት የበለፀገ ነው። በያዝነው የምርት ዘመን የፍራፍሬና አትክልት ምርት በተለየ ሁኔታ አጥጋቢ ሆኗል።

34 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል ፍራፍሬና 7ነጥብ 6 ኩንታል አትክልት ተመርቷል።

ይህን በደቡብ ክልል የታየ ስኬት በሌሎች ክልሎችም ለማስፋፋት የጋራ እድገት ለማስገኘትና የምግብ ዋስትና ትልማችንን አሳክቶ ዘላቂ ልማትን በሚያረጋግጥ መልክ ጠንክረን መስራት ይገባል።

መስከረም28 ቀን 2017 ዓም
👍14😢21🤨1
"ኢትዮጵያ ከአንድ ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ ፍልሰተኞች መጠለያ ናት"
- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
*

(ኢ ፕ ድ)

ኢትዮጵያ ከአንድ ነጥብ 1 ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ ፍልሰተኞች መጠለያ ናት ሲሉ የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለፁ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ ዛሬ ከተባበሩት መንግስታት የዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት (UN-IOM) ዳይሬክተር ጄነራል ኤሚ ፖፕ ጋር ውይይት አድርገናል፡፡ ከተቋሙ ጋር በጋራ አብሮ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ላይም መክረናል፡፡

በዚህም የህገ ወጥ ፍልሰት ተግዳሮቶችን በዘላቂነት መፍታት እና የውጪ ሀገር ስራ ስምሪት ለዘላቂ ልማት የሚያበረክተዉን አስተዋፅዖ ማሳደግ በሚቻልባቸው የትብብር ሀሳቦች ላይ ከስምምነት ደርሰናል።

የዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ህገወጥ ፍልሰትን ከመከላከል፣ ከፍልሰት ተመላሾች እና ተፈናቃዮችን ከመደገፍ አኳያ ለሚያደርገው ድጋፍ ምስጋና ለማቅረብ እወዳለሁ ብለዋል።

መስከረም 28 ቀን 2017 ዓም
👍4👏1😁1