Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.76K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ጊቤ 2 የኃይል ማመንጫ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት 631 ነጥብ 53 ጌጋ ዋት ሰዓት ኃይል አመነጨ
*****
(ኢ ፕ ድ)

ጊቤ 2 የውኃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ በ2017 በመጀመሪያው ሩብ ዓመት 631 ነጥብ 53 ጌጋ ዋት ሰዓት ኃይል ማመንጨቱን የጣቢያው ሥራ አስኪያጁ አቶ ሹመት በላቸው ገለፁ።

ጣቢያው በሩብ ዓመቱ 565 ነጥብ 5 ጊጋ ዋት ሰዓት ኃይል ለማመንጨት አቅዶ 631 ነጥብ 53 ጌጋ ዋት ሰዓት በማምረት የዕቅዱን 111 ነጥብ 68 በመቶ ማሳካት ችሏል።

ጣቢያው በየወሩ በአማካይ እስከ 360 ነጥብ 59 ሜጋ ዋት ኃይል ሲያመርት እንደነበረም ሥራ አስኪያጁ ገልጸዋል።

የጣቢያው አራቱም ተርባይኖች ውሃን ለመቆጣጠር የሚያገለግለው የብረት አካል ወይም ኖዝል በመበላቱ የአንድ ተርባይን የማመንጨት አቅም ከ105 ሜጋ ዋት ወደ 25 ሜጋ ዋት ድረስ ቀንሶ እንደነበር አቶ ሹመት አስታውሰዋል፡፡

በራስ አቅም በመጠገን አራቱም ዩኒቶች ወደ ሥራ መግባታቸው ለአፈጻጸሙ ከፍ ማለት በምክንያትነት ጠቅሰዋል።

ጣቢያው በበጀት ዓመቱ 1 ሺ 859 ነጥብ 13 ጊጋ ዋት ሰዓት ኃይል ለማምረት አቅዷል።

በ2002 ዓም አገልግሎት መስጠት የጀመረው የጊቤ 2 የውኃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ በአራት ተርባይኖች 420 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም እንዳለው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ጥቅምት 15 ቀን 2017 ዓም

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@ethiopianpressagency...
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍41
"በፈተናዎች እየተገነባ የመጣ #ሠራዊት"‼️

በተለያዩ ሚዲያዎች ስለኢትዮጵያ ለሚሟገቱ አራት ኢትዮጵያውያንን የክብር አባል እውቅና ተበርክቷል።

117ኛው የመከላከያ ሠራዊት ቀን "በፈተናዎች እየተገነባ የመጣ #ሠራዊት" በሚል በመከላከያ ጠቅላይ መምሪያ ተከብሯል። በዕለቱ በተለያዩ ሚዲያዎች ስለኢትዮጵያ የሚሟገተውን መሐመድ ዓልአሩሲን ጨምሮ አራት ኢትዮጵያውያ የክብር አባል እውቅና ተበርክቷል።

ጥቅምት 15 ቀን 2017 ዓም

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@ethiopianpressagency...
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍51😁1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በማሌዢያ ኳላላምፑር የተደረገላቸው አቀባበል‼️

ጥቅምት 15 ቀን 2017 ዓም
👍10👎8
ኢትዮጵያ ከኤርትራ ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታ ተሰርዟል
*****
(ኢ.ፕ.ድ)

በቻን ማጣርያ የመጀመርያ ዙር ኢትዮጵያ ከ ኤርትራ ሊያደርጉት መርሐ ግብር ወጥቶላቸው የነበረው ጨዋታ ኤርትራ ከውድድሩ ራሷን ማግለሏን ካፍ በማሳወቁ ተሰርዟል።

ኢትዮጵያ በቀጣይ ዙር የሱዳን እና ታንዛንያ አሸናፊን እንደምትገጥም የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

ጥቅምት 16 ቀን 2017 ዓ.ም
👍12🥰2
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መልዕክት‼️

ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ኢብራሂም ብሎም የማሌዢያ ሕዝብና መንግሥት በቆይታችን ለሰጣችሁን ደማቅ አቀባበልና ፍቅር እናመሰግናለን።

ትብብራችንን ትኩረታቸውን በግብርና፣ ማዕድን፣ ማኑፋክቸሪንግና ታዳሽ ኃይል ላይ ባደረጉ የንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፎች ብሎም ሰፊ አድማስ ባላቸው ሌሎች ቁልፍ ሥራዎች ላይ ለማጠናከር ተስማምተናል።

የማሌዢያ የንግድ ማኅበረሰብ በፍጥነት በመስፋፋት ላይ ባለው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ ያለውን የኢንቨስትመንት እድል እንዲጠቀሙ አበረታታለሁ።

ጥቅምት 16 ቀን 2017 ዓም

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@ethiopianpressagency...
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍12😱1