Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.76K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
"በፈተናዎች እየተገነባ የመጣ #ሠራዊት"‼️

በተለያዩ ሚዲያዎች ስለኢትዮጵያ ለሚሟገቱ አራት ኢትዮጵያውያንን የክብር አባል እውቅና ተበርክቷል።

117ኛው የመከላከያ ሠራዊት ቀን "በፈተናዎች እየተገነባ የመጣ #ሠራዊት" በሚል በመከላከያ ጠቅላይ መምሪያ ተከብሯል። በዕለቱ በተለያዩ ሚዲያዎች ስለኢትዮጵያ የሚሟገተውን መሐመድ ዓልአሩሲን ጨምሮ አራት ኢትዮጵያውያ የክብር አባል እውቅና ተበርክቷል።

ጥቅምት 15 ቀን 2017 ዓም

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@ethiopianpressagency...
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍51😁1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በማሌዢያ ኳላላምፑር የተደረገላቸው አቀባበል‼️

ጥቅምት 15 ቀን 2017 ዓም
👍10👎8
ኢትዮጵያ ከኤርትራ ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታ ተሰርዟል
*****
(ኢ.ፕ.ድ)

በቻን ማጣርያ የመጀመርያ ዙር ኢትዮጵያ ከ ኤርትራ ሊያደርጉት መርሐ ግብር ወጥቶላቸው የነበረው ጨዋታ ኤርትራ ከውድድሩ ራሷን ማግለሏን ካፍ በማሳወቁ ተሰርዟል።

ኢትዮጵያ በቀጣይ ዙር የሱዳን እና ታንዛንያ አሸናፊን እንደምትገጥም የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

ጥቅምት 16 ቀን 2017 ዓ.ም
👍12🥰2
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መልዕክት‼️

ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ኢብራሂም ብሎም የማሌዢያ ሕዝብና መንግሥት በቆይታችን ለሰጣችሁን ደማቅ አቀባበልና ፍቅር እናመሰግናለን።

ትብብራችንን ትኩረታቸውን በግብርና፣ ማዕድን፣ ማኑፋክቸሪንግና ታዳሽ ኃይል ላይ ባደረጉ የንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፎች ብሎም ሰፊ አድማስ ባላቸው ሌሎች ቁልፍ ሥራዎች ላይ ለማጠናከር ተስማምተናል።

የማሌዢያ የንግድ ማኅበረሰብ በፍጥነት በመስፋፋት ላይ ባለው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ ያለውን የኢንቨስትመንት እድል እንዲጠቀሙ አበረታታለሁ።

ጥቅምት 16 ቀን 2017 ዓም

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@ethiopianpressagency...
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍12😱1
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
👍2
ኢትዮጵያ በብሪክስ ያላት ተሳትፎ ለጋራ እድገት አዎንታዊ ሚና ይጫወታል-አምባሳደር ኤቭጌኒ
*******
(ኢ ፕ ድ)

ኢትዮጵያ በብሪክስ ያላት ተሳትፎ ለጋራ እድገት አዎንታዊ ሚና እንደሚጫወት በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኤቭጌኒ ቴሬክሂን ገለጹ።

ከሰሞኑ በሩሲያ ካዛን ከተማ ለሦስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው 16ኛው የብሪክስ ጉባዔ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ምክክር በማድረግ መግባባቶች ላይ በመድረስ መጠናቀቁ ይታወሳል።

ኢትዮጵያ ጥምረቱን ከተቀላቀለች በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በተሳተፈችበት በዚሁ ጉባኤ ብሪክስ በቀጣይ ፍትኃዊ የዓለም ሥርዓት ለመፍጠር የሚያስችሉ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።

በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጌኒ ተሬክሂን ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ብሪክስ እንደ ብራዚል፣ ሩሲያ፣ ሕንድ፤ ቻይናና ደቡብ አፍሪካ በቀዳሚነት የጀመሩት ግዙፍ ጥምረት ነው ብለዋል።

እነዚህን አገራት ተከትሎ ወደ ጥምረቱ ከተቀላቀሉት ሃገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ መሆኗን ገልጸው፥ ማዕቀፍ ውስጥ ኢትዮጵያ መካተቷ ለጋራ እድገቷ አስተዋጽዖ ያበረክታል ነው ያሉት።

የብሪክስ አባል አገራት በምጣኔ ኃብትና በሕዝብ ለሕዝብ በመሳሰሉ ጉዳዮች በጋራ የሚሰሩ ሲሆን ይህም የአባል አገራት ሁለንተናዊ እድገት ለማሳለጥ የሚያስችላቸው መሆኑን አንስተዋል።

ኢትዮጵያ በብሪክስ ያላት ተሳትፎ ለራሷ ምጣኔ ኃብታዊ እድገት የራሱ አስተዋጽዖ እንደሚያበረክት ገልጸው፥እንዲሁም ኢትዮጵያ ለብሪክስ ዓላማ መሳካት የራሷን አስተዋጽኦ እንደምታበረክትም ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

የብሪክስ አባል አገራት የዓለምን አንድ ሦስተኛው ኢኮኖሚና 50 በመቶ የሚጠጋውን የዓለም ሕዝብ የያዙ ሲሆን አሁን ላይ ከ30 በላይ አገራት ብሪክስን ለመቀላቀል ጥያቄ አቅርበዋል።

ይህንንም ተከትሎ ኅብረቱ ወደፊት አድማሱን ይበልጥ እያሰፋ እንደሚቀጥል ነው ከወዲሁ ከፍተኛ ግምት የተሰጠው።

በዚህም ኅብረቱ በቀጣይ የኢኮኖሚ ትብብርን በማጠናከርና የሕዝብ ለሕዝብ ትስስርን በማሳደግ ሚዛናዊ የዓለም ሥርዓት ለመፍጠር አይነተኛ ሚና እንደሚጫወት ይጠበቃል።

ጥቅምት 16 ቀን 2017 ዓም

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@ethiopianpressagency...
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍2🔥21
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የኳላላምፑር የልማት ስራዎች ጉብኝት በፎቶ‼️
👍11