Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.76K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 11ኛ መደበኛ ስብሰባው‼️

👉 በኢትዮጵያ የውጭ ባንኮች እንዲሳተፉ የሚፈቅደውን የባንክ ስራ ረቂቅ አዋጅ አፅድቋል፣

👉 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅን አፅድቋል ፣

ብሔራዊ ባንክ የውጭ ባንኮችን ለመቆጣጠርና ለማስተዳደር የሚያስችል የአሰራር ስርዓት መዘርጋት እንደሚገባ የምክር ቤት አባላት አሳስበዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ፤ የባንክ ሥራ ረቂቅ አዋጅ በፋይናንስ ዘርፉ ዓለም አቀፍ ተወዳደሪ ለመሆንና ኢንቨስትመንትን ለማሳብ ያግዛል።

የውጭ ባንኮች ወደ ሀገር ውስጥ ይገባሉ ማለት በጋርና በሽርክና ጭምር ከሀገር ውስጥ ባንኮች ጋር በትብብር ይሰራሉ። የባንክ ሥራ ረቂቅ አዋጁ ለሀገር ውስጥ ባንኮችም የዕውቀት ሽግግርን ይፈጥራል።

የሀገር ውስጥ ባንኮችም አቅማቸውን በማጎልበት ተወዳደሪ ለመሆን ሰብሰብ ብለው የፋይናንስ አቅማቸውን ማጠናከር ይጠበቅባቸዋል።

የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና የባንክ ስራ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ ለምክር ቤቱ ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ ቀርቦ መፅደቁን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መረጃ ያመለክታል።

ታህሳስ 8 ቀን 2017 ዓም

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@ethiopianpressagency...
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍122👎1
አየር መንገዱ “ኤር ኮንጎ” የሚል ስያሜ የተሰጠው አየር መንገድ አቋቁሞ ስራ አስጀመረ
*****
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት ጋር በጋራ በመሆን “ኤር ኮንጎ” የሚል ስያሜ የተሰጠው አየር መንገድ አቋቁሞ በይፋ ስራ አስጀመረ።

ኤር ኮንጎ በሁለት ቦይንግ 737 አውሮፕላኖች በሀገሪቱ ውስጥ ባሉ ሰባት ኤርፖርቶች በረራ በማድረግ አገልግሎት መጀመሩን የአየር መንገዱ መረጃ አመላክቷል።

ጥምረቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ራዕይ 2035 አንዱ አካል ሲሆን ከዚህም በፊት በሎሜ አስካይ አየር መንገድ፣ በሊሎንግዌ የማላዊ አየር መንገድ እንዲሁም በሉሳካ የዛምቢያ አየር መንገድን በጋራ ማቋቋሙ ይታወሳል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
👍10
የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ.....‼️

✍️ በሁለት ቢሊዮን ብር ወጪ የማሰልጠኛ መሰረተ ልማት ግንባታ ያከናውናል፣

✍️ ከጋቦን የመጡ ከ300 በላይ ሰልጣኞችን ተቀብሎ እያሰለጠነ ይገኛል፣

✍️ በተያዘው በጀት ዓመት ከሁለት ሺህ በላይ ሰልጣኞችን በአቪዬሽን ዘርፍ ለማሰልጠን አቅዷል፣
******
(ኢ ፕ ድ)

የኢትዮጵያ ሲቪል #አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የመማር ማስተማር አቅሙን ለማሳደግ የተለያዩ የማስልጠኛ መሰረተ ልማቶችን እየገነባ መሆኑን አስታወቀ፡፡ ግንባታው በ12 ወራት ውስጥ ይጠናቀቃል።

ከጋቦን የመጡ ከ300 በላይ ሰልጣኞችን ተቀብሎ በተለያዩ የአቪዬሽን ሙያዎች እያሰለጠነም ይገኛል።

የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ካሴ ይማም ለኢፕድ እንደገለጹት፤ ዩኒቨርስቲው ከኢትዮጵያ አልፎ በየዓመቱ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት በርካታ ተማሪዎችን በመቀበል አሰልጥኗል።

በተያዘው በጀት ዓመት ከሁለት ሺህ በላይ ሰልጣኞችን በተለያዩ የአቪዬሽን ዘርፍ ለማሰልጠን አቅዶ እየሰራ መሆኑን ጠቁመው በቅርቡ ከተመረቁት ተማሪዎች ከኢትዮጵያና ከ12 #አፍሪካ አገራት የተውጣጡ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው በአብራሪነት፣ በአውሮፕላን ቴክኒሺያንነት፣ በበረራ መስተንግዶና በሌሎች የስልጠና መስኮች በዓመት እስከ አራት ሺህ የማሰልጠን አቅም እንዳለው ጠቁመዋል፡፡

በአጠቃላይ ከኢትዮጵያና ከተለያዩ የዓለም ሀገራት የተውጣጡ ከ20 ሺህ በላይ ሰልጣኞችን ማስመረቁ ይታወሳል።

በሄለን ወንድምነው

ታህሳስ 8 ቀን 2017 ዓም
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍62
እንደምን አደሩ‼️
#አዲስ_ዘመን_ዛሬ‼️
የታህሳስ 9 ቀን 2017 ዓ.ም አዲስ ዘመን ጋዜጣ
https://press.et/?p=143199
መልካም ቀን!
👍1
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍1
#የሌማት_ትሩፋት

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በ2015 ሀገር በቀሉን የሌማት ትሩፋት መርሐግብር ያስጀመሩ ሲሆን የአራት አመታት የሥራ እቅድ የወተትና ወተት ተዋፅዖ፣ ዶሮ፣ የእንቁላል፣ የማርና የአሳ ምርት ብሎም ምርታማነት ማሳደግ ላይ ያተኮረ ነው።

በትልቅ ደረጃ ከሚመረቱት ባሻገር በአነስተኛ የመኖሪያ ቤት ደረጃ የሚደረጉ እንደ የጓሮ ዶሮ ርባታ፣ አነስተኛ የአሳ ምርት ሥራ እና የንብ ማነብ እንቅስቃሴዎችን የመደገፍ ሥራም ይሰራል። እነዚህ ሥራዎች በምግብ ራስን በመቻልና የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦትን በቤት እና በሀገር ደረጃ በማረጋገጥ ረገድ ወሳኝ
ሚና ይጫወታሉ።

#PMOEthiopia
👍31👎1
#ህዝባዊ_የድጋፍ_ሰልፍ_በአማራ_ክልል #የተማሪዎች መልዕክት‼️

👉 ደብተርና ብዕር እንጅ ጥይት አንፈልግም፣

👉 እጃችሁን ከትምህርት ቤታችንና ከህልማችን ላይ አንሱ፣

👉 መማር እንፈልጋለን

👉 ህፃናት የፅንፈኛ ኃይሎች መነገጃ አይደሉም፣

👉 መንግሥት ት/ቤቶችን ከፅንፈኛ ቡድን ጥቃት ይጠብቅልን፣

👉 የነገ ሀገር ተረካቢ ተማሪዎች ያለምንም ስጋት ወደ ትምህርት ገበታቸው ይመለሱ፣

👉 ህፃናትን ከትምህርት ገበታቸው ማስቀረት የፅንፈኝነት ጥግ ነው፣
👍82😁2🍌1