Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት‼️

ከህጻንነታቸዉ ጀምሮ በኮልፌ የወንዶች ልጆች ማሳደጊያ እና በቀጨኔ የሴቶች ማሳደጊያ ማዕከል ካሳደግናቸው ልጆቻችን መካከል ሰባቱን ለወግ ለማዕረግ አብቅተን የጋብቻ ስነ ስርዓታቸውን ለመፈጸም ያበቃን ፈጣሪ የተመሰገነ ይሁን። ሙሽሮች እንኳን ደስ ያላችሁ!

እንኳን ፈጣሪ በህይወት ውጣ ውረድ ውስጥ ረድቷችሁ ለዚህ ለተባረከ እና ለተቀደሰ የህይወታችሁ ምዕራፍ ቀን አደረሳችሁ። መልካም ጋብቻ ይሁንላችሁ!

የከተማ አስተዳደራችን ወላጅ ለሌላቸዉ ወላጅ እና ቤተሰብ በመሆን አሳድጎ፣ ለወግ ለማዕረግ እንዲበቁ ከማድረግ በተጨማሪ በቀጣይ የህይወታቸው ምዕራፍ የስራ እድል በመፍጠር ለሌሎች ምሳሌ የሚሆን ዉጤታማ ህይወት እንዲኖራቸው እየተመኘን በዚህ በተቀደሰ ስራ የተሳተፉትን ሁሉ ላመሰግናቸው እወዳለሁ።

በድጋሚ መልካም ጋብቻ፤ ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ።

ጥር 18 ቀን 2017 ዓም
👍5👏1
ጂማን ዓለም አቀፍ ከተማ ለማድረግ ልንከተላቸው የሚገቡ ዐሥር አቅጣጫዎች
******
(ኢ ፕ ድ)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጂማን ዓለም አቀፍ ከተማ ለማድረግ የሚያስችሉ አቅጣጫዎች አስቀመጡ።

በዚህም፤

1. ቡናን በጥራትና በስፋት ማምረት፤ በተለይ የጥሪኝ ቡና ስፔሻሊቲን ማስፋፋት፣

2. ልዩ ልዩ ኦርጋኒክ የሻይ ቅጠል ዝርያዎችን በልዩ ብራንድ ጂማ ላይ ማቀነባበር፣

3. የተፈጥሮ ማዳበሪያን በማምረትና በመጠቀም፣ ልዩ ልዩ ፍራፍሬዎችን ማምረት፣ ማሸግና መላክ፣

4. የከብት ወተትና ሥጋ፤ እንዲሁም የዶሮ ዕንቁላል እና ሥጋን በጥራትና በብዛት በማምረት አሽጎ መላክ፣

5. ልዩ ልዩ ቅመማ ቅመም ለውጭ ገበያ በሚመጥን መልኩ ማቀነባበር፣ ማሸግና መላክ፣

6. ልዩ ልዩ የእንጨት ሥራዎችን በዓለም አቀፍ ደረጃ፣ በፋብሪካዎች በጥራት ማምረት፣

7. የሸክላ ፋብሪዎችን በማስፋፋት፤ ለወለል፣ ለግርግዳ እና ለጣራ የሚያገለግሉ የግንባታ ምርቶችን ወደ ውጭ መላክ፣

8. የጂማንና የአካባቢዋን ታሪካዊ፣ ተፈጥሯዊ፣ ሃይማኖታዊና ባህላዊ ጸጋዎችን በማልማትና በማስተሣሠር የቱሪዝም መዳረሻ ማድረግ፣

9. የጂማ ሕዝብ ከጥንት ጀምሮ የሚታወቅበትን ሰላሙን እና እንግዳ ተቀባይነቱን ማጽናት፣

10. ጎጂ ማኅበራዊ ልማዶችን እና ደካማ የሥራ ባህልን ማሻሻል፣

ጥር 2017 ዓም
👍86👏1
አትሌት ወርቅነሽ ኢዴሳ የኦሳካ ማራቶን ውድድርን አሸነፈ
*

(ኢ ፕ ድ)
አትሌት ወርቅነሽ ኢዴሳ በጃፓን ኦሳካ በተካሄደ የሴቶች ማራቶን ውድድር አሸናፊ ሆነች።

አትሌት ወርቅነሽ ኢዴሳ ርቀቱን 2 ሰዓት 20 ደቂቃ 59 ሰከንድ በመግባት አንደኛ በመውጣት አሸንፋለች ።

በተያያዘ  በስፔን ሚጃ ቴራሳ ግማሽ ማራቶን ኢትዮጵያዊያን  አትሌቶች በሁለቱም ፆታ አሸንፏል ።

በወንዶች  አትሌት ሚኪያስ ባረጋ 1 ሰዓት ከ02 ደቂቃ ከ18 ሴኮንድ  በመግባት አሸንፏል ።

አትሌት ሚኪያስ ባረጋ የገባበት ሰዓት የቦታው ክብረወሰን ሆኖ ተመዝግቧል።

በሴቶች አትሌት ኪሮስ ሙዑዝ  በቀዳሚነት ስታጠናቅቅ አትሌት ገነት ሳህለ ሁለተኛ ወጥታለች ።

ጥር 18 ቀን 2017 ዓ.ም
👍6👏1
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ውሳኔዎችን አሳለፈ
***
(ኢ ፕ ድ)

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ባካሄደው የ4ኛ ዓመት 6ኛ መደበኛ ስብሰባው በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

በዚሁም መሰረት ካቢኔው የሀገሪቱን ዲፕሎማሲ ታሳቢ ያደረገ የኤምባሲዎች የመሬት ጥያቄንና የከተማዋን የኢኮኖሚ እንቅቃሴ ለሚያጎለብቱ፣ ሰፊ የስራ እድል እየፈጠሩ ላሉ፣ የዉጭ ምንዛሬ እያስገኙ ላሉ የአምራች ኢንዱስትሪዎች የማምረቻ ማስፋፊያ ቦታ ጥያቄዎችን መርምሮ ውሳኔ አሳልፏል።

ጥር 19 ቀን 2017 ዓም
👍9👏1
የብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ከጥር 23 እስከ 25 ድረስ ይካሄዳል

👉 የብልጽግና ፓርቲ ጉባኤ በሶስት ምክንያቶች ዓለም አቀፍ ትኩረት ይስባል
******
(ኢ ፕ ድ)

የብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ከጥር 23 እስክ 25 ቀን 2017 ዓም "ከቃል እስከ ባህል" በሚል መሪ ሐሳብ እንደሚካሄድ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንትና የዋና ጽህፈት ቤት ሃላፊ አደም ፋራህ አስታወቁ።

የብልጽግና ፓርቲ ጉባኤ በሶስት ምክንያቶች ዓለም አቀፍ ትኩረት ይስባል ሲሉም ልጸዋል።

አንደኛ ምክንያት ብልጽግና ፓርቲ ትልቅ ሕዝብ ትልቅ ታሪክ ያላት ታላቅ አገር የሚመራ ገዥ ፓርቲ በመሆኑ ነው። ጉባኤ የሚወሰኑና የሚቀመጡ አቅጣጫዎች ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ሁኔታ ላይ በከፍተኛ ደረጃ ተጽዕኖ የሚፈጥር በመሆኑ ነው፡፡

ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ የብልጽግና ፓርቲ በራሱ ግዙፍ ፓርቲ በመሆኑ ነው፡፡ ፓርቲው መለያውን አካታችነትን፣ ሚዛናዊነትን እና አገር በቀል እሳቤን አድርጎ ትልቅ ሕልምና ርዕይ አንግቦ የሚንቀሳቀስ ግዙፍ ፓርቲ በመሆኑም ጭምር እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

በሶስተኛ ደረጃ በሁሉም ዘርፎች ፓርቲው ስኬታማ ጉዞ እያደረገ በብዙዎች ዘንድ ኢትዮጵያን አፍሪካዊት የብልጽግና ተምሳሌት እንደሚያደርግ የሚጠበቅ ትልቅ ተስፋ የተጣለበት ፓርቲ በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡

ፓርቲው በሚቀጥሉት ዓመታት ሊያያሳካቸው ያሰባቸውን ስኬቶች በተመለከተ አቅጣጫዎች የሚቀመጡበትና እስከቀጣዩ ጉባኤ ድረስ ፓርቲውን የሚመሩ ከፍተኛ አመራሮች የሚመረጡበት ወሳኝ መድረክ እንደሆነ ገልጸዋል።

በጉባኤው የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች፣ ከውጭ ሀገራት 15 እህት ፓርቲዎች ተሳታፊ እንደሚሆኑ ተናግረዋል።

በጉባኤው ባለፈው መደበኛ ጉባኤው የተላለፉ ውሳኔዎችና ፓርቲው ያሰቀመጣቸው አቅጣጫዎች ይገመገሙበታል። በቀጣይም ሊሰሩ የሚገባቸው አቅጣጫና ውሳኔ ይተላለፍበታል ተብሏል።

ፓርቲው በአሁኑ ወቅት 15 ነጥብ 7 ሚሊየን አባላት ያሉት እንደሆነ ይታወቃል።

በአስቴር ኤልያስ

ጥር 19 ቀን 2017 ዓም
👍13👎2😁1
የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት‼️

በብዙ የማህበራዊ ስራዎች ላይ ተሳትፎ በማድረግ ላይ የሚገኘው MNRC ለኮሪደር ልማት ስራችን ግልጋሎት የሚውል ሶስት የከርብ ስቶን መስሪያ ማሽኖችን በድጋፍ አበርክቶልናል።

ይህ ድጋፍ የነበረውን የከርብ ስቶን ማሽን ችግር በማቃለል የተሻለ ጥራት ያለዉ ስራ በፍጥነት መስራት ያስችለናል።
የMNRC ባለቤት ወ/ሮ ማህደር ገ/መድን ላደረጉልን ድጋፍ በከተማ አስተዳደራችን ስም ላመሰግናቸው እወዳለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

ጥር 19 ቀን 2017 ዓም
6👍5👏1
ኢትዮጵያና ደቡብ አፍሪካ በብሪክስ ማዕቀፍ በትብብር ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ገለፁ
****
(ኢ ፕ ድ)

ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ(ዶ/ር) በኢትዮጵያ የደቡብ አፍሪካ አምባሳደር ኢኖንሴባ ሎሲን ጋር በሁለትዮሽና አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል። የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት የበለጠ ማጠናከር እንደሚገባም ተጠቅሷል።

ኢትዮጵያና ደቡብ አፍሪካ ጠንካራ የሁለትዮሽ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት ናቸው፣ አፍሪካ ኀብረትን ጨምሮ በበርካታ ባለብዙ መድረኮች ላይም በትብብር እንደሚሰሩ ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የደቡብ አፍሪካ አምባሳደር ኢኖንሴባ ሎሲ በበኩላቸው ግንኙነቱን ለማሳደግ እንደሚሠሩ ገልፀው፤ ከሁለትዮሽ ግንኙነት ባሻገር በአፍሪከ ህብረት፣ በብሪክስ ማዕቀፍና በሌሎች ዓለም ዓቀፍ መድረኮች የጋራ ጥቅሞቻቸውን ለማስጠበቅ በትብብር ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀዋል።

በመጪው ወር ለሚካሄደው ለ38ኛ የአፍሪካ ኀብረት የመሪዎች ጉባኤ ስኬትም በትብብር እንደሚሰሩ መግለፃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

ጥር 19 ቀን 2017 ዓም
👍2👏1
ባለፉት 6 ወራት ከ590 ሚሊዮን ዶላር በላይ ኢንቨስትመንት መሳብ መቻሉ ተገለጸ
****
(ኢ ፕ ድ)

ባለፉት 6 ወራት 597 ሚሊየን ዶላር በላይ ኢንቨስትመንት ያስመዘገቡ ባለሃብቶች ወደ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችና ድሬዳዋ ነጻ የንግድ ቀጣና መግባታቸውን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አስታውቋል፡፡

የኮርፖሬሽኑ የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽንና ማርኬቲንግ ስራ አስፈጻሚ አቶ ዘመን ጁነዲ፤ ከ80 በላይ ኢንቨስትመንቶች ኮርፖሬሽኑ ወደ ሚያስተዳድራቸው ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች መሳባቸውን ገልጸዋል።

በተሳቡት ኢንቨስትመንቶች 14 የማምረቻ ሼድና ከ70 ሄክታር በላይ የለማ መሬት ለባለሃብቶቹ ተላልፏል።

ኢንቨስትመንቶቹ በመቐለ፣ ቦሌ ለሚ፣ ቂሊንጦ፣ ኮምቦልቻ፣ ድሬዳዋ ልዩ ነፃ ንግድ ቀጠና፣ ጅማና ሰመራ ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች ውስጥ የሚሰማሩ መሆናቸውን የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የተመሰረተበትን 10ኛ ዓመትና የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 6 ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት የግምገማ መድረክ በድሬዳዋ ከተማ ተካሂዷል፡፡

#ኢንቨስትመንት #ልዩ_የኢኮኖሚ_ዞኖ

ጥር 19 ቀን 2017 ዓም
👍31👏1