Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የጅማ አባ ጅፋር ቤተ መንግስት እድሳትና በጅማ የገበታ ለትውልድ ፕሮጄክት ጉብኝት

#PMOEthiopia
6👎2👏2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"ያየነውን ለማሳየት እንተጋለን"
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
**
(ኢ ፕ ድ)

ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሀብት የታደለች ሀገር ናት፤ ቢሰራባቸው በዓለም እያየን ከምንደነቅባቸው ስፍራዎች በዕጅጉን የላቁ ውበት ያላቸው ስፍራዎች በሁሉም የኢትዮጵያ አከባቢዎች መኖራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ።

#ጅማ_አባ_ጅፋር_ቤተመንግስት_ዕድሳት #ገበታለትውልድ

ጥር 17 ቀን 2017 ዓም
👍9👏3
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍4
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የአጋሮና የበሻሻ ህዝብ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያደረገው አቀባበል‼️

#PMOEthiopia
👍7🖕4
አትሌት ማርታ የ3000 ሜትር ክብረ ወሰን በመስበር አሸነፈች
***
(ኢ ፕ ድ)

በካዛኪስታን ዋና ከተማ አስታን በተካሄደ የ3 ሺህ ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር አትሌት ማርታ አለማየሁ ክብረ ወሰን በመስበር አሸንፋለች።

አትሌት ጉሚ ሽቶ እና አክሱማዊት አምባዬ ውድድሩን ሁለተኛና ሶስተኛ በመሆን አጠናቅቀዋል፡፡

አትሌት ማርታ ርቀቱን ለመጨረስ 8 ደቂቃ ከ39 ሰኮንድ የወሰደባት ሲሆን ውጤቱም ከ18 ዓመት በታች ባሉ አትሌቶች ፈጣኑ ሰዓት ሆኖ በክብረ ወሰንነት መያዙን የወርልድ አትሌቲክስ መረጃ ያመለክታል።

ጥር 17 ቀን 2017 ዓም
11👍4👏1
የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት‼️

ከህጻንነታቸዉ ጀምሮ በኮልፌ የወንዶች ልጆች ማሳደጊያ እና በቀጨኔ የሴቶች ማሳደጊያ ማዕከል ካሳደግናቸው ልጆቻችን መካከል ሰባቱን ለወግ ለማዕረግ አብቅተን የጋብቻ ስነ ስርዓታቸውን ለመፈጸም ያበቃን ፈጣሪ የተመሰገነ ይሁን። ሙሽሮች እንኳን ደስ ያላችሁ!

እንኳን ፈጣሪ በህይወት ውጣ ውረድ ውስጥ ረድቷችሁ ለዚህ ለተባረከ እና ለተቀደሰ የህይወታችሁ ምዕራፍ ቀን አደረሳችሁ። መልካም ጋብቻ ይሁንላችሁ!

የከተማ አስተዳደራችን ወላጅ ለሌላቸዉ ወላጅ እና ቤተሰብ በመሆን አሳድጎ፣ ለወግ ለማዕረግ እንዲበቁ ከማድረግ በተጨማሪ በቀጣይ የህይወታቸው ምዕራፍ የስራ እድል በመፍጠር ለሌሎች ምሳሌ የሚሆን ዉጤታማ ህይወት እንዲኖራቸው እየተመኘን በዚህ በተቀደሰ ስራ የተሳተፉትን ሁሉ ላመሰግናቸው እወዳለሁ።

በድጋሚ መልካም ጋብቻ፤ ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ።

ጥር 18 ቀን 2017 ዓም
👍5👏1
ጂማን ዓለም አቀፍ ከተማ ለማድረግ ልንከተላቸው የሚገቡ ዐሥር አቅጣጫዎች
******
(ኢ ፕ ድ)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጂማን ዓለም አቀፍ ከተማ ለማድረግ የሚያስችሉ አቅጣጫዎች አስቀመጡ።

በዚህም፤

1. ቡናን በጥራትና በስፋት ማምረት፤ በተለይ የጥሪኝ ቡና ስፔሻሊቲን ማስፋፋት፣

2. ልዩ ልዩ ኦርጋኒክ የሻይ ቅጠል ዝርያዎችን በልዩ ብራንድ ጂማ ላይ ማቀነባበር፣

3. የተፈጥሮ ማዳበሪያን በማምረትና በመጠቀም፣ ልዩ ልዩ ፍራፍሬዎችን ማምረት፣ ማሸግና መላክ፣

4. የከብት ወተትና ሥጋ፤ እንዲሁም የዶሮ ዕንቁላል እና ሥጋን በጥራትና በብዛት በማምረት አሽጎ መላክ፣

5. ልዩ ልዩ ቅመማ ቅመም ለውጭ ገበያ በሚመጥን መልኩ ማቀነባበር፣ ማሸግና መላክ፣

6. ልዩ ልዩ የእንጨት ሥራዎችን በዓለም አቀፍ ደረጃ፣ በፋብሪካዎች በጥራት ማምረት፣

7. የሸክላ ፋብሪዎችን በማስፋፋት፤ ለወለል፣ ለግርግዳ እና ለጣራ የሚያገለግሉ የግንባታ ምርቶችን ወደ ውጭ መላክ፣

8. የጂማንና የአካባቢዋን ታሪካዊ፣ ተፈጥሯዊ፣ ሃይማኖታዊና ባህላዊ ጸጋዎችን በማልማትና በማስተሣሠር የቱሪዝም መዳረሻ ማድረግ፣

9. የጂማ ሕዝብ ከጥንት ጀምሮ የሚታወቅበትን ሰላሙን እና እንግዳ ተቀባይነቱን ማጽናት፣

10. ጎጂ ማኅበራዊ ልማዶችን እና ደካማ የሥራ ባህልን ማሻሻል፣

ጥር 2017 ዓም
👍86👏1
አትሌት ወርቅነሽ ኢዴሳ የኦሳካ ማራቶን ውድድርን አሸነፈ
*

(ኢ ፕ ድ)
አትሌት ወርቅነሽ ኢዴሳ በጃፓን ኦሳካ በተካሄደ የሴቶች ማራቶን ውድድር አሸናፊ ሆነች።

አትሌት ወርቅነሽ ኢዴሳ ርቀቱን 2 ሰዓት 20 ደቂቃ 59 ሰከንድ በመግባት አንደኛ በመውጣት አሸንፋለች ።

በተያያዘ  በስፔን ሚጃ ቴራሳ ግማሽ ማራቶን ኢትዮጵያዊያን  አትሌቶች በሁለቱም ፆታ አሸንፏል ።

በወንዶች  አትሌት ሚኪያስ ባረጋ 1 ሰዓት ከ02 ደቂቃ ከ18 ሴኮንድ  በመግባት አሸንፏል ።

አትሌት ሚኪያስ ባረጋ የገባበት ሰዓት የቦታው ክብረወሰን ሆኖ ተመዝግቧል።

በሴቶች አትሌት ኪሮስ ሙዑዝ  በቀዳሚነት ስታጠናቅቅ አትሌት ገነት ሳህለ ሁለተኛ ወጥታለች ።

ጥር 18 ቀን 2017 ዓ.ም
👍6👏1