Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ለዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ወሳኝ መሰረት የጣሉ ተግባራት ተከናውነዋል- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
****
(ኢ ፕ ድ)

ባለፉት የለውጥ ዓመታት ለዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ወሳኝ መሰረት የጣሉ ተግባራት ተከናውነዋል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

ዛሬ የኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ እና ውጥኖችን የተመለከተ ኤግዚቢሽንና ዐውደ ጥናት አካሂደናል ብለዋል።

መንግሥት ከለውጡ ማግሥት 2012 ዓ.ም ጀምሮ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ሀገራችን የቴክኖሎጂ ዕድገት ዕድሎችን እንድትጠቀም የሚያስችሉ ተግባራትን አከናውኗል ብለዋል።

የዲጂታል መሠረተ ልማት በመሥፋፋቱ የፋይናንስና የክፍያ ስርዓት በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ መሆኑን ተናግረዋል።

የመንግሥት አገልግሎቶችን የማዘመንና ወደ ዲጂታል የማሸጋገር እንዲሁም የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ መጨመሩንም ገልጸዋል።

የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስራዎች የተቀናጁ፣ ደህንነታቸው የተጠበቀ፣ የሃብት ብክነትን የማያስከትሉ፣ የዜጎቻችንን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡና ፈጣን ለውጥ የሚያመጡ እንዲሆኑ መንግሥት የጀመረውን ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል።

የመጀመሪያውን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ትግበራ እያጠናቀቅን በመሆኑም በቀጣይ 5 ዓመታት ስራ ላይ የሚውል የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ዝግጅት እያጠናቀቅን እንገኛለን ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።

ጥር 19 ቀን 2017 ዓም
👍5👏1
ኢትዮጵያ በአፍሪካ የጎብኚዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ከጨመረባቸው ሀገራት ቀዳሚ ደረጃ ላይ ተቀመጠች
*******
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ባለፉት አምስት አመታት ውስጥ የጎብኚዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ከጨመረባቸው ሀገራት ቀዳሚ መሆኗን የተባበሩት መንግስታት የዓለም ቱሪዝም ድርጅት መረጃ አመልክቷል።

ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሞሮኮንና ግብጽን በማስከተል የጎብኝዎች ቁጥር ከነበረበት መጠን በ40 በመቶ ዕድገት አሳይቷል።

ከዓለም ኳታርን፣ ኤል ሳልቫዶርን፣ አልቤንያን፣ ሳዑዲዓረቢያንና ኩራካዎን በመከተል ስድስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።

እአአ ከ2019 ወዲህ ባስመዘገበችው የቱሪስት ፍሰት መጠን ኢትዮጵያ ከአለም ሃገራት ስድስተኛ፤ ከአፍሪካ ደግሞ ሞሮኮና ግብፅን በማስከተል ቀዳሚ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

#ምድረቀደምት #ኢትዮጵያ #ቱሪዝም #ቱሪስት

ጥር 19 ቀን 2017 ዓም
👍16😁2👏1
በህገ-ወጥ መንገድ ተከማችቶ የነበረ ከ2 ሺህ ሊትር በላይ ቤንዚን ተያዘ
*****
በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 በህገ-ወጥ መንገድ በአንድ ኮንቴነር ውስጥ በጀሪካን ተሸሽጎ የነበረ 2 ሺህ 360 ሊትር ቤንዚን ከሁለት ግለሰቦች ጋር በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀ፡፡

መንግስት የነዳጅ አቅርቦት ሰንሰለቱ በህጋዊ መንገድ እንዲደረግና ግብይቱም በቴሌ ብር ብቻ እንዲሆን ከማድረግ ጀምሮ በርካታ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ይታወቃል።

ፖሊስ ባደረገው ክትትል በህገወጥ መንገድ በአንድ ኮንቴነር ውስጥ በጀሪካን ተሸሽጎ የነበረ 2 ሺህ 360 ሊትር ቤንዚል ከሁለት ግለሰቦች ጋር በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ  ተገልጿል።

ህብረተሰቡ በመሰል የወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ ግለሰቦችን ሲመለከት ለፖሊስ ጥቆማ እንዲሰጥ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።

ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የነዳጅ ውጤቶችን ግብይት ሥርዓት አዋጅን ማፅደቁ ይታወሳል።

አዋጁ የነዳጅ ውጤቶች ግብይት ከአስመጪው ጀምሮ እስከ መጨረሻው ተጠቃሚ ድረስ ቴክኖሎጂ የተደገፈ፤ የግብይት ሰንሰለት ውስጥ እየታዩ ያሉ ሕገ-ወጥ ተግዳሮቶችን ለመቆጣጠር የሚያስችልና ሕጋዊ የነዳጅ ውጤቶች የግብይት ሥርዓትን ለማስፈን ያስችላል ተብሏል።

#አዋጅ #የነዳጅ_ውጤቶች #የችርቻሮ_መሸጫ_ዋጋ

ጥር 19 ቀን 2017 ዓም
👍6👏1
በሀረሪ ክልል ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ 41 ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፍቃድ ተሰጠ
*******
(ኢ ፕ ድ)
በሀረሪ ክልል ባለፈው ስድስት ወራት ከ 2 ቢሊዬን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ 41 ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፍቃድ መሰጠቱን የክልሉ የኢንተርፕራይዞች ልማትና ኢንዱስትሪ ቢሮ ገለፀ።
👍3
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የአፍሪካ ኢነርጂ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ዳሬ ሰላም ገቡ
****
(ኢ ፕ ድ)

የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች የሚሳተፉበት የኢነርጂ ጉባዔ በነገው ዕለት በታንዛኒያ ይካሄዳል።

ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በጉባኤው ላይ ለመሳተፍ ታንዛኒያ ዳሬ ሰላም ገብተዋል። ዳሬ ሰላም ጁሊየስ ኒዬሬሬ አየር ማረፊያ ሲደርሱ በሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ጉባዔው እስከ ፈረንጆቹ 2030 ድረስ ለ300 ሚሊዮን አፍሪካውያን የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽ በሚደረግበት መንገድ ላይ እንደሚመክር ኢቢሲ ዘግቧል።

ለ600 ሚሊዮን አፍሪካውያን የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽ አለመሆኑን መረጃዎች ያመላክታሉ።

ጥር 19 ቀን 2017 ዓም
👍16👏1
ህይወት ፋና ሪፈራል ሆስፒታል ከ300 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የካንሰር ህክምና እየሰጠ እንደሚገኝ ተገለጸ
******
(ኢ ፕ ድ)

ህይወት ፋና ሪፈራል ሆስፒታል ከ300 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የካንሰር ህክምና እየሰጠ እንደሚገኝ የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና የማህበረሰብ ተሳትፎ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ይስሐቅ የሱፍ ገለፁ።

የካንሰር ህክምና ማዕከሉ ለምስራቁ የሀገሪቷ ክፍል አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና የማህበረሰብ ተሳትፎ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ይስሐቅ የሱፍ ለኢፕድ እንደገለፁት ከ300 እስከ 400 ለሚሆኑ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ታማሚዎች አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡

ሶማሊያ እና ጅቡቲ ሀገራት የካንሰር ታማሚዎች በሆስፒታሉ የህክምና አገልግሎት እያገኙ መሆኑን አብራርተዋል።

በሆስፒታሉ የኬሞ ቴራፒና የጨረር ህክምና አገልግሎት ለካንሰር ታካሚዎች እየተሰጠ ነው ያሉት ዶክተር ይስሐቅ፤ የህክምና አገልግሎት አሰጣጡ እንዲሻሻል ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

ከጤና ዘርፍ ባለፈ የማህበረሰብ አቀፍ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

በአማን ረሺድ

ጥር 20 ቀን 2017 ዓም
👍12
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ ዶ/ር ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡት የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ካነሷቸው ዋና ዋና ሀሳቦች‼️

👉 ከቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም 913 ሚሊዮን ዶላር፤ ከአበባ አትክልትና ፍራፍሬ 263 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል፣

👉 ከእንስሳትና እንስሳት ተዋፅዖ 54 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል፣

👉 አንድ ነጥብ 92 ሚሊዮን ላሞችን ማዳቀል ተችሏል፣

👉 የወተት ምርት 7 ቢሊዮን ሊትር ወተት ማምረት ተችሏል፣

👉 የእንቁላል ምርትን 4 ቢሊዮን ለማምረት ታቅዶ 4 ነጥብ 5 ቢሊዮን ተገኝቷል፣

👉 116 ሺህ ቶን የዶሮ ሥጋ ለማምረት ታቅዶ 105 ሺህ ቶን ማምረት ተችሏል፣

👉 102 ሺህ ቶን የዓሣ ምርት ለማምረት ታቅዶ 91 ሺህ ቶን የዓሣ ምርት ማምረት ተችሏል፣

👉 የአንድ ቀን ጫጩት 61 ነጥብ 5 ሚሊዮን፤ የዓሣ ጫጩት 3 ነጥብ 91 ሚሊዮን ተሰራጭቷል፣

👉 የአንድ ቀን ጫጩት አቅርቦት ለመጨመር የቅድመ ወላጅ ዶሮ ማባዥ ማዕከል ተቋቁሟል፣

👉 ከሁሉም የእንስሳት መኖ ምንጮች 135 ሚሊዮን ቶን ለማምረት ታቅዶ 129 ሚሊዮን ቶን ማከናወን ተችሏል፣

👉 167 ሚሊዮን እንስሳት ለመከተብ ታቅዶ 180 ሚሊዮን እንስሳት መከተብ ተችሏል፣

በአጠቃላይ ከቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ከአበባ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም ከእንስሳትና እንስሳት ተዋፅዖ 1.23 ቢሊዮን ዶላር ተገኝቷል። በሌሎች ተቋማት ክትትል የሚደረግባቸውን ወጭ የግብርና ምርቶችን ጨምሮ አንድ ነጥብ 61 ቢሊዮን ዶላር ተገኝቷል ብለዋል::

መንግስት የወሰደው የኢኮኖሚ ማሻሻያ እርምጃ ለወጭ የግብርና ምርቶች አፈፃፀም ዕድገት አስተዋዖ አድርጓል።

#በሌማት_ትሩፋት #የዓሣ_ሀብት #ቡና
👍12
በኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፉ ተቀማጭ ገንዘብ ሁለት ነጥብ 74 ትሪሊዮን ብር ደርሷል
*****
(ኢ ፕ ድ)

በኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ ተቀማጭ ገንዘብ ሁለት ነጥብ 74 ትሪሊዮን ብር መድረሱን የብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምህረቱ ገለጹ።

የብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምህረቱ ለኢፕድ እንደገለጹት፤ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፉ ተቀማጭ ገንዘብ ሁለት ነጥብ 74 ትሪሊዮን ብር ደርሷል። የሀገሪቱ ባንኮች ከዓመት ዓመት በተቀማጭ ገንዘብ፣ አጠቃላይ ባላቸው የፋይናንስ እሴት ለውጥ እያመጡ መሆኑን ገልጸዋል።

በቅርቡ የውጭ ባንኮች ሀገር ቤት ገብተው እንዲሠሩ የጸደቀው አዋጅ በዋናነት የውጭ ባለሀብቶች በባንክ መስክ ተሰማርተው ለኢኮኖሚው አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ነው ያሉት አቶ ማሞ፤ የዘርፉን ተወዳዳሪነት በማሻሻል ባንኮች በኢኮኖሚው ውስጥ የሚጫወቱትን ሚና ከፍ ለማድረግ እንደሆነ ገልጸዋል።

የባንክ ዘርፉ ለውጭ ኢንቨስትመንት ክፍት ማድረግ ማለት የኢትዮጵያ ባንኮች ችግር ላይ ይወድቃሉ ማለት አይደለም። የሀገር ውስጥ ባንኮች አዳዲስ አሠራርና አገልግሎት ተምረው ለኢኮኖሚ የሚያደርጉትን አስተዋጽኦ ይጨምራል።

#ባንኮች #የውጭ_ባንኮች #ፋይናንስ #የውጭ_ባለሀብቶች

https://press.et/?p=144629
👍81
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍101
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በኢትዮጵያ በሁሉም የአየር ጠባይ የሚያገለግሉ መንገዶች ከ126 ሺህ ወደ 170 ሺህ ኪሎ ሜትር አድጓል
*****
(ኢ ፕ ድ)

በኢትዮጵያ በሁሉም የአየር ጠባይ የሚያገለግሉ መንገዶች በስድስት አመታት ብቻ ከ126 ሺህ ኪሎ ሜትር ወደ 170 ሺህ ኪሎ ሜትር እንዳደገ ያውቃሉ?

በፌዴራል መንግሥት የተሰሩ የአስፋልት መንገዶች ብቻ 26 ሺህ 722 ኪሎ ሜትር ያህል ሲሆኑ በአሁኑ ወቅት በተለያየ የአፈፃፀም ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

ከነዚህም መካከል የ63 ኪሎ ሜትር የጅማ-አጋሮ-በሻሻ የመንገድ ፕሮጀክት የሚገኝበት ሲሆን ወደ ታሪካዊው የጅማ አባጅፋር ቤተ መንግሥት የሚያዳርስ ዐበይት ከተሞችን የሚያገናኙ ሰፋፊ መንገዶች የተካተቱበት መንገድ ይገኛል።

በጅማ እና አጋሮ ብቻ ከ20 ኪሎ ሜትር በላይ የከተማ መንገዶች የተለዩ የብስክሌት መጋለቢያዎች አካተዋል።

#መንገድ #ኢትዮጵያ
👍71
በኢትዮጵያ ላይ ጫና እንዲደረግ ከግብጽ ጉቦ የተቀበሉት ሴናተር በ11 ዓመት እስራት ተቀጡ
*****
(ኢ ፕ ድ)

በኢትዮጵያ ላይ ጫና እንዲደረግ የግብፅን ጥቅም ለማስጠበቅ ጉቦ የተቀበሉት የቀድሞው የኒው ጀርዚ ሴናተር ቦብ ሜኔንዴዝ የ11 ዓመት እስራት ተፈርዶባቸዋል።

ሌላ ሀገርን በመርዳት 16 ክሶች የቀረቡባቸው ሜንዴዝ፣ ቢያንስ 15 ዓመታት ሊያስፈርድባቸው እንደሚገባ ተገልጿል።

በተለይ ከግብፅ መንግሥት የተቀበሏቸው ጥፍጥፍ ወርቆች፣ ጥሬ ገንዘብና መርሴዲስ ቤንዝ መኪና ለወንጀላቸው ማረጋገጫ ተደርገው ለፍርድ ቤት በማሰረጃነት መቅረባቸውን የሮይተርስ ዘገባ ያመላክታል።

ሜንዴዝ በጠበቃቸው በኩል ቀለል ያለ የማኅበራዊ አገልግሎት ቅጣት ቢጠይቁም ፍርድ ቤቱ ጥያቄያውን አልተቀበለውም።

በፈረንጆቹ 2020 ላይ የወቅቱ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የሶስትዮሽ ድርድር ላይ በንቃት እንዲሳተፉ ጫና አድርገው እንደነበር አይዘነጋም።

የኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን መሪዎች በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ የሶስትዮሽ ውይይት በማድረግ ላይ የነበሩ ሲሆን የወቅቱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ይህ ውይይት ወደ ዋሸንግተን እንዲመጣ ማድረጋቸው አይዘነጋም፡፡

ሜኔንዴዝ ዲሞክራት ፓርቲን ወክለው የአሜሪካ ህግ አውጪ ምክር ቤትን ከመቀላቀላቸው በፊት የኒው ጀርሲዋ ዩኒየን ሲቲን በከንቲባነት መርተዋል፡፡

ጥር 22 ቀን 2017 ዓም

#የዓባይ_ግድብ #የሁለትዮሽ_ድርድር #ኢትዮጵያ #ግብፅ
👍143