Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የአፍሪካ ኢነርጂ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ዳሬ ሰላም ገቡ
****
(ኢ ፕ ድ)

የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች የሚሳተፉበት የኢነርጂ ጉባዔ በነገው ዕለት በታንዛኒያ ይካሄዳል።

ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በጉባኤው ላይ ለመሳተፍ ታንዛኒያ ዳሬ ሰላም ገብተዋል። ዳሬ ሰላም ጁሊየስ ኒዬሬሬ አየር ማረፊያ ሲደርሱ በሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ጉባዔው እስከ ፈረንጆቹ 2030 ድረስ ለ300 ሚሊዮን አፍሪካውያን የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽ በሚደረግበት መንገድ ላይ እንደሚመክር ኢቢሲ ዘግቧል።

ለ600 ሚሊዮን አፍሪካውያን የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽ አለመሆኑን መረጃዎች ያመላክታሉ።

ጥር 19 ቀን 2017 ዓም
👍16👏1
ህይወት ፋና ሪፈራል ሆስፒታል ከ300 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የካንሰር ህክምና እየሰጠ እንደሚገኝ ተገለጸ
******
(ኢ ፕ ድ)

ህይወት ፋና ሪፈራል ሆስፒታል ከ300 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የካንሰር ህክምና እየሰጠ እንደሚገኝ የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና የማህበረሰብ ተሳትፎ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ይስሐቅ የሱፍ ገለፁ።

የካንሰር ህክምና ማዕከሉ ለምስራቁ የሀገሪቷ ክፍል አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና የማህበረሰብ ተሳትፎ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ይስሐቅ የሱፍ ለኢፕድ እንደገለፁት ከ300 እስከ 400 ለሚሆኑ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ታማሚዎች አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡

ሶማሊያ እና ጅቡቲ ሀገራት የካንሰር ታማሚዎች በሆስፒታሉ የህክምና አገልግሎት እያገኙ መሆኑን አብራርተዋል።

በሆስፒታሉ የኬሞ ቴራፒና የጨረር ህክምና አገልግሎት ለካንሰር ታካሚዎች እየተሰጠ ነው ያሉት ዶክተር ይስሐቅ፤ የህክምና አገልግሎት አሰጣጡ እንዲሻሻል ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

ከጤና ዘርፍ ባለፈ የማህበረሰብ አቀፍ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

በአማን ረሺድ

ጥር 20 ቀን 2017 ዓም
👍12
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ ዶ/ር ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡት የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ካነሷቸው ዋና ዋና ሀሳቦች‼️

👉 ከቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም 913 ሚሊዮን ዶላር፤ ከአበባ አትክልትና ፍራፍሬ 263 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል፣

👉 ከእንስሳትና እንስሳት ተዋፅዖ 54 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል፣

👉 አንድ ነጥብ 92 ሚሊዮን ላሞችን ማዳቀል ተችሏል፣

👉 የወተት ምርት 7 ቢሊዮን ሊትር ወተት ማምረት ተችሏል፣

👉 የእንቁላል ምርትን 4 ቢሊዮን ለማምረት ታቅዶ 4 ነጥብ 5 ቢሊዮን ተገኝቷል፣

👉 116 ሺህ ቶን የዶሮ ሥጋ ለማምረት ታቅዶ 105 ሺህ ቶን ማምረት ተችሏል፣

👉 102 ሺህ ቶን የዓሣ ምርት ለማምረት ታቅዶ 91 ሺህ ቶን የዓሣ ምርት ማምረት ተችሏል፣

👉 የአንድ ቀን ጫጩት 61 ነጥብ 5 ሚሊዮን፤ የዓሣ ጫጩት 3 ነጥብ 91 ሚሊዮን ተሰራጭቷል፣

👉 የአንድ ቀን ጫጩት አቅርቦት ለመጨመር የቅድመ ወላጅ ዶሮ ማባዥ ማዕከል ተቋቁሟል፣

👉 ከሁሉም የእንስሳት መኖ ምንጮች 135 ሚሊዮን ቶን ለማምረት ታቅዶ 129 ሚሊዮን ቶን ማከናወን ተችሏል፣

👉 167 ሚሊዮን እንስሳት ለመከተብ ታቅዶ 180 ሚሊዮን እንስሳት መከተብ ተችሏል፣

በአጠቃላይ ከቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ከአበባ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም ከእንስሳትና እንስሳት ተዋፅዖ 1.23 ቢሊዮን ዶላር ተገኝቷል። በሌሎች ተቋማት ክትትል የሚደረግባቸውን ወጭ የግብርና ምርቶችን ጨምሮ አንድ ነጥብ 61 ቢሊዮን ዶላር ተገኝቷል ብለዋል::

መንግስት የወሰደው የኢኮኖሚ ማሻሻያ እርምጃ ለወጭ የግብርና ምርቶች አፈፃፀም ዕድገት አስተዋዖ አድርጓል።

#በሌማት_ትሩፋት #የዓሣ_ሀብት #ቡና
👍12
በኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፉ ተቀማጭ ገንዘብ ሁለት ነጥብ 74 ትሪሊዮን ብር ደርሷል
*****
(ኢ ፕ ድ)

በኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ ተቀማጭ ገንዘብ ሁለት ነጥብ 74 ትሪሊዮን ብር መድረሱን የብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምህረቱ ገለጹ።

የብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምህረቱ ለኢፕድ እንደገለጹት፤ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፉ ተቀማጭ ገንዘብ ሁለት ነጥብ 74 ትሪሊዮን ብር ደርሷል። የሀገሪቱ ባንኮች ከዓመት ዓመት በተቀማጭ ገንዘብ፣ አጠቃላይ ባላቸው የፋይናንስ እሴት ለውጥ እያመጡ መሆኑን ገልጸዋል።

በቅርቡ የውጭ ባንኮች ሀገር ቤት ገብተው እንዲሠሩ የጸደቀው አዋጅ በዋናነት የውጭ ባለሀብቶች በባንክ መስክ ተሰማርተው ለኢኮኖሚው አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ነው ያሉት አቶ ማሞ፤ የዘርፉን ተወዳዳሪነት በማሻሻል ባንኮች በኢኮኖሚው ውስጥ የሚጫወቱትን ሚና ከፍ ለማድረግ እንደሆነ ገልጸዋል።

የባንክ ዘርፉ ለውጭ ኢንቨስትመንት ክፍት ማድረግ ማለት የኢትዮጵያ ባንኮች ችግር ላይ ይወድቃሉ ማለት አይደለም። የሀገር ውስጥ ባንኮች አዳዲስ አሠራርና አገልግሎት ተምረው ለኢኮኖሚ የሚያደርጉትን አስተዋጽኦ ይጨምራል።

#ባንኮች #የውጭ_ባንኮች #ፋይናንስ #የውጭ_ባለሀብቶች

https://press.et/?p=144629
👍81
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍101
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በኢትዮጵያ በሁሉም የአየር ጠባይ የሚያገለግሉ መንገዶች ከ126 ሺህ ወደ 170 ሺህ ኪሎ ሜትር አድጓል
*****
(ኢ ፕ ድ)

በኢትዮጵያ በሁሉም የአየር ጠባይ የሚያገለግሉ መንገዶች በስድስት አመታት ብቻ ከ126 ሺህ ኪሎ ሜትር ወደ 170 ሺህ ኪሎ ሜትር እንዳደገ ያውቃሉ?

በፌዴራል መንግሥት የተሰሩ የአስፋልት መንገዶች ብቻ 26 ሺህ 722 ኪሎ ሜትር ያህል ሲሆኑ በአሁኑ ወቅት በተለያየ የአፈፃፀም ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

ከነዚህም መካከል የ63 ኪሎ ሜትር የጅማ-አጋሮ-በሻሻ የመንገድ ፕሮጀክት የሚገኝበት ሲሆን ወደ ታሪካዊው የጅማ አባጅፋር ቤተ መንግሥት የሚያዳርስ ዐበይት ከተሞችን የሚያገናኙ ሰፋፊ መንገዶች የተካተቱበት መንገድ ይገኛል።

በጅማ እና አጋሮ ብቻ ከ20 ኪሎ ሜትር በላይ የከተማ መንገዶች የተለዩ የብስክሌት መጋለቢያዎች አካተዋል።

#መንገድ #ኢትዮጵያ
👍71
በኢትዮጵያ ላይ ጫና እንዲደረግ ከግብጽ ጉቦ የተቀበሉት ሴናተር በ11 ዓመት እስራት ተቀጡ
*****
(ኢ ፕ ድ)

በኢትዮጵያ ላይ ጫና እንዲደረግ የግብፅን ጥቅም ለማስጠበቅ ጉቦ የተቀበሉት የቀድሞው የኒው ጀርዚ ሴናተር ቦብ ሜኔንዴዝ የ11 ዓመት እስራት ተፈርዶባቸዋል።

ሌላ ሀገርን በመርዳት 16 ክሶች የቀረቡባቸው ሜንዴዝ፣ ቢያንስ 15 ዓመታት ሊያስፈርድባቸው እንደሚገባ ተገልጿል።

በተለይ ከግብፅ መንግሥት የተቀበሏቸው ጥፍጥፍ ወርቆች፣ ጥሬ ገንዘብና መርሴዲስ ቤንዝ መኪና ለወንጀላቸው ማረጋገጫ ተደርገው ለፍርድ ቤት በማሰረጃነት መቅረባቸውን የሮይተርስ ዘገባ ያመላክታል።

ሜንዴዝ በጠበቃቸው በኩል ቀለል ያለ የማኅበራዊ አገልግሎት ቅጣት ቢጠይቁም ፍርድ ቤቱ ጥያቄያውን አልተቀበለውም።

በፈረንጆቹ 2020 ላይ የወቅቱ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የሶስትዮሽ ድርድር ላይ በንቃት እንዲሳተፉ ጫና አድርገው እንደነበር አይዘነጋም።

የኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን መሪዎች በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ የሶስትዮሽ ውይይት በማድረግ ላይ የነበሩ ሲሆን የወቅቱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ይህ ውይይት ወደ ዋሸንግተን እንዲመጣ ማድረጋቸው አይዘነጋም፡፡

ሜኔንዴዝ ዲሞክራት ፓርቲን ወክለው የአሜሪካ ህግ አውጪ ምክር ቤትን ከመቀላቀላቸው በፊት የኒው ጀርሲዋ ዩኒየን ሲቲን በከንቲባነት መርተዋል፡፡

ጥር 22 ቀን 2017 ዓም

#የዓባይ_ግድብ #የሁለትዮሽ_ድርድር #ኢትዮጵያ #ግብፅ
👍143
የአየር ወለድ ትምህርት ቤት የልዩ ሀይል ፀረ-ሽብር አባላትን በአየር ወለድነት አሰልጥኖ አስመረቀ
*****
(ኢ ፕ ድ)

በኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ የአየር ወለድ ትምህርት ቤት የልዩ ሀይል ፀረ-ሽብር ሠልጣኞችን በአየር ወለድነት አሰልጥኖ አስመርቋል።

የኮማዶና አየር ወለድ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ ለተመራቂ የልዩ ሀይል ፀረ-ሽብር አባላት የአየር ወለድ ልዩ ምልክት የሆነውን የደረት ክንፍ አልብሰዋል።

የአየር ወለድ ስልጠና የወሰዱት የክፍሉ አባላት ቀደም ብለው እጅግ ፈታኝና ውስብስብ የሆነ የልዩ ሀይል ፀረ- ሽብር ስልጠናን መውሰዳቸውን አስታውሰው የክፍሉ አባላት የአየር ወለድ ስልጠናን በተጨማሪነት መሰልጠን አስፈላጊና ወሳኝ በመሆኑ ስልጠና መሰጠቱን ተናግረዋል፡፡

የልዩ ሀይል ፀረ-ሽብር አባላት በግልም ሆነ በቡድን የሚሰጣቸውን ውስብስብና ልዩ ግዳጅ ለመወጣ የሚያስችላቸው አቅም እንዲኖራቸው ተደርገው በላቀ ደረጃ መሰልጠናቸውን የገለፁት ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ ተመራቂዎችም የሀገሪቷ ፈጣን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የዜጎቿን ህይወት የመቀየር ልማታዊ ጉዞ እንዳይደናቀፍ የተዘጋጁበትን ልዩ ግዳጅ በፍፁም ዲሲፕሊንና ፅናት ለመወጣት ዝግጁ መሆን እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

አዛዡ ዕዙና ተቋሙ የትምህርት ቤቱን አቅም ለመገንባት በርካታ ስራዎችን መስራታቸውን በማስታወስ የአየር ወለድ ትምህርት ቤት በዚሁ ደረጃ የሚጠበቅበትን ተልዕኮ በብቃት እየተወጣ የሚገኝ በመሆኑ ለተገኘው ውጤት ያለእረፍት ለተጉት አሰልጣኞች ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የኮማንዶና አየር ወለድ ማሰልጠኛ ማዕከል አዛዥ ኮሎኔል ቦጃ አጋ በበኩላቸው የአየር ወለድ ትምህርት ቤት በማዕከሉ ስር ከሚገኙ አራት ትምህርት ቤቶች መካከል አንዱ መሆኑን በመግለፅ ትምህርት ቤቱም ራሱን በማብቃት ተቋሙ በሀገር ላይ በየትኛውም ወቅት እና ቦታ የሚቃጣን ጥቃት ለመመከት ለልዩ ግዳጅ የሚፈልገውን የሰው ሀይል በላቀ ቴክኖሎጂ እያሰለጠነ እና እያበቃ የሚገኝ ሥለመሆኑ አስገንዝበዋል፡፡

የስልጠናውን ሪፖርት ያቀረቡት የአየር ወለድ ትምህርት ቤት አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል ፀጋዬ ካሱ ትምህርት ቤቱ ተመራቂ የልዩ ሀይል ፀረ-ሽብር አባላትን በልዩ ሁኔታ በጥራት በማሰልጠን የሚፈለገውን አቅም እንዲገነቡ ማደረጉን ገልፀው ለስልጠናው ስኬት የአሰልጣኙ ሀገራዊ ፍቅርና አንድነት የጎላ አስተዋፅኦ ነበረው ማለታቸውን ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መረጃ ያመለክታል።

ጥር 22 ቀን 2017 ዓም
👍52👏1
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍7