Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.76K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ 56 ከተሞች የኮሪደር ልማት ስራ እየተከናወነ ይገኛል
*******
(ኢ ፕ ድ)

በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ 56 ከተሞች የኮሪደር ልማት እየተሰራ መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ገለጹ።

በአዲስ አበባ የተሰሩት የልማት ስራዎች የሀሳብ፣ የአመራር፣ የህብረተሰብ ንቁ ተሳትፎ ድምር ውጤት ናቸው ብለዋል

የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ ብልጽግና ፓርቲ በአንደኛ ጠቅላለ ጉባኤው ለመተግበር ያስቀመጣቸው አቅጣጫዎች ወደተግባር መቀየራቸውን በአዲስ አበባ ከተማ ተመልክተናል ብለዋል።

በአዲስ አበባ ተጀምሮ ተጨባጭ ውጤት ካስገኘው የኮሪደር ልማት ስራ ተሞክሮ በመውሰድ ወደሌሎች ከተሞች በማስፋት እየተሰራ ነው ያሉት ሚኒስትሩ የከተሞቹን ገጽታ በመቀየርና ህብረተሰቡን ተጠቃሚ በማድረግ ረገድ ጉልህ ሚና አበርክቷል።

ኢትዮጵያ ትልቅ ህዝብና በርካታ ጸጋዎች ያሏት ሀገር መሆኗን ገልጸው፤ ለሀገሪቱ የሚያስፈልጋት አዳዲስ ቴክኖሎጂ ብቻ ሳይሆን ያላትን ሀብት አቧራውን በማራገፍ መግለጥ ጭምር ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ከሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተውጣጡ የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ ጠቅላላ ጉባኤ ተሳታፊዎች በአዲስ አበባ ከተማ የተሰሩ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።

በሄለን ወንድምነው

ጥር 22 ቀን 2017 ዓም
👍6
ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተሰጠ መግለጫ‼️

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ በደረሰው የአውሮፕላን አደጋ የተሰማውን ሀዘን ገለፀ።

ለአሜሪካ መንግሥትና ሕዝብ ያለውን አጋርነት በመግለፅ በአደጋው ለተጎዱ ቤተሰቦችም መጽናናትን ተመኝቷል።

በአሜሪካ 64 ሰዎችን ይዞ ሲበር የነበረ የመንገደኞች አውሮፕላን በሮናልድ ሬገን አየር ማረፊያ ለማረፍ ሲቃረብ አራት የበረራ አባላትን ከያዘ የጦር ሄሊኮብተር ጋር ተጋጭቶ መከስከሱ መረጃዎች ያመላክታሉ።

ጥር 22 ቀን 2017 ዓም
😁13😢5👍2
የብልጽግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባዔ ዛሬ ጥር 23 ቀን 2017 ዓም መካሄድ ይጀምራል
*******
(ኢ ፕ ድ)

የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ ጉባዔ ከዛሬ ጥር 23 ቀን ጀምሮ እስከ 25 ቀን 2017 ዓም ድረስ 'ከቃል እስከ ባህል' በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

በጉባኤው ለመሳተፍ፤

👉 የሩሲያው ዩናይትድ ራሺያ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር ዲ.ኤ ሜዴቭዴቭ፣

👉 የደቡብ አፍሪካው አፍሪካ ናሽናል ኮንግረንስ ፓርቲ የብሔራዊ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ኖጦሉ ኪይቬት፣

👉 የካዛኪስታን አማናት ፓርቲ እና የሀገሪቱ ፓርላማ የታችኛው ምክር ቤት አባል ሳማት ኑር ታተዛ፣

👉 የኩባው ኮሚኒስት ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሜቴ አባል ዩዲ ሜርሴዲስ ኸርናንዴዝ

👉 የቱርኬሚስታን ዲሞክራቲክ ፓርቲ መሪ አታ ሰርዳሮቭ እና በሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመካከለኛዉ ምስራቅና አፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ያዝጉሊ ማምዶቭ በጉባኤ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።

እንግዶቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በጉባዔው ላይ የጎረቤት ሀገራት እና የብሪክስ አባል ሀገራት እህት ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮች ይታደማሉ ተብሏል።

የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ ጉባዔ ከጥር 23 እስከ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

በማርቆስ በላይ

ጥር 23 ቀን 2017 ዓም
5👍5👏1
ከባህርና ደረቅ ትራንስፖርት አገልግሎት ከ46 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተገኝቷል
*****
(ኢ ፕ ድ)

የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ባለፋት ስድስት ወራት ከባህርና ደረቅ ትራንስፖርት አገልግሎት 46 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ። 9 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብርም ያልተጣራ ትርፍ ማግኘቱን ገልጻል።

የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክ ዋና ስራ አስፈፃሚ በሪሶ አመሎ (ዶ/ር)፣ በሰጡት ማብራሪያ፤ በባለፉት ስድስት ወራት ከባህርና ደረቅ ትራንስፖርት አገልግሎት 44 ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ 46 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ገቢ ተገኝቷል።

በግማሽ አመቱ 6 ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ብር ትርፍ ለማግኘት ታቅዶ 9 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ያልተጣራ ትርፍ ተገኝቷል።

ድርጅቱ በባህርና በደረቅ የትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፤ አገልግሎቱን በዲጅታል የማዘመን ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል። ደርጅቱ አለም አቀፍ ተወዳዳሪ ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ሰራዎች እየተሰሩ ነው ሲሉ ጠቁመዋል።

በታደሠ ብናልፈው

ጥር 23 ቀን 2017 ዓም
4
"የአገው ፈረሰኞች #የኢትዮጵያን ዳር ድንበርና ሉዓላዊነት በማስጠበቅ ታላቅ ሚና ነበራቸው። ለዚህም #የዓድዋ ዘመቻ ተሳትፏቸው ጉልሕ ምስክር ነው። ዛሬም የአባቶቻቸውን ፈለግ በመከተል ሰላምንና ጸጥታን በማስከበር ተገቢውን ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ። ዛሬ የሚከበረው በዓል፣ ፈረሰኞቻችንና ፈረሶቻችን የሰላምና የልማት ዘብ መሆናቸውን ለትውልድ የሚመሰክሩበት እንደሚሆን አምናለሁ"

- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

ጥር 23 ቀን 2017 ዓም
👏1
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍31🥰1
ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተሰጠ የሀዘን መግለጫ‼️

✍️ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በደቡብ ሱዳን ዩኒቲ ግዛት በደረሰው የአውሮፕላን መከስከስ አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ዜጎች የተሰማውን ሀዘን ገልጿል። በአደጋው የሚወዷቸውን በሞት ላጡ ቤተሰቦች መጽናናትን ተመኝቷል። ዩኒቲ ግዛት በደረሰው የአውሮፕላን መከስከስ አደጋ የ20 መንገደኞች ሕይወት አልፏል።

✍️ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በህንድ ኩምብ ሜላ ፌስቲቫል ላይ በሰዎች መብዛት ምክንያት በተፈጠረ ግርግር ሕይወታቸውን ላጡ ዜጎች የተሰማውን ሀዘን ገልጿል። በተፈጠረ ግርግርም 15 ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል።

በመግለጫው የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ከህንድ ህዝብና መንግስት ጎን መሆኑን ገልጾ፤ ለህንድ ህዝብና መንግስት መጽናናትን ተመኝቷል። በህንድ ፕራያጋራጅ በኩምብ ሜላ ፌስቲቫል በተፈጠረ ግርግርም 15 ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል።

ጥር 23 ቀን 2017 ዓም
👍51
በጌዴኦ ዞን ለዓባይ ግድብ ግንባታ 16 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ
******
(ኢ ፕ ድ)
በጌዴኦ ዞን ባለፈው አንድ ወር ውስጥ በንቅናቄ በተሰራ ሥራ ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ 16 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን የዞኑ የሕዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ገለጸ።

በዞኑ ህብረተሰቡ በቦንድ ግዥ በነቂስ በመሳተፍ ዳግም አሻራውን እያኖረ መሆኑም ተመላክቷል።

የጽህፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ ብርሃኑ ሮቤ ለኢዜአ እንደገለጹት፥የሕዳሴው ግድብ ዋንጫ ወደዞኑ መምጣትን ተከትሎ ባለፈው አንድ ወር ውስጥ የገቢ ማሰባሰብ ሥራ ተከናውኗል።

የ16 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር ቦንድ ግዥ የተፈጸመ ሲሆን ተጨማሪ ከ11 ሚሊዮን ብር በላይ ቃል ተገብቷል።

በድጋፉ የመንግስት ሠራተኞች፣ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ ተቋማትና ማህበራት መሳተፋቸውን አመልክተዋል።

የዞኑ ህዝብ በቦንድ ግዥ በነቂስ በመሳተፍ ዳግም አሻራውን ማኖሩንም አቶ ብርሃኑ ተናግረዋል።

የሕዳሴው ግድብ ዋንጫ በዞኑ የነበረውን የአንድ ወር ቆይታ አጠናቆ ለወላይታ ዞን መሰጠቱን ያነሱት አቶ ብርሃኑ፣ በበጀት ዓመቱ ቀጣይ ወራት ለግድቡ የሚሰበሰበውን ገቢ 60 ሚሊዮን ብር ለማድረስ ታቅዷል ብለዋል።

#ዓባይ #የዓባይ_ግድብ #ኢትዮጵያ #ግብፅ

ጥር 23 ቀን 2017 ዓም
👍4👏1