Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በባሕር ኃይል በትብብር መሥራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ መከሩ
*******
(ኢ ፕ ድ)
የሩሲያ ባሕር ኃይል ምክትል አዛዥ አድሚራል ቪላዲሚር ቮሮቢቭ የተመራ ልዑክ የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል የሚገነባቸውን የባሕር ኃይል ተቋማት ጠቅላይ መምሪያውና ቢሾፍቱ የሚገኘውን ማሰልጠኛ ማዕከል ጎብኝቷል፡፡

በጉብኝቱ በጋራ ባሕር ኃይልን በሚያጠናክሩና በቀጣይ ትብብሮች ለማመቻቸት ስምምነት ተፈርሟል፡፡ በቀጣይ የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ጋር በሚኖሩ ትብብሮች ዙሪያ ምክክር አድርገዋል።

የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ኮሞዶር ጀማል ቱፊሳ፤ ትብብሩ በስልጠናና ዐቅም ግንባታ ያተኮረ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ በቀጣይም አብሮ በመሥራት ተቋማችን የጀመረውን የባሕር ኃይል ግንባታ ለማጠናከርና በዓለም አቀፍ ውኃ ላይ የሀገራችንን ጥቅም ለማስከበር ዝግጁነታችንን የበለጠ ለማጠናከር መክረናል ማለታቸውን የመከላከያ ሠራዊት ማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ መረጃ አመላክቷል፡፡

መጋቢት 5 ቀን 2017 ዓም
👍17👏63😁3
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍11👏1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በየአመቱ የሚያከናውኑትን የኢፍጣር መርሐግብር በዝቅተኛ የኑሮ ሁኔታ ላይ ለሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች በብሔራዊ ቤተመንግሥት አከናውነዋል።

#PMOEthiopia
👍10👏21
በትግራይ ክልል ህዝብን ችግር ውስጥ የሚከቱ ድርጊቶች መቆም ይኖርባቸዋል - የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ
*****
(ኢ ፕ ድ)

በትግራይ ክልል የሕወሃት አንደኛው አንጃ ለራሱ ጥቅም ሲል እየፈጠራቸው ያሉ ድርጊቶች ተገቢነት የሌላቸውና ህዝብን ችግር ውስጥ የሚከቱ በመሆናቸው መቆም እንዳለባቸው የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አሳስቧል።

"የፓርቲው ሊቀ መንበር አረጋዊ በርሔ (ዶ/ር) በሰጡት መግለጫ፣ በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት ሁሉንም አካታች የሆነ አስተዳደር በክልሉ መተግበር አንዳለበት ጠቅሰው፣ የትግራይ ህዝብ ከመጠን በላይ በጦርነት ተጎድቷል ብለዋል።

ከፕሪቶሪያው ስምምነት ወዲህ በክልሉ የተቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር በህወሃት አንጃ እንዲጨናገፍ ተደርጓል።

በመሆኑም የፌደራል መንግስት በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት ሁሉንም ያካተተ አስተዳደር ተመስርቶ ህዝቡን ከዳግም መከራ ሊታደገው ይገባል ሲሉ ገልፀዋል።

ሔርሞን ፍቃዱ

መጋቢት 6 ቀን 2017 ዓም
👍8👏2🥰1
በመስቀል አደባባይ ለሚከናወነው የኢፍጣር ፕሮግራም የሚዘጉ መንገዶች ይፋ ሆኑ
*******
(ኢ ፕ ድ)
በዛሬው ዕለት በመስቀል አደባባይ ለሚከናወነው የኢፍጣር ፕሮግራም ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህም ዛሬ ከቀኑ 5 ሠዓት ጀምሮ በመስቀል አደባባይ በሚከናወነውን የኢፍጣር ፕሮግራም ምክንያት በማድረግ

👉 ከኦሎምፒያ ወደ መስቀል አደባባይ (ኦሎምፒያ አደባባይ ላይ)

👉 ከጥላሁን አደባባይ ወደ ሳንጆሴፍ መብራት (ጥላሁን አደባባይ ሲሆን ከባድ ተሽከርካሪ አጎና ላይ)

👉 ከለገሃር መብራት ወደ መሰቀል አደባባይ (ለገሃር መብራት)

👉 ከቴሌ ማቋረጫ ወደ ስታድየም (ቴሌ ማቋረጫ ላይ)

👉 ከሀራምቤ መብራት ወደ መስቀል አደባባይ (ሀራምቤ መብራት ላይ)

👉 ከብሔራዊ ቤተ መንግሥት ወደ መስቀል አደባባይ (ብሔራዊ ቤተመንግሥት ላይ)

👉 ከቅዱስ ዑራኤል አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ (ባምቢስ መቅረዝ ሆስፒታል መታጠፊያ ድረስ) የሚዘጋ መሆኑን በመገንዘብ አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ፖሊስ አሳስቧል፡፡

መጋቢት 7 ቀን 2017 ዓም
👍21