ብሬነሽ ደሴ ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች የ5 ኪ.ሜ ሩጫ ውድድርን አሸነፈች
****
(ኢ ፕ ድ)
የ2017 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች የ5 ኪሜ ሩጫ ውድድር ብሬነሽ ደሴ ከግሎባል ስፖርት በአንደኝነት አጠናቀቀች።
በግሏ የተወዳደረችው አብዙ ከበደ 2ኛ ደረጃን ይዛ የብር ሜዳልያ አሸናፊ ሆናለች። መቅደስ ሽመልስ ደግሞ 3ኛ በመሆን የነሀስ ሜዳሊያ ተሻላሚ ሆናለች። ለአሸናፊዎቹ ከ50 ሺህ ብር ጀምሮ ሽልማትም ተበርክቶላቸዋል።
ከ25 በላይ በተለያዩ የሙያ መስኮች የተሰማሩ ተምሳሌት ሴቶች፣ ሴት አምባሳደሮች፣ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሚሰሩ ሴት ኃላፊዎች የተሳተፉበት የ2017 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች የ5 ኪሜ ሩጫ ውድድር ተካሂዷል።
መጋቢት 7 ቀን 2017 ዓም

👍8
የአካባቢን ጸጋ ለይቶ፣ የተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃን መተግበር የሀገርን ብልጽግና የማረጋገጫ አንዱ መንገድ ነው። ይህን ርዕይ ወደ ተግባር እየቀየሩ ከሚገኙ አካባቢዎች የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ታች አርማጭሆ ወረዳ አንዱ ነው፡፡
በአካባቢው እየተከናወኑ የሚገኙ የሌማት ትሩፋት ሥራዎችና የአረንጓዴ አሻራ ስራዎች ይበል የሚያሰኙ ናቸው።
- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

👍4👏1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በብሔራዊ ቤተመንግሥት በተደረገው ሁለተኛው የኢፍጣር ምሽት ከተለያዩ ሀገራት የመጡ 200 የሚሆኑ ስደተኞች ተስተናግደዋል። ተሳታፊዎችም ብሔራዊ ቤተመንግሥት ጎብኝተዋል።
👏14❤8👍5
ኢትዮጵያ ከምትገዛቸው ከ800 በላይ የመድኃኒት አይነቶች ውስጥ የምታመርተው ከ100 በታች ነው
👉 በግዢ መዘርዝር ከተያዙ መድኃኒቶች ውስጥ 20 በመቶው አቅራቢ የላቸውም
****
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያ ከምትገዛው ከ800 በላይ የመድኃኒት አይነቶች ውስጥ የምታመርተው ከ100 በታች መሆኑን የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት አስታወቀ፡፡
አገልግሎቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ንጉሴ ለኢፕድ እንደገለጹት፣ የማህበረሰቡን የጤና ፍላጎት መሰረት ያደረጉ 800 መድኃኒቶች በመንግስት ጤና ተቋማት ቢመረጡም በኢትዮጵያ የሚመረተው ከመቶ በታች ነው፡፡
አገልግሎቱ መድኃኒቶችን ከሀገር ውስጥና ከውጪ አገራት ገዝቶ እንደሚያቀርብ ጠቅሰው፣ በግዢ መዘርዝር ከያዛቸው መድኃኒቶች 20 በመቶው አቅራቢ የሌላቸው፣ 30 በመቶው መድኃኒት አንድ አቅራቢ ብቻ እንዳላቸውና ቀሪዎቹ ቢሆኑ የተሻለ አቅራቢ እንደሌላቸው ተናግረዋል።
የሀገር ውስጥ የመድኃኒት ምርት መጠንን ማሳደግ ስትራቴጂካዊ መፍትሄ መሆኑን ጠቅሰው፣መድኃኒቶችን በሀገር ውስጥ ለማምረት ኢንቨስትመንትን መሳብ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡
አገልግሎቱ ከሚገዛው መድኃኒት በገንዘብ መጠን ሲታይ የዛሬ አራት አመት የአገር ውስጥ መድኃኒት ድርሻ ከ20 በመቶ በላይ እንደነበረ በመግለጽ፣ ባለፉት ሶስት ዓመታት ወደ 8 በመቶ እየቀነሰ የመጣ ሲሆን በተደረገው ማሻሻያ ወደ 36 በመቶ ከፍ ማለቱንና አሁን ደግሞ ወደ 41 እያደገ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡
የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ በዘርፉ ኢንቨስትመንት ላይ ትልቅ ለውጥ እያመጣ እንደሚገኝም ጠቁመዋል፡፡
በማርቆስ በላይ
መጋቢት 9 ቀን 2017 ዓም

👎5👍4🤔1
ሥራ ፈላጊ ነዎት❓
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
👎2❤1👍1