1446ኛው የዒድ አል-ፈጥር በዓል በድምቀት ተከብሮ ተጠናቀቀ
በአዲስ አበባ 1446ኛው የዒድ አል-ፈጥር በዓል በድምቀት ተከብሮ ተጠናቅቋል።
በበዓሉ ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ፣ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና የእምነቱ ተከታዮች በተገኙበት ተከብሯል።
መጋቢት 21 ቀን 2017 ዓም

👍1
"በዓላቶቻችን ትናንትን ያኖሩን፤ ዛሬን ያስተሳሰሩንና ነገ ላይ የሚያደርሱን ዕሴቶች ናቸው"
– ኑረዲን ቃሲም (ዶ/ር)
*******
(ኢ ፕ ድ)
ዒድ አልፈጥርንና መሰል በዓላቶቻችን ትናንትን ያኖሩን፤ ዛሬን ያስተሳሰሩንና ነገ ላይ የሚያደርሱን ዕሴቶች መሆናቸውን ዓለም አቀፍ የቁርዓን ዳኛ ኑረዲን ቃሲም (ዶ/ር) አስታወቁ።
ኑረዲን (ዶ/ር) ለኢፕድ እንደተናሩት፤ ዒድ አልፈጥር በሙስሊሙ ማኅበረሰብ ዘንድ ትልቅ የበረከትና የተቸገሩ ሳይቀሩ ተደስተው እንዲውሉ የሚደረግበት ልዩ ጊዜ ነው። በዚህም ሙስሊሙ ይህንን የእምነቱን አስተምሮ ተግባራዊ ሲያደርግ በዓሉን በተለያየ አግባብ እንዲመለከተውና ነገውን እንዲሠራ ያስችለዋል።
በመረዳዳት ውስጥ፤ በአብሮነት ውስጥ ያለውን ታላቅነት እንዲረዳው ያግዘዋል ብለዋል።
በዓላቶቻችን እምነታችንን በተግባር እንድንኖረው የሚያስችሉን ናቸውም የሚሉት ኑረዲን (ዶ/ር)፤ በዒድ ጊዜ የሚደረገው ሰዎችን የማገዝ ተግባር አንዱ እንደሆነ ጠቅሰዋል።
በዓሉ አንድም ሰው ወደ ልመና እንዳይወጣ በማገዝ አብሮነታችንን ማሳየት እንደሚገባ አመልክተው፤ ኢትዮጵያውያን ለበዓላት ልዩ ትርጉም የሚሰጡበት ዋነኛ ምክንያት በበዓላቶቻችን ውስጥ ትናንትን ማሰብ፤ ዛሬን መተሳሰርና ነገን አሻግሮ ማየት ስላለ መሆኑን ገልጸዋል።
በዓላቶቻችን ትናንትን በፍቅርና በደስታ አቆይተው ዛሬን አሳይተውናል። ዛሬን አስተሳስረው ደግሞ ነጋችን መልካም እንደሚሆን ይነግሩናል። ሁሌ ቅንና ለሰዎች የምንጨነቅም እንድንሆን መልካም ሥነምግባርን ያላብሱናል።

👏5👍3
ጎንደር ከተማ አባቶቻችን ያለልዩነት የሰሯት ከተማ ናት"- ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ቻላቸው ዳኘው
*****
(ኢ ፕ ድ)
1ሺህ 446ኛ የዒድ አልፈጥር በዓል በጎንደር ከተማ አጼ ፋሲለደስ ስቴዲየም በድምቀት ተከብሯል።
በመርሐ ግብሩ የተገኙት የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ቻላቸው ዳኘው እንደገለፁት፣በጎንደር ታሪክ የስልምና ታሪክ በአፄ ፋሲለደስ የንግስና ዘመን ትልቅ ቦታ ነበረው። በጎንደር ወርቃማ ዘመን ነጋድረስ የከተማዋን የንግድ ስርዓት በማሳደግ ድርሻው ከፍተኛ እንደነበር ጠቅሰዋል።
ዛሬም እኛ ፖለቲከኞች ሰላምን እንዘምራለን፤ የሀይማኖት አባቶች ለሀገራቱ ሰላም ሊያግዙን ይገባል ብለዋል።
ጎንደርን አባቶቻችን ያለ ልዩነት የሰሯት ከተማ ናት ያሉት ከንቲባው የሙስሊሙ ማህበረሰብ በከተማዋ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን በማገዝ እያደረጉት ላለው አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል።
#ዒድሙባረክ #ዒድአልፈጥር #ኢድ #ጎንደር

👍3👏1
❤4👍3👎1👏1