ጎንደር ከተማ አባቶቻችን ያለልዩነት የሰሯት ከተማ ናት"- ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ቻላቸው ዳኘው
*****
(ኢ ፕ ድ)
1ሺህ 446ኛ የዒድ አልፈጥር በዓል በጎንደር ከተማ አጼ ፋሲለደስ ስቴዲየም በድምቀት ተከብሯል።
በመርሐ ግብሩ የተገኙት የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ቻላቸው ዳኘው እንደገለፁት፣በጎንደር ታሪክ የስልምና ታሪክ በአፄ ፋሲለደስ የንግስና ዘመን ትልቅ ቦታ ነበረው። በጎንደር ወርቃማ ዘመን ነጋድረስ የከተማዋን የንግድ ስርዓት በማሳደግ ድርሻው ከፍተኛ እንደነበር ጠቅሰዋል።
ዛሬም እኛ ፖለቲከኞች ሰላምን እንዘምራለን፤ የሀይማኖት አባቶች ለሀገራቱ ሰላም ሊያግዙን ይገባል ብለዋል።
ጎንደርን አባቶቻችን ያለ ልዩነት የሰሯት ከተማ ናት ያሉት ከንቲባው የሙስሊሙ ማህበረሰብ በከተማዋ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን በማገዝ እያደረጉት ላለው አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል።
#ዒድሙባረክ #ዒድአልፈጥር #ኢድ #ጎንደር
መጋቢት 21 ቀን 2017 ዓም

👍3👏1
❤4👍3👎1👏1
“በረመዳን ወር የምንተገብራቸውን መልካም ዕሴቶች የሕይወታችን ልምዶች ልናደርጋቸው ይገባል”
-ኡስታዝ አቡበከር አሕመድ
*******
(ኢ ፕ ድ)
በረመዳን ወር የምንተገብራቸው የመተሳሰብ፣ የመረዳዳትና መሰል መልካም እሴቶችን ሁልጊዜም የሕይወታችን ልምዶች ማድረግ እንደሚገባ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኡስታዝ አቡበከር አሕመድ ገለጹ፡፡
ኡስታዝ አቡበከር አሕመድ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ ረመዳን መሠረታዊ እሴት በሰዎች ልብ ውስጥ የፈጣሪ ፍራቻ፣ መተዛዘን፣ ስለሌሎች መኖርን፣ መደጋገፍንና ማሰብን የሕይወታችን አካል እንድናደርግ ለ11 ወራት የሚሆን ስንቅ የሚይዝበት ወር ነው።
በመሆኑም በረመዳን ወር የምንተገብራቸውን የመተሳሰብ፣ የመረዳዳትና ለሌሎች መልካም እሴቶች ሁልጊዜም የሕይወታችን ልምዶች አካል ማድረግ ይጠበቅብናል ብለዋል።
ረመዳን አንዱ ስለሌላው የሚኖርበት ስለሆነ መልካም ተግባራት በስፋት የሚከናወኑበት ወር መሆኑን ጠቅሰው፤ ይህ ተግባር ደግሞ ሰዎች ዘወትር ሊኖራቸው የሚገባ ባሕሪ መሆን እንዳለበት ገልጸዋል።
እኛ ዋጋ ለማግኘት ብለን በፈቃዳችን ስንፆም ለችግር የተጋለጡ ወገኖቻችንን ማሰብና አለኝታነታችንን ማሳየት ይገባናል ብለዋል።

👍11❤4👎1👏1
👉 ኢትዮጵያ ታሪካዊ የቀይ ባሕር ተዋሳኝነቷን መልሳ ማግኘት አለባት፣
👉 ኢትዮጵያ ቀይ ባሕርን ልታጣ የቻለችበት ውጤት ራሱን የቻለ የኋላ ታሪክ አለው፣
👉 ቀይ ባሕርን እንድናጣ ያደረገው በወቅቱ የተመድ ውስጥ ይሠራ የነበረ አንድ ግብጻዊ ዲፕሎማት ነው፣
👉 የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ገዢ ፓርቲዎች ውሳኔዎችን አሳለፉ እንጂ በሁለቱም ወገን ያሉ ሕዝቦች አልተወያዩበትም፣
👉 በሰላማዊ መንገድ እነሱም እኛም ተጠቃሚ መሆን የምንችልበትን መንገድ መፍጠር አለብን፣
👉 የዓለም ሀገራት ኢትዮጵያ በአካባቢው መኖሯ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ያደርጋል የሚል አመኔታ አድሮባቸዋል፣
👉 ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ጋር ያላትን ግንኙነት በቱርክ አደራዳሪነት መልሳ ማስተካከል ችላለች
👉 ኢትዮጵያ የዓባይን ግድብ በማጠናቀቋ ታላቅ ድል ነው
👉 በራሷ አቅም ግዙፍ ፕሮጀክትን ማሳካት የምትችል ታላቅ ሀገር መሆኗን ለዓለም አሳይታለች፣
👉 ግድቡን ለመገንባት ያሳየነውን ሕብረትና አንድነት ከድህነት መውጣት እንደምንችል ያየንበት ፕሮጀክት ነው፣
👉 አሁን ካለንበት ወቅታዊ ሁኔታ አንጻር እንደ ሕዝብ ሰላም መረጋጋት አንድነትን ማምጣት ይጠበቅብናል፣
ዝርዝር መረጃውን ለማግኘት ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=148451

👍5❤4
የሹዋሊድ በዓል አብሮነትንና ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን በሚያጎለብት መልኩ ይከበራል
***
(ኢ ፕ ድ)
የሹዋሊድ በዓል ሰላምን፣ አብሮነትንና ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን በሚያጎለብት መልኩ እንደሚከበር የሀረሪ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች አሰታወቀ።
ከቀናት በኋላ የሚከበረው የዘንድሮው የሸዋል ኢድ በአል "የቅርስ ሀብቶቻችን ለቱሪዝም ልማታችን" በሚል መሪ ሀሳብ በድምቀት ይከበራል።
የሹዋሊድ በዓል በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ የባህል ድርጅት የማይዳሰስ አለም አቀፍ ቅርስ ሆኖ መመዝገቡ ይታወሳል።

👍2👏1
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
የሹዋሊድ በዓል አብሮነትንና ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን በሚያጎለብት መልኩ ይከበራል *** (ኢ ፕ ድ) የሹዋሊድ በዓል ሰላምን፣ አብሮነትንና ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን በሚያጎለብት መልኩ እንደሚከበር የሀረሪ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች አሰታወቀ። ከቀናት በኋላ የሚከበረው የዘንድሮው የሸዋል ኢድ በአል "የቅርስ ሀብቶቻችን ለቱሪዝም ልማታችን" በሚል መሪ ሀሳብ በድምቀት ይከበራል። የሹዋሊድ…
ከሀረሪ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት የተሰጠ መግለጫ‼️
የሹዋሊድ በዓል ሰላምን፣ አብሮነትን እና ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን በሚያጎለብት መልኩ ይከበራል
የሹዋሊድ ክብረ በዓል በሀረሪ ብሄረሰብ ዘንድ ለምዕተ አመታት ሲከበር የኖረና በትውልድ ቅብብሎሽ ባህሉንና ወጉን ጠብቆ ከነክብሩ ዛሬ ላይ የደረሰ ባህላዊ በዓል ነው።
የሀረሪ ህዝብ ልዩ መገለጫ እሴት የሆነው የሹዋሊድ በአል ከበዓልነቱ ባሻገር የሀረሪ ህዝብ ጥልቅ የሆነ ማህበራዊና ምጣኔ ሃብታዊ እሴቶች መገለጫም ነው።
የበዓሉ አከባበር የሀገራችን ሕዝቦች የአብሮነት ዕሴትን እያጎለበቱ ከሚገኙ ባህላዊ በዓላት መካከል አንዱ ሲሆን በተለይ በምስራቁ የሀገራችን ክፍል የባህል ትውውቅ በመፍጠር የህዝብ ለህዝብ ትስስር በማጠናከር በኩልም ገንቢ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።
የሹዋሊድ በዓል አከባበር ከህዳር 2016 ጀምሮ በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የማይዳሰስ አለም አቀፍ ቅርስ ሆኖ ተመዝግቧል። በመሆኑም በዓሉ የሀረሪ ህዝብ ብቻ ሳይሆን የመላ ኢትዮጵያውያን ከዚያም አልፎ የዓለም ህዝቦች ሁሉ ሃብት ሆኖ ይገኛል።
ሹዋሊድ የክልላችን ብሎም የሀገራችን የቱሪዝም ዘርፍ እንዲጎለብት ከማድረግ አንፃር የላቀ ጠቀሜታ ያለው በዓል ነው።
ዘንድሮ የሚከበረው የሸዋል ኢድ በአል "የቅርስ ሀብቶቻችን ለቱሪዝም ልማታችን" በሚል መሪ ሀሳብ በድምቀት ይከበራል።
የዘንድሮው የሹዋሊድ በዓል አከባበርም ሰላምን፣ አብሮነትን እና ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን በሚያጎለብት መልኩ ለማክበር አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል።
በበዓሉም የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች እና አጎራባች ክልሎች በሐረር ከተማ የባህል፣ ፌሲቲቫልና አውደ ርዕይ፣ የልማት ስራዎች ጉብኝትን ጨምሮ ሌሎች መርሃግብሮች የሚካሄድ ሲሆን በበዓሉ ላይም ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚመጡ እንግዶች ይታደሙበታል ተብሎ ይጠበቃል።
የሀረሪ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት
መጋቢት 22 ቀን 2017 ዓ. ም
ሐረር

👍5👏1
ሥራ ፈላጊ ነዎት❓
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍3
ቆቃ የውሃ ኃይል ማመንጫ ግድብ ለማመንጨት የታቀደውን ኃይል ማሳካት የሚያስችል ውኃ ይዟል
****
(ኢ ፕ ድ)
የቆቃ የውሃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ግድብ በ2017 በጀት ዓመት ለማመንጨት የያዘውን የኃይል ዕቅድ ማሳካት የሚያስችል የውሃ መጠን መያዙን የጣቢያው ሥራ አስኪያጅ ገልጸዋል፡፡
የጣቢያው ሥራ አስኪያጅ አቶ ሞርካ ኃይሌ እንደገለጹት ማመንጫ ጣቢያው በ2017 በጀት ዓመት 134 ነጥብ 9 ጊጋ ዋት ሰዓት ኃይል ለማምረት አቅዶ በ9 ወራት ውስጥ 119 ጊጋ ዋት ሰዓት ኃይል አመንጭቷል።
አሁን ላይ በግድቡ ያለው የውሃ መጠን ከባህር ጠለል በላይ 1586 ነጥብ 68 ሜትር ሲሆን ባለፈው በጀት ዓመት በተመሳሳይ ወቅት ከባህር ጠለል በላይ 1587 ነጥብ 01 ሜትር እንደነበር አስታውሰዋል።
በግድቡ ውስጥ የሚገኘው የውሃ መጠን ጣቢያው በቀሪ ወራት ያለምንም የውሃ እጥረት ኃይል እንዲያመነጭና ዓመታዊ ዕቅዱን እንዲያሳካ የሚያስችለው መሆኑንም አቶ ሞርካ ተናግረዋል።
ጣቢያው ከ65 ዓመታት በኋላም ሲገነባ ከተቀመጠለት 110 ጊጋ ዋት ሰዓት በላይ አማካይ ዓመታዊ የኃይል ምርት እያመረተ መሆኑን ገልፀው ለዚህም የኦፕሬሽንና የጥገና ክፍሉ ሚና ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመዋል።
ከ25 ዓመት በፊት በኤሌክትሮ ሜካኒካል ክፍሉ የመልሶ ግንባታ ሥራ መከናወኑንም አቶ ሞርካ ተናግረዋል።
የግድቡን ደህንነት ለመጠበቅና የእምቦጭ አረምን ለመከላከል ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ መልኩ በዕቅድ እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመው የቆቃ የውኃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ በሦስት ተርባይን 43 ነጥብ 2 ሜጋ ዋት የማምረት አቅም እንዳለው ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የተገኘው መረጃ ያመላክትል።
#ታዳሽ ኃይል #ግድብ
መጋቢት 22 ቀን 2017 ዓም

👍12👏1
በ‘አዲስ ምዕራፍ” ፕሮግራም ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ ተወሰደ
****
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በኢ ቢ ኤስ ቴሌቪዥን ጣቢያ ‘አዲስ ምዕራፍ’ በተሰኘ ፕሮግራም ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ።
ባለስልጣኑ ፕሮግራሙ እሑድ መጋቢት 14 ቀን 2017 ዓ.ም ያሰራጨውን ፕሮግራም ከመገናኛ ብዙኃን አዋጅ እና ከዘርፉ ሕጎች አንጻር መገምገሙን ገልጿል።
በዚሁ መሰረት በጣቢያው የቀረበው ፕሮግራም በሐሰተኛ መረጃ ላይ የተመሰረተ፣ ሕዝብን የሚያሳስትና ጥርጣሬን የሚፈጥር፣ የመገናኛ ብዘኃን አዋጅ 1238/2013፣ የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በወጣው አዋጅ 1185/2012 እንዲሁም የጋዜጠኝነት ሙያ ስነ-ምግባርን፣ መደበኛ የጋዜጠኝነት አሰራርን የሚጥስ የፓራጆርናሊዝም አሰራርን የተከተለ ሆኖ ተገኝቷል ብሏል፡፡
ጣቢያውም በፕሮግራሙ ዙሪያ ተጠይቆ ለባለሥልጣኑ በሰጠው ምላሽ ያሰራጨው ፕሮግራም ሐሰተኛ መሆኑንና ስህተት መፈጸሙን ማረጋገጡን ባለሥልጣኑ ባወጣው መረጃ አመላክቷል።
ባለሥልጣኑ ጉዳዩን መርምሮ በጣቢያው የሚሰራጨው “አዲስ ምዕራፍ” የተሰኘ ፕሮግራም በኤዲቶሪያል አሰራሩ ላይ አስፈላጊውን እርምት ወስዶ ለባለሥልጣኑ እስኪያሳውቅና ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ ፕሮግራሙ ከስርጭት ታግዶ እንዲቆይ መወሰኑን እና የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ የተሰጠ መሆኑን ገልጿል።
መጋቢት 23 ቀን 2017 ዓም

👍5❤1🥰1