Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.76K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
መጋቢት 24 አካታች የፖለቲካ ስርዓት የተፈጠረበት ታሪካዊ ቀን ነው - አቶ ኦርዲን በድሪ
****
(ኢ ፕ ድ)

መጋቢት 24 በሀገራችን የፖለቲካ ታሪክ አካታችና አቃፊ የፖለቲካ ስርዓት የተፈጠረበትና የሀሳብ ልዕልና የበላይነት መጎናፀፍ የቻለበት ታሪካዊ ቀን ነው ሲሉ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ገለጹ።

ርዕሰ መስተዳድሩ ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበትን 7ኛ ዓመት አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት፥ መጋቢት 24 በሀገራችን የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ፣ አዲስ የፖለቲካ ምዕራፍና ሀገራዊ ተስፋን ሰንቆ የመጣ ነው ብለዋል፡፡

ሀገራዊ ለውጡ ዜጎች ሀሳባቸውን በነፃነት ማራመድ እንዲችሉና የፍትህና የዳኝነት ሰርዓት ከማንኛውም ጣልቃ ገብነት ነፃ እንዲሆን ማስቻሉን ገልጸው፥ ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች እልባት ያገኙበትና ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል ችግሮች የተፈቱበት ነው ብለዋል።

በብሔራዊ ገዥ ትርክት ህብረ ብሔራዊ አንድነትን ለመገንባት ጥረት የተደረገበትና የፖለቲካ ቁርሾን በማስቀረት የበቀልና የመጠፋፋት ፖለቲካን በሽግግር ፍትህና ሀገራዊ ምክክር ለመፍታት የሚያስችል ተስፋ የተሰነቀበት ነው ሲሉም ገልጸዋል።

መጋቢት 24 የህዝቦችን የዘመናት ጥያቄዎች በህገ መንግስታዊና በዲሞክራሲያዊ መንገድ እንዲመለሱ በማስቻል አበርክቶው የጎላ መሆኑን መግለፃቸውን የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን መረጃ ያመለክታል።

መሰል ስኬቶችና ነፃነቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የውስጥ አንድነትን ማጠናከር ሉአላዊነትን መጠበቅ እንዲሁም የመልማትና የመበልፀግ አቅሞችን መጠቀም እንደሚገባም አሳስበዋል።

የነገ ኢትዮጵያን ዛሬ መስራትና ለነገ ትውልድ በየፈርጃችን ዛሬ ላይ መትጋት ይኖርብናል ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል።

መጋቢት 24 ቀን 2017 ዓም
👍7👎6👏1
ከ22 ቶን በላይ ወርቅ ለውጪ ገበያ ቀርቧል
****
(ኢ ፕ ድ)

በ2017 በጀት ባለፉት ስምንት ወራት 22 ነጥብ 5 ቶን ወርቅ ለውጪ ገበያ ማቅረቡን የማዕድን ሚኒስቴር አስታወቀ።

ኢንዲስትሪና ማዕድን ጉዳዮች ቋሚ ኮሜቴ የማዕድን ሚኒስቴርን የስምንት ወር የዕቅድ አፈጻጸም ገምግሟል።

የማዕድን ሚኒስትር ኢንጅነር ሀብታሙ ተገኘ ባለፉት ስምንት ወራት 22 ነጥብ 5 ቶን ወርቅ ለውጪ ገበያ መቅረቡን ለኢንዲስትሪና ማዕድን ጉዳዮች ቋሚ ኮሜቴ ባቀረቡት ሪፖርተር ገልጸዋል።

በስምንት ወራት ውስጥ ሰድስት ቶን ወርቅ ለውጪ ገበያ ለማቅረብ ታቅዶ እንደነበር ጠቅሰው፤ 22 ነጥብ 5 ቶን ወርቅ ማቀርብ መቻሉን ገልጸዋል።

ለውጪ ገበያ እየቀረበ ያለው የወርቅ ምርት አሁን ባለበት ሁኔታ ከቀጠለ በበጀት ዓመቱ መጨረሻ 33 ቶን ወርቅ ይደርሳል። ይህም ኢትዮጵያን ከፍተኛ ወርቅ ለውጪ ከሚያቀርቡ የአፍሪካ ሀገራት ተርታ የሚያሰልፍ ነው ብለዋል።

የወርቅ ምርት በኩባንያዎችና በባህላዊ መንገድ እየተመረተ መሆኑንን በሪፖርታቸው የገለፁት ሚኒስትሩ፤ ከተመረተው ወርቅ 95 በመቶ የሚሆነው በባህላዊ መንገድ የተመረተ መሆኑን ገልጸዋል።

ባለፋት ስምንት ወራት ከማዕድን ዘርፍ ወጪ ንግድ ከተገኘው አንድ ነጥብ 88 ቢሊዮን ዶላር ትልቁን ድርሻ ይይዛል።

የወርቅ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ አነስተኛ የወርቅ ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎችን ስራ እንደሚጀምሩም ገልጸዋል።

በታደሠ ብናልፈው

መጋቢት 24 ቀን 2017 ዓም
👍7
“በድህነት ለተሳለቁብን፤ ከዚያ ካላችሁበት አረንቋ አትወጡም፣ የብልጽግናን ሽታ አታዩትም፣ መልማት አይቻላችሁ፣ መሻገር አይሆንላችሁ ለእናንተ የተገባና የተፈቀደ አይደለም ላሉን ግለሰቦችና ቡድኖች፤ ሕዝብ ከወሰነ፣ ሀገር ከወሰነ፣ ምን ሊያመጣ እንደሚችል፣ ሕዳሴም አረጓዴ ዐሻራም ያሳያሉ"

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

ነሐሴ 2016 ዓም ከተናገሩት የተወሰደ

#ዓባይ_ግድብ #ኢትዮጵያ #ህዳሴ #ታዳሽኃይል #ኢነርጂ #የአየርንብረትለውጥ
👍11👏81
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
Photo
👉 ባለፉት ስምንት ወራት የኢትዮጵያ የውጪ ንግድ 4 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ደርሷል፣

👉 የጥራት መንደሩ በአመት ከ4 ነጥብ 5 ሚሊየን ቶን በላይ ወጪና ገቢ ምርቶችን ጥራት ያረጋግጣል፣

👉 በኢትዮጵያ ረቂቅ የንግድ ፖሊሲ ላይ የባለድርሻ አካላት የውይይት መድረክ ተጀምሯል፣
*****
(ኢ ፕ ድ)

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በመድረኩ ላይ እንደገለጹት፣ በ2010 ዓም የኢትዮጵያ የውጪ ንግድ 2 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር የነበረ መሆኑን ጠቅሰው በስምንት ወራት የውጪ ንግድ 4 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ደርሷል።

በ2017 በጀት ዓመት መጨረሻ ከ6 ቢሊየን ዶላር በላይ ለማድረስ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

መንግስት የንግዱ ዘርፍ ተወዳዳሪና ተገማች ለማድረግ በመስራት ላይ መሆኑን መሆኑን ጠቅሰው ንግዱ ቀጠናውን የሚያስተሳስር የንግድ ልውውጥ ለማድረግ መሆኑንም ገልጸዋል።

በሀገሪቱ የንግድ ፖሊሲ እንዳልነበረ በመግለጽ ከብዙ ጥረትና ድካም በኋላ ረቂቅ የንግድ ፖሊሲ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

ባለፉት ስምንት ወራት 2 ነጥብ 5 ሚሊየን የንግድ ማህበረሰብ አዲስ የንግድ ፈቃድ አውጥቷል። ከአንድ ሺህ 300 በላይ የቅዳሜና እሁድ ገብያዎችን በማደራጀት ሸማቹን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሥራዎች መሰራታቸውን ገልጸዋል።

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በንግዱ ዘርፉ ላይ ለውጥ እያመጣ እንደሚገኝ ጠቅሰው የኢትዮጵያን የአለም የንግድ ድርጅት አባል ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያን የአለም የንግድ ድርጅት አባል እንድትሆን የሚያስችል ተጨባጭ ተስፋ ታይቶበታል ያሉት ሚኒስትሩ የንግድ ፖሊሲው ሀገሪቱ ያላትን ዝግጁነት የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል።

ሀገሪቱ ጥራት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የጥራት መንደርን ከ8 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ መገንባቱን ጠቅሰው በዓመት ከ4 ነጥብ 5 ሚሊየን ቶን በላይ ወጪና ገቢ ምርቶችን የጥራት የማረጋገጥ ሥራ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

በማርቆስ በላይ

መጋቢት 25 ቀን 2017 ዓም
👍51👏1
የኢትዮጵያ አየር መንገዱ ወደ ማካው ከተማ የመጀመሪያ የካርጎ በረራውን አደረገ
****
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻይናዋ ማካው ከተማ የመጀመሪያ የካርጎ በረራውን በዛሬው ዕለት አድርጓል።

አየር መንገዱ በማካው ባስጀመረው የካርጎ አገልግሎት ስነ ስርዓት ላይ በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈራ ደርበው እንደገለፁት የአገልግሎቱ መጀመር አየር መንገዱ የካርጎ ትስስሩን ለማስፋትና የዓለም ንግድን ለማሳለጥ ያለው ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አየር መንገዱ በቻይና የካርጎ መዳረሻውን ወደ 10 ከፍ ማድረጉን በቤጂንግ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።

መጋቢት 25 ቀን 2017 ዓም
👍9👏1
ከለውጡ ወዲህ በቱሪዝሙ ዘርፍ የተመዘገቡ ውጤቶች‼️

👉 225 ኢንቨስትመንቶች ተጠናቀው አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል

👉 472 የአሀገር ውስጥና የውጭ ባለሃብቶች ዘርፉን ተቀላቅለዋል፣

👉 ደረጃቸውን የጠበቁ የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ብዛት ቀድሞ ከነበረበት ወደ አንድ ሺህ 573 አድጓል

👉 ከአራት ሚሊዮን 169 ሺ 646 የውጭ ቱሪስቶች ኢትዮጵያን ጎብኝተዋል

👉 ከውጭ ጎብኚ15 ነጥብ 64 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል፣

👉 የሀገር ውስጥ ቱሪዝም በፊት ከነበረበት 18 ሚሊዮን ወደ 58 ነጥብ 2 ሚሊዮን ጎብኚዎች አድጓል፣

የሀገር ውስጥ ቱሪዝምን ለማነቃቀትና የጉብኝት ባህልን ለማጠናከር በተሰሩ የማስተዋወቅና ስርፀት ስራዎች ከለውጡ በፊት ከነበረበት 18 ሚሊዮን በአሁኑ ወቅት ወደ 58 ነጥብ 2 ሚሊዮን ማደጉን የፕላንና ልማት ሚኒስቴር አመላክቷል።

በመስከረም ሰይፉ

መጋቢት 25 ቀን 2017 ዓም
👍10👎1