Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.76K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ሌ/ጄኔራል ታደሰ ወረደ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንትነትን ሲረከቡ የፈረሙት የትግራይ ክልል አካታች ጊዜያዊ አስተዳደር የተልዕኮ አፈጻጸም የቃል ኪዳን ሰነድ‼️

መጋቢት 30 ቀን 2017 ዓም
👍6
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት‼️

ባለፈው አንድ ወር ገደማ የኢትዮጵያን ሕገ መንግሥት፣ የፕሪቶርያን ስምምነትና የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡን ምክር በማከል ሰፊ ውይይቶች ሲካሄዱ ቆይተዋል። የአቶ ጌታቸው የሥልጣን ዘመን በሕጉ መሠረት ሲያበቃ የሚቀሩ ቁልፍ ሥራዎችን የሚያከናውን አካል፣ ጊዜያዊ መንግሥቱ መቀጠለ አለበት የሚል ድምዳሜ ከተያዘ በኋላ፣ ይሄንን ሽግግር ማን መርቶ ከግብ ሊያደርስ ይችላል? የሚሉ ውይይቶችን ስናደርግ ቆይተናል።

ዛሬ በሰላማዊ መንገድ በአዲስ ባህል የሥልጣን ሽግግሩንና ቅብብሎሹን ለማካሄድ የተዘጋጀ ፕሮግራም አከናውነናል።

ሌ/ጄኔራል ታደሰ ባለፋት ሁለት ዓመታት የአቶ ጌታቸው ምክትል ሆነው ያገለገሉ ሰው ናችው። ባለፋት ሁለት ዓመታት የነበሩ ድካሞችንና ጥንካሬዎችን በግልጽ የሚገነዘቡ ሰው ናቸው።

አሁን ትግራይ ውስጥ ያለውን ክፍተት ሞልተው ወደ ፊት ሊወስዱ ይችላሉ የሚል እምንት በብዙ አካላት የታመነ ነው። የትግራይ ሕዝብ የጠማውን ሰላምና ልማት፣ እንደ ሌሎች ወንድሞቹ ወጥቶ የመግባት መሻት ስናሳካ፣ ለኢትዮጵያም ለአፍሪካም እጅግ ጠቃሚ የሆነ ነገር ሠርቶ ለማለፍ ታሪክ የሰጣቸውን ዕድል እንደሚጠቀሙበት ተስፋ አደርጋለሁ።

መጋቢት 30 ቀን 2017 ዓም
👍12
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሃሙድ አሊ ዩሱፍ ጋር ያደረጉት ቆይታ‼️
5👏2👍1
የቀድሞው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አሰተዳደር ፕሬዝዳንት የትግራይን ህዝብ አመሰገኑ

የሁለት ዓመት የጊዜያዊ መስተዳድር ሀላፊነቴን በይፋ አስረክቤያለሁ። የትግራይ ህዝብ ላሳየኝ ክብርና ድጋፍ ላቅ ያለ ምስጋና አለኝ። ህዝባችን ወደ ተሻለ ሁኔታ እንዲመለሰ ሁለንተናዊ ፍላጎቱ እንዲሟላለት የተቻለኝን ሁሉ አደርጋለሁ። የሰላምና የለውጥ ፍላጎት እንዳይሰናከል ትግላችንን እናጠናክር። ክብረት ይስጥልኝ!"

አቶ ጌታቸው ረዳ

መጋቢት 30 ቀን 2017 ዓም
12👍2👎1😁1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የፕሬዚዳንትነት ርክክብ ሥነሥርዓት‼️
😁2
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 4 አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ
******
(ኢ ፕ ድ)
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በ4ኛ ዓመት 9ኛ መደበኛ ስብሰባው አራት አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አስተላልፏል።

በዚህም መሰረት፤-

1ኛ. በፕላንና ልማት ቢሮ እና በትምህርት ሚኒስቴር በጋራ ተጠንቶ የቀረበዉን ከአራት ኪሎ እስከ ሽሮ ሜዳ ያለዉ አካባቢ የዩኒቨርሲቲ መንደር በመሆን በአካባቢዉ ያሉትን አገልግሎቶች አካቶ የትምህርት፣ የምርምር፣ የእውቀትና የባህል ልህቀትን በከተማዋ ለማሳደግ በሚያስችል አግባብ የቀረበ በመሆኑ፤ ካቢኔዉ ተወያይቶ የመንደር ምስረታውን ዉሳኔ አፅድቋል፡፡

2ኛ. የምግብ ስርዓትና ኒዉትሪሽን ምክር ቤት ማቋቋሚያ ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ ዉሳኔ አስተላልፏል።

3ኛ. የአደጋ ስጋት አመራር ምክር ቤትና የአደጋ ዝግጁነት ፈንድ ማቋቋሚያ ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ ዉሳኔ አስተላልፏል፡፡

4ኛ. በመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቀረበዉን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያላቸዉ ፕሮጀክቶች፤ የመሬት ምደባ ጥያቄዎች አስመልክቶ ካቢኔዉ ተወያይቶ ዉሳኔ ማሳለፉን ከከንቲባ ፅሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

መጋቢት 30 ቀን 2017 ዓም
👍5
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
Photo
በቀጣዮቹ ጊዜያት የትግራይን ህዝብ ልማት እና የለውጥ ፍላጎት የሚያሳኩ ተግባራት ይከናወናሉ
******
(ኢ ፕ ድ)
በቀጣዮቹ ጊዜያት የትግራይን ህዝብ ልማት እና የለውጥ ፍላጎት የሚያሳኩ ተግባራት እንደሚከናወኑ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደ ገለጹ።

የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር የፕሬዚዳንት ርክክብ ስነ ስርዓት ተካሂዷል።

በዚህም ሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደ፥የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንትነትን ተረክበው የትግራይ ክልል አካታች ጊዜያዊ አስተዳደር የተልዕኮ አፈጻጸም የቃል ኪዳን ሰነድን ፈርመዋል።

በሥነ-ስርዓቱም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ ተወካዮች ተገኝተዋል።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ሌተናል ጄኔራል ታደሰ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፥ባለፉት ሁለት ዓመታት ያልተሰሩ በቀጣይ መሰራት ያለባቸው በርካታ ተግባራት አሉ።

ከፕሪቶሪያው ስምምነት አፈጻጸም ጋር የተያያዘ ብቻም ሳይሆን የተፈጠሩ የጸጥታ፣የፖለቲካ እንዲሁም የኢኮኖሚ ችግሮች መኖራቸውን ገልጸዋል።

እነዚህ ችግሮች ቀላል አለመሆናቸውን ገልጸው፥በዚህ ላይ ለውጥ ለማምጣት በትኩረት እንደሚሰራም አረጋግጠዋል።

በቀጣዮቹ ጊዜያት የትግራይን ህዝብ የልማት ጥያቄ እና የለውጥ ፍላጎት የሚያሳኩ ተግባራት እንደሚከናወኑ ጠቁመዋል።

እንዲሁም የፕሪቶሪያ ስምምነት ሙሉ በሙሉ እንዲተገበር እንደሚሰራ እንዲሁም ያሉ ውጥረቶችን የማርገብ ስራ እንደሚከናወን አመልክተዋል።

የህዝቡን የለውጥ ፍላጎት ለማሳካት የሚሰራበት መሆኑን ጠቅሰው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የቀድሞው ፕሬዚዳንት ጌታቸው ረዳ በበኩላቸው፥ጊዜያዊ አስተዳደሩ ባለፉት ሁለት ዓመታት በርካታ ስራዎችን መስራቱን ገልጸዋል።

ለአብነትም አገልግሎቶችን የመመለስ፣ የሰብዓዊ ድጋፍ እንዲሁም ተፈናቃዮችን የመመለስ ስራ መሰራቱን ገልጸው፤ ነገር ግን በቂ አለመሆናቸውን ተናግረዋል።

የፌዴራል መንግስት ለተጨማሪ አንድ ዓመት የጊዜያዊ አስተዳደሩ እንዲቀጥል ማድረጉ አዎንታዊ ተግባር መሆኑንም ገልጸዋል።

የትግራይን የሰላም እና የለውጥ ፍላጎት ለማሳካት እና የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በውስጥ የነበሩ የፖለቲካ ንትርኮች የፕሪቶሪያ ስምምነት በተሟላ መልኩ እንዳይከናወን በማድረግ ረገድ የአንበሳውን ድርሻ እንደሚወስድ አንስተዋል።

እርስ በእርስ በመጓተት መቀጠል እንደማይቻል የገለጹት አቶ ጌታቸው፥የተገኘውን ሰላም ለማደብዘዝ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች መኖራቸውን በመገንዘብ ሰላሙን ለማጽናት ጠንክሮ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

አሁን ላይ በትግራይ ህዝብ ዘንድ ያለው የሰላም እና የለውጥ ፍላጎት ሊቀለበስ የማይችል መሆኑን ገልጸዋል። እነዚህን ከግምት በማስገባት የቀሩ ስራዎችን ማጠናቀቅ ስራ ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

መጋቢት 30 ቀን 2017 ዓም
👍94