Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
"በዚህ ዓመት ከቡና የወጪ ንግድ 3 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት በትኩረት ይሰራል"

-የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ
++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | በ2018 ዓ.ም ከቡና የወጪ ንግድ 3 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት እየተሰራ መሆኑን የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

"ፈጠራና ፍጥነት ለቡናችን ስኬት" በሚል መሪ ቃል ሃገር አቀፍ የቡና ኤግዚቢሽንና እውቅና መርሃ ግብር በሳይንስ ሙዚየም ተካሂዷል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በመርሐግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር የአረንጓዴ ልማት ስራውን ካሻሻለው አንዱ የቡና ዘርፍ ነው።

በዚህም አርሶ አደሩ ቡናን በክላስተር እንዲያመርት፣ በተሻለ ዋጋ እንዲሸጥ እና ወደ ውጪ የሚላከው ምርት እንዲጨምር አድርጓል ብለዋል።

በ2018 በጀት ዓመት 600 ሺህ ቶን ቡና ወደ ውጪ በመላክ 3 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት በትኩረት እንደሚሰራም ገልፀዋል።

ቡና ኢኮኖሚያዊ ብቻ ሳይሆን ማህበራዊ ጠቀሜታው ከፍተኛ በመሆኑ የአገር ውስጥ ፍጆታውም በዛው ልክ ከፍ ማለቱን አመላክተዋል ።

ቡናን በዘመናዊ መንገድ የማልማት ስራው ላይ በማተኮርና በዓለም ተወዳዳሪ እንዲሆን ማድረግ ያስፈልጋል ያሉት አቶ ተመስገን እሴት ጨምሮ ወደ ውጭ መላክ ቀጣይ የቤት ስራ ስለሚሆንም የዘርፉ ላኪዎች እራሳቸውን የማብቃት ስራዎችን እንዲሰሩ አሳስበዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ2017 ዓ.ም በቡና፣ ሻይ እና ቅመማ ቅመም የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ላኪዎች እውቅና ሰጥተዋል።

በዳግማዊት አበበ
+++++++++++
#gazette_plus #ጋዜጣ_ፕላስ
4
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ላውረንስ ዎንግ በእድገትና አመራር ልምዶቻቸውን ለመለዋወጥ ለእሳት ዳር ወግ ተቀምጠዋል። #PMOEthiopia
5👍3
በማርበርግ ቫይረስ እስካሁን የ6 ሰዎች ሕይዎት አልፏል
++++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | በማርበርግ ቫይረስ የ6 ሰዎች ሕይዎት ማለፉን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

የጤና ሚኒስቴር የማርበርግ ቫይረስ ወቅታዊውን ሁኔታን በሚመለከት ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጥቷል።

የጤና ሚኒስትር መቅደስ ዳባ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ ጤና ሚኒስቴር የማርበርግ በሽታ ካሳወቀበት ህዳር 5 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ቫይረሱን ለመግታት በርካታ ስራዎችን እየሰሩ ይገኛል።

ቫይረሱ ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ እሰከ ዛሬ ጠዋት ድረስ 73 ላብራቶሪ ተሰርቶ በ11 ግለሰቦች ላይ ቫይረሱ መኖሩ ተረጋግጧል ብለዋል።

ቫይረሱ ከተገኘባቸው 11 ሰዎች የ6 ሰዎች ሕይዎት ማለፉን እና 5 ሰዎች በህክምና ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል።

በሕክምና ላይ ካሉት ሰዎች መካከል ደግሞ አንዱ ጽኑ ህሙም እንደሆነ አመላክተዋል።

በበሽታው ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ 349 ሰዎች ተለይተው ክትትል ሲደረግ መቆየቱን ገልጸው፤ 119 የክትትል ጊዜ ገድብ ጨርሰው ወጥተዋል ብለዋል።

ምልክት ከታየባቸው ሰዎች ጋር ንክኪ ሲኖር እራስን መለየት፣ እጅን በሳሙና መታጠብ እና ሌሎች የጥንቃቄ ስራዎችን መስራት ከሁሉም እንደሚጠበቅ ገልጸዋል።

በሄለን ወንድምነው

#ጋዜጣ_ፕላስ #ጤና #ኢትዮጵያ #ማርበርግ #ቫይረስ
14
አፍሪካውያን ተጽእኖ ፈጣሪ ሴቶች
+++++++++++++++

ዘርፈ-ብዙ ተፅእኖዎችን በመስበር እና ሌሎች ዕድሎችን በመፍጠር ከታሪክ አኳያ ተደማጭነትን ያተረፉ፣ በጦረኝነት እና በአመራር ብቃት ኃያላን ንግሥት የነበሩ፣ በፖለቲካ፣ በንግድ፣ በሰብዓዊ መብት ተሟጋችነት፣ በጥብቅና ሥራ ስኬትን ያገኙ እና ዓለም አቀፋዊ እውቅናን ያገኙ በርካታ አፍሪካዊ ሴቶችን መጥቀስ ይቻለል፡፡

ከእነዚህ መካከል በንግሥና ዘመናቸው ብርቱና ቆራጥ አመራር የሰጡ፣ ጎበዝ ዲፕሎማትና ወታደራዊ ስትራቴጂስት የነበሩ፣ ከቅኝ ገዢዎች ጋር በመታገል የመንግሥታቸውን እና የሕዝባቸውን ነፃነት ያስጠበቁ፣ የ17ኛው ክፍለ ዘመኗን የአንጎላዋ ንግሥት ንዚንጋ፣ የናይጀሪያዋ የዛዛው መንግሥት አሚና፣ ደቡብ አፍሪካዊቷ ዊኒ ማዲኪዜላ ማንዴላ፣ የጋናዋ ያአ አሳንቴዋ እና የእኛዋ ንግሥት ጣይቱ ብጡል ይጠቀሳሉ።

ሙሉ ጽሑፉ ተከታዩን ማስፈንጠሪያ በመጫን ያገኙታል https://press.et/am-digital-content/share/am-stories/40vj94a53qpdg5ms91511z5h41
6
ኮፕ 32 ቁልፍ የዝግጅት ተግባራትን ለማቀናጀት የሚያስችል የብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ስብሰባ ተደረገ
++++++++++++++


#ጋዜጣ_ፕላስ - በትናንትናው ዕለት የኮፕ 32 ተወካይ ፕሬዚዳንት መሰየምን ተከትሎ ዛሬ ጠዋት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ቁልፍ የዝግጅት ተግባራትን ለማቀናጀት የሚያስችል የብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ስብሰባ ተደርጓል።

ስብሰባው ኢትዮጵያ ኮፕ 32ን ስታስተናግድ አካታችና በሚገባ የተሰናዳ ጉባኤ እንድታሳካ ለማረጋገጥ መንግሥት ያለውን ቁርጠኝነት ያሳየበት እንደነበር የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታውቋል። #PMO
#PMOEthiopia #COP32 #G20
3👍1