Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
አፍሪካውያን ተጽእኖ ፈጣሪ ሴቶች
+++++++++++++++

ዘርፈ-ብዙ ተፅእኖዎችን በመስበር እና ሌሎች ዕድሎችን በመፍጠር ከታሪክ አኳያ ተደማጭነትን ያተረፉ፣ በጦረኝነት እና በአመራር ብቃት ኃያላን ንግሥት የነበሩ፣ በፖለቲካ፣ በንግድ፣ በሰብዓዊ መብት ተሟጋችነት፣ በጥብቅና ሥራ ስኬትን ያገኙ እና ዓለም አቀፋዊ እውቅናን ያገኙ በርካታ አፍሪካዊ ሴቶችን መጥቀስ ይቻለል፡፡

ከእነዚህ መካከል በንግሥና ዘመናቸው ብርቱና ቆራጥ አመራር የሰጡ፣ ጎበዝ ዲፕሎማትና ወታደራዊ ስትራቴጂስት የነበሩ፣ ከቅኝ ገዢዎች ጋር በመታገል የመንግሥታቸውን እና የሕዝባቸውን ነፃነት ያስጠበቁ፣ የ17ኛው ክፍለ ዘመኗን የአንጎላዋ ንግሥት ንዚንጋ፣ የናይጀሪያዋ የዛዛው መንግሥት አሚና፣ ደቡብ አፍሪካዊቷ ዊኒ ማዲኪዜላ ማንዴላ፣ የጋናዋ ያአ አሳንቴዋ እና የእኛዋ ንግሥት ጣይቱ ብጡል ይጠቀሳሉ።

ሙሉ ጽሑፉ ተከታዩን ማስፈንጠሪያ በመጫን ያገኙታል https://press.et/am-digital-content/share/am-stories/40vj94a53qpdg5ms91511z5h41
6
ኮፕ 32 ቁልፍ የዝግጅት ተግባራትን ለማቀናጀት የሚያስችል የብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ስብሰባ ተደረገ
++++++++++++++


#ጋዜጣ_ፕላስ - በትናንትናው ዕለት የኮፕ 32 ተወካይ ፕሬዚዳንት መሰየምን ተከትሎ ዛሬ ጠዋት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ቁልፍ የዝግጅት ተግባራትን ለማቀናጀት የሚያስችል የብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ስብሰባ ተደርጓል።

ስብሰባው ኢትዮጵያ ኮፕ 32ን ስታስተናግድ አካታችና በሚገባ የተሰናዳ ጉባኤ እንድታሳካ ለማረጋገጥ መንግሥት ያለውን ቁርጠኝነት ያሳየበት እንደነበር የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታውቋል። #PMO
#PMOEthiopia #COP32 #G20
3👍1
የመንግሥት ሠራተኞች የጤና መድን ተጠቃሚ ሊሆኑ ነው
++++++++++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | የመንግሥት ሠራተኞች በቀጣዩ 2019 ዓ.ም የጤና መድን አገልግሎት ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የኢትዮጵያ ጤና መድን አገልግሎት አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ጤና መድን አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ወርቁ እንደገለጹት፤ መደበኛ በሆኑ የሥራ መስኮች የተሰማሩ ዜጎች የጤና መድን አገልግሎት እንዲያገኙ ታስቦ የተዘጋጀው የማኅበራዊ ጤና መድን አገልግሎት በአዋጅና ደንብ ከጸደቀ 14 ዓመታትን አስቆጥሯል።

አዋጁ ሠራተኛው ከደመወዙ ሦስት በመቶው እንዲቆረጥና የፌዴራልና የክልል መንግሥታትም ለቀጠሩት ሠራተኛ ሦስት በመቶውን እንዲሸፍኑ ይደነግጋል።

ሆኖም ግን ባለፉት ዓመታት በመንግሥት በኩል በቂ ገንዘብ ባለመኖሩና በኑሮ ዉድነት አማካኝነት ሳይተገበር ቢቆይም በዘንድሮዉ ዓመት ግን የተሻለ ተስፋ ታይቷል ብለዋል።

በዘንድሮው ዓመት በጤናው ዘርፍ የተሰማሩ ከ500 ሺህ በላይ ሠራተኞች ለአገልግሎቱ መመዝገባቸውን የጠቀሱት ዳይሬክተሩ፤ ከገንዘብ ሚኒስቴርም 4 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር መጽደቁን ተናግረዋል።

በሚቀጥለው ዓመትም ሁሉም የመንግሥት ሠራተኛ ተጠቃሚ እንዲሆን የፌዴራልም ሆነ የክልል መንግሥታት በጀት ይይዛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ አመላክተዋል።

መስከረም ሰይፉ
#ጋዜጣ_ፕላስ #gazetteplus #ጤና_መድን #ጤና #ኢትዮጵያ
11👍3
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በመደመር መንግሥት ዕይታ፣ የዘርፎች እመርታ!
+++++++++++
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ለብልፅግና ከፍተኛ አመራሮች የሰጡት ስልጠና
ክፍል አንድ ዛሬ ምሽት 2:30 ይጠብቁን
1