Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በአማራ ክልል መንግሥት እና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት መካከል የሰላም ስምምነት ተደረገ
++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ l በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት መካከል የሰላም ስምምነት ተደርጓል።

የስምምነት ሰነዱን ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በኩል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ እና ከአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ተወካይ ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ ተፈራርመዋል።

የሰላም ስምምነቱን የአፍሪካ ህብረት እና ኢጋድ ያደራደሩት ሲሆን የሰላም ስምምነቱ በሁለቱም ወገን ሰላም ፈላጊነት የተገኘ መሆኑንም ተገልጿል።

በማርቆስ በላይ
#ጋዜጣ_ፕላስ #gazette_plus_english #አማራ #ሰላም
🤣8👏54👎3
"ኢትዮጵያ ከአይ ኤም ኤፍ /IMF/ ጋር ያላትን ጠንካራ አጋርነት አጠናክራ ትቀጥላለች"

- አህመድ ሺዴ
++++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ | ኢትዮጵያ ከአይ ኤም ኤፍ /IMF/ ጋር ያላትን ጠንካራ አጋርነት አጠናክራ ታስቀጥላለች ሲሉ የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ ገለጹ።

የአይ ኤም ኤፍ ምክትል ሊቀመንበር ናይጄል ክላርክ በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያደረጉ ይገኛል።

የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ እና የአይ ኤም ኤፍ ምክትል ሊቀመንበር ናይጄል ክላርክ ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጥተዋል።

የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ እንደገለጹት፤ መንግስት የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ማሻሻያ በማጠናከር ኢኮኖሚያዊ እድገትን ለማረጋገጥ የሚሰሩ ስራዎችን አጠናክሮ ያስቀጥላል።

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በፋይናንስ በግብርና፣ በማዕድን፣ በቱሪዝም እና በሌሎች ዘርፎች ከፍተኛ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን ገልጸዋል።

የማሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በዓለም ደረጃ ጥሩ ግምት የሚሰጠው ውጤት እያስገኘ ነው ያሉት ሚኒስትሩ፣ ኢትዮጵያ ከአይ ኤም ኤፍ ጋር ያላትን ጠንካራ አጋርነትም አጠናክራ ለማስቀጠል ያላትን ፍላጎት አፅንኦት ሰጥተዋል።

የአይ ኤም ኤፍ ምክትል ዳይሬክተር ናይጄል ክላርክ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም ያላትን እድገት አድንቀዋል።

በማሻሻያው የዋጋ ግሽበት መቀነሱን፣ የውጭ ምንዛሪ ክምችት መጨመሩን ፣ የመንግስት ፋይናንስ መጠናከሩን እና የሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት መጠናከሩን አስታውቀዋል።

በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም በርካታ ውጤቶችን እያስገኘ መሆኑን ገልጸዋል።

አይ ኤም ኤፍ ለሀገሪቱ እና ለህዝቦቿ ኢኮኖሚውን የበለጠ ለማጠናከር በተራዘመ ብድር ኢትዮጵያን ለመደገፍ ቁርጠኛ ሆኖ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።

የአይኤምኤፍ ምክትል ሊቀመንበር ናይጄል ክላርክ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና ከሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች ጋር በኢትዮጵያ እየተከናወኑ ባሉ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች፣ በአይኤምኤፍ ድጋፍ እና የቀጣይ ትብብር ላይ ውይይት አድርገዋል።

በተጨማሪም የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን፣ ኮይሻን እና ሌሎች ሜጋ ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።

በሄለን ወንድምነው

#ጋዜጣ_ፕላስ #ኢትዮጵያ #አይኤምኤፍ
4👍2
"መምህራን በደመወዝ ይበልጠናል የሚሉት ‘ሴክተር’ የለም"
- ሽመልስ አበበ የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ምክትል ፕሬዚዳንት
++++++++++++++++++

#ጋዜጣ ፕላስ | በአሁኑ ጊዜ መምህራን በደመወዝ ይበልጠናል የሚሉት ‘ሴክተር’ የለም ሲሉ የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ምክትል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አበበ ገለጹ።

የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ምክትል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አበበ ለጋዜጣ ፕላስ እንደገለጹት፤ ባለፉት ጊዜያት የመምህራን ደመወዝ ከሌላው ሴክተር በብዙ መንገድ የተጎዳ እንደነበር አስታውሰዋል።

ከሲቪል ሰርቪስ እና ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በሚገባ በአጋርነት በመሰራቱ መምህራን አሁን ላይ በደመወዝ ይበልጠናል የሚሉት ሴክተር የላቸውም ሲሉ አስታውቀዋል።

መምህራን የተሻለ ደመወዝ ላይ ቢሆኑም፤ በሀገሪቱ ያለው የዋጋ ንረት ላይ መንግሥት ትኩረት ማድረግ ይገባዋል ብለዋል።

በሄለን ወንድምነው
++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ #መምህራን #ኢትዮጵያ #መምህር
11👍5👎2
የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት ከክልሉ መንግስት ጋር ያደረገው የሰላም ስምምነት የያዛቸው ዋና ዋና ነጥቦች
+++++++++

✍️ የአማራ ህዝብ በማንነቱ እንዳይገደል፣ እንዳይሳደድ እና እንዳይፈናቀል፤

✍️ የተፈናቀሉ ዜጎች እንዲመለሱ ማድረግ፤

✍️ የአማራ ክልል እኩል የመልማትና የመጠቀም መብት እንዲኖረው ማድረግ፤

✍️ በፋኖ ስም በፌደራልም ሆነ በክልል ማረሚያ ቤት ያሉ አባላት እንዲፈቱ፤

✍️ የቆሰሉ ሰዎችን መልሶ የማቋቋም ስራ እንዲሰራ፤

✍️ አቅምና እውቀት ያላቸው አባላት እንዲሁም የወታደር ቁመና ያላቸው የጸጥታ ሃይሉን እንዲሁም ማህበረሰቡን እንዲቀላቀሉ ማስቻል፤

✍️ የመንግስት ሰራተኞች ወደ መደበኛ ስራቸው እንዲመለሱና የቀረባቸው ጥቅማ ጥቅም እንዲከፈላቸው፤

✍️ ትምህርታቸውን ያቋረጡ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ የሚሉ ጉዳዮች ላይ ከመግባባት ተደርሷል፤

ምንጭ:- ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ
የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት የውጪ ጉዳይ መምሪያ ሃላፊ
25👏4
20ኛው የኢትዮጵያ የብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን

"ዲሞክራሲያዊ መግባባት፤ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት"

የ20ኛው የኢትዮጵያ የብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በዓል ታዳሚዎች - ሆሳዕና
1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
'ብሄራዊ ጥቅም' የምንፈልገው ፣ የምንሞትለትና የምንታገልለት ጉዳይ ነው- ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ
👉 https://youtu.be/ayTJYUFkmYM?si=YO-2yPTpz8ldvffQ
2
ጅማ ከተማ 21ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን እንድታዘጋጅ ተመረጠች
+++++++++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | ጅማ ከተማ 21ኛውን የብሔር ብሔረሰቦች ቀን እንድታዘጋጅ ተመረጠች።

20ኛው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች በዓል “ዴሞክራሲያዊ መግባባት፣ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ሃሳብ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ነው።

በዚሁ መርሃግብር ላይ ጅማ ከተማ በቀጣይ ዓመት 21ኛውን የብሔር ብሔረሰቦች ቀን እንድታዘጋጅ ተመርጣለች።

በልጅዓለም ፍቅሬ
+++++++++++++++++
#Gazetteplus #ጋዜጣፕላስ #ጅማ
5